>

900 እስረኛ ከከርቸሌ ወጥቶ ፤90 ሚሊዮን ሕዝብ በአስቸኳይ አዋጅ ከርቸሌ ገባ፡፡ (በፍቃዱ ሞረዳ)

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅም እንደገና ታወጀ፤ ገዱም ሄደ፡፡ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አስፈላጊነት አንዱ ‹‹የሕዝቡን ከቦታ ቦታ ተዘዋዉሮ የመስራት መብት ለማስከበር ነዉ ›› ተብሏል፡፡ ሀቁ ግን የሕወሓትን ከቦታ ቦታ በነፃነት ተዘዋዉሮ የመስረቅ/ የመዝረፍ መብትን ሕጋዊ ማድረግ ነዉ፡፡አዋጁን አምኖ ተቀብሎ ለነፃ  ዘረፋና ግድያ እጅ መስጠት፣ አለያም…
ከወዲያ የገዱ ቡድን ተመቷል፡፡ ተረኛዉ የለማ ቡድን ሊሆን ይችላል፡፡ የሚቀጥለዉ ጉዳይስ ምን መሆን ይችላል? እነገዱን በእነ  ኮሎኔል ደመቀ መለወጥ ወይም እነለማን በእነመረራ ማካካስ የሚያዋጣ ግብይት ነዉ? የፖለቲካ ንግድ ስለማናዉቅ መልስ የለንም፡፡የኦሮሞና የአማራ ሕዝብ ዉሳኔ ነዉ፡፡
የታወጀብን አዋጅ ይህን ይመስላል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በመላ ሀገሪቱ ለ6 ወራት የጸና ይሆናል፡-የመከላከያ ሚኒስትርና የብሄራዊ ደህንነት ምክር ቤት ሰብሳቢ  ሲራጅ ፈጌሳ
 ባህርዳር፡ የካቲት 10 /2010 ዓ/ም(አብመድ)የአዋጁ መታወጅ ምክንያት በአንዳንድ አካባቢዎች ህገ-መንስታዊ ስርዓቱን የሚፈታተኑ ጉዳዮች በማጋጠማቸው እና የሰዎች መፈናቀል እና ህይወት ማለፍ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የሚከለክላቸው ወይም ገደቦች 18 ሲሆኑ ከእነዚህም ውስጥ
• ጽሁፍ ማሳተም
• ትዕይንት ማድረግ
• ሰላማዊ ሰልፍ
• በቡድን መንቀሳቀስ
• የጦር መሳሪያና ስለታማ ነገሮችን ይዞ መጓዝ አይቻልም፡፡
• ያለፍርድ ቤት መበርበር
•ለፀጥታው መረጋጋት አስጊ መስሎ ከተገኘ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ማንኛውም አይነት የመገናኛ ዘዴዎች ሊቋረጡ ይችላሉ ።
•የአስቸኳይ ጊዜ ኮማንድ ፖስትና የአፈፃጸም መምሪያ ቦርድ ተቋቁሟል ።
• እንደሁኔታው ታይቶ የሰዓት ዕላፊ ገደብ ማስቀመጥና ሌሎች ድንጋጌዎች አሉት ብለዋል ሚኒስትሩ
ከ15 ቀናት በኋላም ለተከበረው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይቀርባል፡፡
የመከላከያ ሚኒስትርና የብሄራዊ ደህንነት ምክር ቤት ሰብሳቢ ሲራጅ ፈጌሳ አሁን ላይ ስለ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አተገባበር በሰጡት መግለጫ አሳውቀዋል፡፡
 ሚኒስትሩ አክለውም አዋጁ የታወጀው በኢፌዴሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 93 መሰረትን አድርጎ ነው፡፡
ጋሻው ፈንታሁን ከአዲስ አበባ ለማንኛዉም ዘጠኝ ቦላሌ ከፈስ አያድንምና…ስንል እንደነበረዉ ‹‹ በእዉቀት ጎራዴ፣ በብልሃት ጋሻ››  መተጋተግ የሚቀጥል ይመስለናል፡፡
Filed in: Amharic