ንባብ ቤት፤ሀ ለ ሐ መ ሰ–እያሉ የፊደል ዘሮችን የመለየትና መልእክተ ዮሐንስን ፤መዝሙረ ዳዊትንና ሌሎችን– የመማርና የማወቅ ሒደት ነው፡፡ይኽም እንደ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሊታይ ይችላል፡፡(The School of Reading (ንባብ፡:ቤት “nəbab bet”) can be seen as an elementary school). ዜማ ቤት፣ማለት የቃል ትምህርት ሲሆን ትምህርቱን ለምሳሌም ውዳሴ ማርያምን– በሦስት ዓይነት ዜማ ( በግእዝ፤ እዝል፤አራራይ) እያዜሙ መንፈሳዊ መዝሙሮችን የሚማሩበትና ምልጣንም የሚያመለጥኑበት የትምህርት ክፍል ነው፡፡ ይኽም እንደ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ይታያል፡፡ (The School of Zema (ዜማ ቤት “Zema bet”) is regarded as the education of spiritual relics or as a school of Sacred songs. Zema bet is the equvalent of the modern school system’s junior and senior high school). ቅኔ ቤት.ማለት የግእዝ ንባብ የሚተረጎምበትና ሰዋስው ወይም ግስ የሚታወቅበት ሰምና ወርቁን እያስተባበሩ ፤ ቤት እየመቱ ቅኔ የሚቆጠርበትና የሚዘረፍበት የቤተ ግጥም ቦታ ነው፡፡ ይኽም በኮሌጅ ደረጃ ሊታይ ይችላል፡፡(The School of Qǝne (ቅኔ ቤት “Qǝne bet”) is a school of poetry where the Qǝne teaching and learning process is going on. It is the equivalent of a college education).
መጽሐፍ ቤት፤ መጽሐፈ ብሉይ፤ሐዲስ፤ሊቃውንትና መጽሐፈ መነኮሳት የሚተነተኑበትና የሚተረጎሙበት ክፍል ነው፡፡ይኽም ከዩኒቨርሲቲ ደረጃ ጋር የሚመዛዘን ነው(The School of Commentary (መጽሐፍ ቤት “Mӓśḥaf bet”) has the status of a univesity, where different manuscripts are prepared, studied and interpreted in the form of commentary ). እናም ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሤን ፊደል ያስቆጠሯቸው መምህራቸውመሪጌታ አደላ ንጉሤ ይባላሉ፡፡እርሳቸውም የደብረ ገነት ደብረ ኤልያስ ቤተ ክርስቲያን የዜማ መምህር ነበሩ፡፡ዮፍታሔ ፊደል ቆጥረው፤ ዳዊት ደግመው፤ ንባብ ተምረው ጥሩ አንባቢ ከሆኑ በኋላ ጸዋትወ ዜማ ተማሩ፡፡ ጾመ ድጓና ምዕራፍ ከተማሩ በኋላ ወደ መምህር ገብረ ሥላሴ ቅኔ ቤት ገቡ፡፡ ብሩሕ አእምሮና ፈጣን ተዘክሮ ስለነበራቸው በ13 ዓመታቸው የቅኔ ዘራፊ ኾኑ፡፡መምህር ገብረ ሥላሴም ተቀመጥ በወንበሬ፤ ተናገር በከንፈሬ ብለው መርቀዋቸዋል፡፡በኋላም ድጓ ተምረውና የዜማ ትምህርታቸውን በደንብ አለዝበውና በመምህር ገብረ ሥላሴም በቅኔ ተመርቀው በልጅነታቸው መሪጌታ ኾነዋል፡፡