>

ፈጣሪም ሌላ እንዲያደርግ ላረገው ነገር ይመሰገን የለም እንዴ? (ደረጀ ገረፋ ቱሉ)

ኢትዮጵያ ውስጥ አመፅ ብርቅ አይደለም።ትናንሾቹን ሳንጨምር በኢህአዲግ ዘመን እንኳን ሁለት ጊዜ መንግስትን አደጋ ላይ የሚጥሉ አመፆች ተቀስቅሷል።አንደኛው በ1997 ሲሆን ሁለተኛው 2008 ሙሉውን እና 2009 መጀመሪያ ላይ የተካሄደው ነው።
ሁለቱም አመፆች በህዝብ ደረጃ መንግስትን ለመጣል ደርሰዋል። መንግስት ያልወደቀው አመፁ ጠንካራ ስላልሆነ ሳይሆን አመፁን መንግስትን ለመቀየር የተጠቀመበት ጠንካራ የተደራጀ ኃይል ስላሌለ ነው።
ሌላው ቀርቶ በ2006 የተካሄደው አመፅ እራሱ ዘንድሮ እየሆነ ካለው አመፅ ጋር ስወዳደር ከበድ ያለ ነው።በኢህአዲግ ባህሪ የሶስት ቀን የቤት ውስጥ መዋል አድማ እስረኛ ማስፈታት ሳይሆን ብዙ እስረኛ የሚያሳስር እና ብዙ ሱቅ የሚያስወርስ ነው።ይህንን ደግሞ በ 1990ዎቹ መጀመሪያ ላይ ኪራይ ለምን ተጨመረብን ብለው ሱቃቸውን ለሰዓታት በመዝጋታቸው የተወረሱት እነ ሸምሱ እና ዘርመጭት ምስክር ናቸው።
በአጠቃላይ ወደ ኃላ ሄደንም ሲናይ የኃይለስላሴ መንግስት ከወደቀ በኃላ በደርግ የመጀመሪያ ዓመታት ላይ በኢህአፓ እና በሜአሶን የተመራ ከባድ የህዝብ አመፅ ነበር።ነገር ግን ይህ አመፅ ስርዓቱን ዜጎችን ከማስቃየት እና ከማሳሰር አላስቆመም ።
በ1983ትም እንዲሁ ከፍተኛ የሆነ የህዝብ አመፅ ነበረ።በተለይ ኦሮሚያ ላይ የነበረው ኦህዲድ ከዛሬው ተክለሰውነቱ ጋር ስወዳደር እጅግ ደካማ ነበር።ያኔም ቢሆን መንግስት ብዙ ዜጎችን ከማሰር እና ከማሰቃየት በስተቀር የታሰሩትን ለመፍታት እና የማሰቃያ ከምፖችን ለመዝጋት አልሞከረም።

ያኔ የታሰሩት እነ ነdh ገመዳ እና ሌሎች አንጋፋ የኦሮሞ ታጋዮች ዛሬ ድረስ መኖር መሞታቸው አይታወቅም።

ከላይ እንደገለፅኩት በ1997 እና በ1998 ዓም የነበረው አመፅ እጅግ ከፍተኛ ቢሆንም እስረኞችን በማስፈታት ሀገሪቷን ወደ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት አልወሰዳትም።እንዲሁም ሀገሪቷን ከዲሞክራሲያው ስርዓት ወደኃላ የጎተቷት የፕሬስ ህግ፣የፀረ ሽብር ፣የመያዶች ህግ እና ሌሎችም ህጎች በፍርሃት ኢህአዲግ እንዲያወጣ ነው ያደረገው።
በእርግጥ ነገሮች ከተረጋጉ በኃላ በህዝብ ግፍት ሳይሆን በምዕራባውያን ግፍት ኢህአዲግ የቅንጅት መሪዎችን ፈትቷል።ያም የሆነው በአመጽ ምክንያት ሳይሆን ኢህአዲግ ስለተረጋጋ እና ለልማት እርዳታ ፍለጋ እጅ መንሻነት ያደረገው ነገር ነው።
በሀገራችን ታሪክ ከተደረጉት አመፆች የድምፃችን ይሰማን አመፅ መርሳት አይቻልም።ይህንንም አመፅ ተከትሎ ኢህአዲግ ሌሎቹን እስረኞች መፍታት ሳይሆን ከሱ ጋር ስደራደሩ የነበሩትን የኮሚቴ አባላት ማሰር ነበር።
በ2006ም የኦሮሞ አመፅን ተከትሎ የሆነውም ያው ነው።
በ2008 የካቲት እና መጋቢት ወር ላይ የኦሮሞ ህዝብ ያደረገው አመፅ ታሪክ የማይረሳው ነው።ነገር ግን ይህም አመፅ ቢሆን ኦህዲድ ያለ የፌደራል መንግስት እውቅና በማዕከላዊ ኮሚቴው በኩል የአመፁ መንስዔ የሆነውን ማስተር ፕላን ቢያስቀርም ብዙ ህዝብ እንዳይታሰር አለደረገም።እንዲሁም እነ በቀለ እና ሌሎች የ OFCአመራሮች የታሰሩት ይህንን የህዝብ አመፅ ተከትሎ ነው።
በ2008 ክረምት ላይ በአማራ እና በኦሮሚያ ከፍተኛ አመፅ ተክህዶ መንግስትን በጣም ጭንቅ ውስጥ ከቶት ነበር።በዚህም ጊዜ ቢሆን መንግስት መፍትሄ አድርጎ የወሰደው ነገር ቢኖር ብዙ ሰው ማሰረን ነው።
በ2009 ዘጠኝ የኢሬቻን በዓል ተከትሎም የተካሄደው አመፅ ውጤቱ ብዙ እስረኛ እንድለቀቅ አላደረገም።ያው እጅግ ብዙ ህዝብ እንዲታሰር ነው ያደረገው።
ከዚያ ወዲህ በኢትዮጵያ ምድር የተደረጉት አመፆች ከ2008 እና ከ2009 አመፅ ጋር ስነፃፀር ያን ያህል ጠንካራ አልነበሩም።
የ2008ቱ አመፅ ግን ሌሎች አመፆች ያላደረጉትን አንድ የተለየ ነገር ማድረግ ችሏል።የ2008ቱ አመፅ ትልቁ ውጤቱ እና አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ለሆነው በጎ ነገር መሰረት ጥሎ ያለፈው ኦህዲድ ውስጥ የለውጥ ኃይል የሆነውን የለማ ቡድን ስልጣኑን እንዲቆጣጠር ማድረጉ ነው።
ይህ በህዝብ ኃይል ወደስልጣን የመጣው ቡድን ወደ ስልጣን በመጣ በአንድ አመት እድሜው ያደረገው ነገር ቢሆን እንደሌሎቹ ባለስልጣን ስልጣንኑ ለመጠበቅ ህዝቡን ማሰር አይደለም ።ከሱ በፊት በክልሉ በየማጎሪያ ጣቢያ ተስረው የተረሱትን ማስፈታት ነው።በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ብቻ በክልሉ ከ30,000 በላይ እስረኞች ተፈቷል ።
ይህንን ሁሉ እስረኛ ስያስፈታ ያንን ያህል ለስልጣኑ አስግ የሆነ መሬት አንቀጥቅጥ አመፅ ስለተህካሄደ አይደለም።

የነለማ ቡድን ማሰር ሳይሆን መፍታት አመሉ ስለሆነ ነው እንጂ! 
ወደ ስልጣን የመጣው በህዝብ ኃይል ስለሆነ ላመጣው ህዝብ ውለታ መክፈሉ ነው እንጂ !!

የነለማ ቡድን እንደማንኛውም አምባገነን መንግስት በህዝብ እየተፈሩ ሳይሆን በህዝብ እየተፈቀሩ ማስተዳደር ስለፈለጉ ነው እንጂ!! ኢትዮጵያ ውስጥ አመፅ ሰው ሲያሳስር እንጂ እስረኛ አስፈትቶ አያውቅም።
ከሁሉ በላይ ያለፈው የኢህአዲግ ስራ አስፈፃሚ ስብስባ ለተስብሳብዎቹ ምን ያህል በጫና የተሞላ እንደነበር በቃላት መግለጽ ይከብዳል።የዚያ ጫና ምክንያት ግን ህዝብ እያደረገ ያለው አመፅ ሳይሆን ኦህዲድ እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ ነበር።የኢህአዲግ ስራ አስፈፃሚ ስሰበሰብ እና እስረኞችን ፈትቼ ማዕከላዊን እዘጋለሁ ስል ኢትዮጵያ ውስጥ ያንንም ያህል የህዝብ አመፅ አልነበረም ። እሄንን ነገር እደግመዋለሁ።

ደግሞ አምባገነን ስርዓት ስር በለች ሀገር አመፅ ቢኖርስ ?
ህዝብ ስያምፅ አምባገነን ስርዓት እያሰረ ከስልጣኑ ወርዶ ይታሰራል እንጂ የት ሀገር ነው ያሰረውን የፈታው?እንደዚያ ማ ከሆነ ምኑን አምባገነን ሆነ? 

የኦህዲድ አመራር ግን በኢህአዲግ ስራ አስፈፃሚ ስብሰባ ላይ የእስረኞች ይፈቱን ፤የፍትህ ስርዓቱ ይስተካከል እና ሌሎችንም አጀንዳዎችን ይዞ ተከራከተ።ሌሎች ወገኖች ደግሞ ኦሮሚያ ውስጥ ስርዓት አልበኝነት ስለ ሰፈነ አይደለም ሌላ እስረኛ ማስፈታት እነ ለማን ጨምሮ ሌሎች ዜጎችም ታስረው በክልሉ የሲቭል አስተዳደር ተወግዶ የወታዳራዊ አስተዳደር እንዲቆጣጠረው ነበር ሃሳብ ያቀረቡት ።እድለኞች ሆነን የነ ለማ ሃሳብ ተቀባይነት በማግኘቱ እነሆ በኢትዮጵያ ታሪክ አዲስ ምዕራፍ ተከፈተ።
በኢትዮጵያ ማንኛዉም አምባገነን ስርዓት እንደሚያደርገው ህዝብ ስያምፅ ብዙ ሰው ማሰር ሳይሆን በብዙ ምክንያት ላለፉት 25 ዓመታት ወደ ማጎሪያ ካምፕ የተወረወሩት ዜጎች በሙሉ ቀስ በቀስ ከእስር እየወጡ ነው።
አመፅ ይቀሰቅሳሉ ተብለው የታሰሩት እነ እስክንድር ፣ውብሼት፣ አንዷለም ዛሬ ከእስር ወጥተዋል ።
አመፅ ቀስቅሰዋል ተብለው የታሰሩት እነ በቀለ ፣ዶር መራሃ እና እጅግ ብዙ የህዝብ ልጆች ዛሬ ከእስር ተለቀዋል።
አመፅ ቀስቅሰዋል የተባሉት የሙስልም ኮሚቴ አፈላላጊዎች ዛሬ ከእስር ወጥተዋል ።
አምባገነን ስርዓት ባህሪው ህዝብ ሲያምፅ የታሰሩትን መፍታት አይደለም።እስከ መጨረሻው እስትፋንሱ ድረስ ያመፁትን መሳር ነው።አምባገነን ስርዓት ባህሪው እስከመጨረሻው እስትፋንሱ ድረስ እያሰረ መታሰር ነው።
በእምባገነን ስርዓት ያለው እውነታ በመጨረሻው ሰዓት ብዙ ማሰር ነው።በአምባገነን ስርዓት እስከመጨረሻው እያሰሩ ስሸነፉ ከአሸናፍው ጋር እስር ቤት መቀያየር ነው።አሳሪው ታሳር መሆን ነው።

እንደምናውቀው ኢህአዲግ አምባገነን ነው።

እናም በዛሬው ቀን ከአምባገነን ባህሪ በተቃራኒ የሆነው ሁሉ እንዴት ሆነ ብሎ መጠየቅ የግድ ነው።
ለእውነት የታሰሩ ሰዎች ዛሬ ተለቀው በክብር በመቶ ሺ ደጋፍዎች ፊት ለፊት ንግግር ሲያደርጉ፣ልጁ ፊት ለፊት እንደዚያ ተሸማቆ የተወሰደው እስክንድር ፣በቀለወዘተ ዛሬ በሸገር ጎዳናዎች እና በአዳማ አደባባይ ላይ በክብር እና እንደንጉስ ተጅበው ሲሄዱ አንዳቸውም የህዝብን አደራ ተቀብለው ይህንን ቀን በኢትዮጵያ እውን ያደረጉ ሰዎችን ስም ሳይጠሩ ስለፈረንጅ እና ዲያስፖራ ብቻ ምስጋና ስያቀርቡ በእውነት ለእውነት የታሰሩ ሰዎች ቢፈቱም በኢትዮጵያ ምድር ዛሬም እውነት እንደታሰረች ነው አልኩ። ዛሬም ብዙ ሰው ለጭብጨባ እንጂ ወደ ፊት ለሚወስዱን ነገሮች ብዙም ግድ የለውም። አንድ ነገር ከእውነትም በላይ እውነት ነው።
እነ በቀለ ፤ እነ መራራ እና ሌሎች ኢትዮጵያዊያን ባይታገሉ፣የኦሮሞ ህዝብ እና መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ባይታገል እነ ለማ እና አቢይ ወደ ኦህዲድ ስልጣን የመምጣታቸው እድል ዜሮ ነው ባይባልም ጠባብ ነው።ይህ ደረቅ እውነት ነው።

ሌላም ደረቅ እውነት አለ።
እነ ለማ ወደ ስልጣን ባይመጡ ዛሬ ኢህአዲግ ስልንጣ ላይ እያለ በዚህ ቀውጥ ጊዜ ብዙ በቀለዎች ፣ብዙ መራራዎች፣ብዙ አንዷለሞች፤ብዙ እስክንድሮች ፣ብዙ አህመድኖች ወደ ዘብጥያ ይወርዳሉ እንጂ ከእስር አይፈቱም ነበር።እሄም ደረቅ እውነት ነው።ኢህአዲግ እያሰረ ይታሰራታል እንጂ በተዓምር ይህ ቀን አይሆንም ነበር።
እነ ለማ ወደ ስልንጣ ያመጣቸውን ህዝብ ለማስደሰት የቻሉትን እያረጉ ነው። ነገር ግን ኤሊቱ በትንሽ በትልቁ ኢህአዲግ ውስጥ ለቀሩት አምባገነኖች ጅራፍ በማቀበል እያስገረፋቸው ነው። እናም ማንም ሰው መስራት ያለበት ለምስጋና መሆን ባይኖርበትም ።ፈረንጅ ሁሉ እየተጠራ ስመሰገን ስሰማ ጊዜ ሌላ እንዲያደርግ ለሰራው በጎ ነገር ፈጣሪስ ይመሰገን የለም እንዴ አልኩ!! ተሳስቼ ይሆን?
Filed in: Amharic