ፖለቲካ በባህሪው ተለዋዋጭ ነው። የአገራችን  ፖለቲካ እንደዚህ  እንደምንመለከተው እየሆነ ነው ።  ግልብጥብጡ  እየወጣ አሳሪው ታሳሪ እየሆነ ነው።  አንዳርጋቸው እንዲፈታ ተወስኗል ። ነገ ይፈታል ብለን እንጠብቃለን።
አንዲአርጋቸውን በማፈን ሂደት ውስጥ የተሳተፉ አገሮችና ሰዎች ዛሬ  ያኔ እንደነበሩት አይደሉም።
…
1 ~ አንዳርጋቸውን በማፈን  ሴራ ውስጥ  ዋና አገር የነበረችው የመን   በሰማይ በሚወነጨፍ ሚሳዬልና  በሚወረወር ቦምብ  ፈራርሳና ተደረማምሳ  የድንጋይ  ዘመን አገር ሆናለች።
…
2~ አንዳርጋቸውን በማሳፈን  ሴራ ከፍተኛውን ሚና የተጫወተው የየመኑ ፕሬዚደንት የነበረው አሊ አብደላ ሳልህ በሁቲ አማፂያን የራስ ቅሉ በጥይት እንደ ዱባ ተፈልጦ ሲሞት በቴሌቪዥን መስኮት  በአይናችን  በብሌኑ አይተናል።
…
3~ የመን  ሰንአ አለምአቀፍ አውሮፕላን ተርሚናል ውስጥ የታፈነውን  አንዳርጋቸው ፅጌን የራሱን ቻርተር የግል አውሮፕላን ልኮ አስመጥቶ ማእከላዊ እንዲሰቃይ ያደረገው ሼህ መሀመድ አላሙዲን በተራው ሳኡዲ አረቢያ ውስጥ ታስሯል ። ቢዝነሱ እየከሰረ ካምፓኒው እየተዘጋ ከአለም ሀብታሞች ስም ዝርዝር ውስጥ ተፍቋል።
…
4~ አንዳርጋቸውን በማሳፈን ውስጥ ከ20 ሚሊዮን ዶላር በላይና  አዲስ አበባ የሚገኘውን የትምባሆ ፋብሪካ ለየመን ባለሀብቶች በነፃ የሰጠው የደህንነት ምክትል ሃላፊ የነበረው ወልደሙካኤል በሙስና ሰበብ ታስሮ ቃልቲ  ይገኛል።
…
አንዳርጋቸው ፅጌ ዛሬ የኢትዮጵያ ህዝቦች በተለይም የአማራ ፋኖና የኦሮሞ ቄሮዎች ታግለው ባመጡት አጠቃላይ ፖለቲካዊ ትግል ነፃነቱን ሊያገኝ ነው።
” ለክፉና ለአመንዝራ ትውልድ ምልክት አላሳየውም፡፡ እንዲሁ አጠፋዋለሁ!”  እንደሚለው  ፍካሬ – ኢየሱስ ክፉና አመንዝራ የሆኑትና የታሪክ ጎርፍ እያግበሰበሰ ያመጣብን ወያኔዎች  ምልክት ሳያዩ እየጠፉ ነው።
ቦ ጊዜ ለኩሉ  !!
