>
5:14 pm - Wednesday April 30, 0977

"መደመር አይገባኝም...."  በራሱ ደንገር ያደርጋል!!! (መስከረም አበራ)

“መደመር አይገባኝም….”  በራሱ ደንገር ያደርጋል!!!

መስከረም አበራ
* ጓደኛ ከመንገድ ሲቀር ሃሞት ያፈሳል፣ጉልበት ያዝላል…. ልቡ የሻከረ ወዳጅ ደግሞ ማገዙን በማቆም ብቻ ላይወሰን ይችላል፤መሰናክልም ሊያስቀምጥ ይችላል፡፡ ይህን ሁሉ ተቋቁሞ ያሰቡትን ለማሳካት መበርታት አስመስጋኝ ስራ ነው፡፡ በተለይ ጃ-war “ለማ ለማ” ማለት ማብዛቱን ስመለከት “
አቶ ለማ ልዩነት መያዛቸው ተፈጥሯዊ ነው፤ልዩነት እንዳላቸው ወጥተው መናገራቸውም ፖለቲካችን ወደ ዲሞክራሲ የማደግ አንዳንድ ምልክቶች እያሳየ መሆኑን ያመለክታል፡፡ ከሁሉም በላይ የዲሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት ተዝካር መውጣቱን ያመለክታል፡፡በበኩሌ ተመስገን ብያለሁ! ትልቁ ጥያቄየ ግን ኦቦ ለማ በውህደቱ ላይ የማይስማሙ ከሆነ ያች እጅ አወጣጣቸው “ምን የምትሉ እጅ አውጡ” ሲባል የወጣች ትሆን?
በመደመር ላይ ከጅምሩም አልስማማም ነበር ያሉት ነገርም አደናጋሪ ነው፡፡ አብይ ስልጣን ላይ ከወጡ ጀምሮ መደመር ከአፋቸው ተነጥሎ አያውቅም፤ለማ ደሞ ያለ ዛሬ በመደመር ላይ ስምምነት እንደሌላቸው ትንፍስ ብለው አያውቁም፡፡ ዶ/ር አብይ መደመር የሚለውን ሃሳብ መፅሃፍ ለማድረግ ማብሰልሰል ከጀመሩ አስር አመት እንደሆናቸው ክብርት ሙፈሪያት የመፅሃፉ ምርቃት ዕለት ሲናገሩ ሰምቻለሁ፡፡ ለማ ወንበራቸውን ለቀው አብይ ጠ/ሚ እንዲሆኑ መንገድ ሲጠርጉ ይህ መደመር ሃገር መምሪያ እሳቤ እንደሚሆን አብይ ሹክ አላሏቸው ኖሮ ነው?በጣም ጓደኛ እንደሆኑ ነው የሚነገረው …..
ለማንኛውም አቶ ለማ ብዙ የሚያስመሰግን ስራ የሰሩ ሰው ናቸውና ስለሰሩት ማመስገን ግድ ነው፡፡ ህወሃትን ለማስወገድ በተደረገው አደገኛ ትግል፣በወንበሬ ተቀመጥ ብለው በሃገራችን ለውጥ እንዲመጣ ማስቻላቸው፣የኢትዮጵያ መኖር አስፈላጊ እንደሆነ አበክረው መስበካቸው ሊያስመሰግናቸው የሚገባ ነገር ነው፡፡
መደመር አይገባኝም ያሉት ነገር ደንገር እንዳደረገኝ ግን መካድ አልሻም፡፡ውህዱን ፓርቲ እውን ለማድረግ ዶ/ር አብይ በከፍተኛ ፈተና ውስጥ እንደከረሙ የዛሬው የአቶ ለማ ንግግር በደንብ አስረድቶኛል፡፡እስከ ሞት የተማማለ የቅርብ ጓደኛ ያልደገፈው፣ ያላገዘው፣አይዞህ ያላላውን ጉዞ መጓዝ ትልቅ ብርታት ይጠይቃል፡፡ ለዛውም በኦሮሞ ብሄርተኞች ውስጥ ሆኖ ይህ ከባድ ነው! ጓደኛ ከመንገድ ሲቀር ሃሞት ያፈሳል፣ጉልበት ያዝላል…. ልቡ የሻከረ ወዳጅ ደግሞ ማገዙን በማቆም ብቻ ላይወሰን ይችላል፤መሰናክልም ሊያስቀምጥ ይችላል፡፡ ይህን ሁሉ ተቋቁሞ ያሰቡትን ለማሳካት መበርታት አስመስጋኝ ስራ ነው፡፡ በተለይ ጃ-war “ለማ ለማ” ማለት ማብዛቱን ስመለከት “ብራቮ አብይ” ብያለሁ…..!!!!!!!
Filed in: Amharic