>

ብአዴን እና ኢፒዲኦ ፈጣሪያችሁ ወያኔ ሊያጠፋችሁ መወሰኑን እንድታውቁት

 – አባይ ጸሀየ ፡ እኛም ተናግረናል እነሱም ተናገረዋል ለመጠፋፋት ዝግጁ ነን!!

አዳነ አታነው

አባይ ጸሀየ የሚባል የወያኔ አለቃ ዛሬ አይጋ ገጽ ላይ በተለቀቀ የትግርኛ ኢዶዎ/ድምጽ ወደ አማርኛ ተተርጉሞ አባሪ በተደረገው መሰረት፣ ግልጽ በሆነ መንገድ ለኢሀዴግ አባል ድርጅቶች የማስጠንቀቂያ መልእክት አስተላልፏል፡፡ “ተስማምተን ካልሰራን” ማንም አሸናፊ ስለማይሆን ለመጠፋፋት ዝግጁ መሆናችን ሊታወቅ ይገባል ሲል መልእክቱን አስተላልፏል፡፡

አቶ አባይ ጸሀየ እንደሚታወቀው በ $77 ቢልዮን ብር ቅሌት ትክሻው ያበጠ ተራ ዘረኛ ግለሰብ ሲሆን፣ የኢሀዴግ የውስጥ ፖለቲካ “እኛም ተንግረናል እነሱም ተናግረዋል’ ሲል በአባል ድርጅቶች መሀከል የተካሄደውን የውስጥ ፍትጊያ ጠቅሷል፡፡ ስምምነት ላይ አንዳልተደረሰ እና በተለይ ኦፒዲኦ አና ብአዴን ሀሳባቸውን በየጊዜው እየቀያየሩ እንዳስቸገሯቸው ተናግሯል፡፡

በወታደሩ ውስጥ የትግራይ የበላይነት ጉዳይ ያነሳና “ሁሉም አባል ድርጅቶች በእኛ የተቁቁሙ ስለሆነ ጀነራል መሆን አይችሉም ብሏል፡፡

ትግራይ ውስጥ 5 ዩኒቨርሲቲ የሰራነው “ትግራይ ካላት የስትራተጂ ጠቀሜታ አንጻር” ነው ብሏል፡፡ በመንገድ ረገድም ለትግራይ የተሰራው የትጋራይን ኢኮኖሚ ወደ መሀል አገር አንዲዛመድ ለማድረግ ነው ብሏል፡፡

አባይ ጸሀየ ከመጥበቡ የተነሳ ለወታደሩ ማእርግ ትኽሻ ላይ የሚቀመጡ የሹመቶች ጌጦች “በአክሱም አንጥረኞች” ብቻ እንዲሰራ ማድረጉ ይታወሳል፡፡ በኢትዮጵያ ስም የሚንቀሳቀሰው የወያኔ ሰራዊት አልባሳትም ከአድዋ አልሜዳ የአልባሳት ፋብሪካ ብቻ እንዲገዛ ከተወሰነ አመታት አልፈዋል፡፡

በነገራችን ላይ ትግራይ ውስጥ ጥጥ አይመረትም፡፡

ብአዴን እና ኢፒዲኦ የሚባሉ ጉደኞች ከወዲሁ እርሳቸውን ከወያኔ ጥቃት ለመከላከል ቢዘጋጁ ይሻላቸዋል፡፡ ካልሆነ ግን ወያኔ ሊበላቸው እንደተዘጋጀ አባይ ጸሀየ ግልጽ አድርጙል፡፡ እኔ እንኻ አዝኘላችሁ ሳይሆን ግን ፈጣሪያችሁ ወያኔ ሊያጠፋችሁ መወሰኑን እንድታውቁት በሚል ነው፡፡ ከጠፋችሁ ግን ከተዝካራችሁ የሚቆም እንደሌለ ከወዲሁ ይታወቅ !!፡፡

Filed in: Amharic