>

ስንክሳሯ ተነብቦ የማያልቀው ኢትጵዮያ እንዲህ ናት ... (ከዳንኤል ቶማስ)

ስንክሳሯ ተነብቦ የማያልቀው ኢትጵዮያ እንዲህ ናት …

ዳንኤል ቶማስ


ተላልፋ ከተሰጠች ሁለት ዓመት የሞላትና ሙሉ በሙሉ በአሜሪካና በሌሎች ሃያል አገራት ባለቤትነት የምትመራውን, የኢትዮጵያውያን ያልሆነችውን, አዲሲቱዋን ኢትዮጵያ በሞግዚትነት እየመራ ያለው አብይ አህመድና ሌሎች መሰል አጋሮቹ(የሲ አይ ኤ እና የሃያላኑ ምልምል ባለስልጣናት) ለዚህ ህዝብ አዳዲስ እለታዊ አጀንዳዎችን እየሰጡ እሱኑ በማራገብ ተጠምደን እንድንቀጥል የማድረግ ተግባራቸውን ቀጥለዋል!እኛ የእነሱን አጀንዳ ተቀብለን ስናራግብ እነሱ ግን ከመጋረጃው ጀርባ የሃያላኑን ስውር ደባ ከአለቆቻቸው በሚወርድላቸው እለታዊ,ሳምንትዊ,ወርህዊና ዓመታዊ ትእዛዛት መሰረት ተግባራቸውን መፈጸማቸውን ቀጥለዋል::የታጩትም ለዚህ ነውና እሱኑ ብቻ ይፈጽማሉ::ሌላ አገራዊና አገር በቀል ስራ ለአገርና ለህዝብ የሚጠቅም ስራ ከአዲሱ መንግስት የምትጠብቅ ህዝብ ሆይ!የዋህነትህና ጅላጅልነትህ ገደብ ቢኖረው መልካም ነበር!አለመታደል ሆኖ ግን ድንዛዜው እንደቀጠለ ነው!

በማስ የተወጋነው የድንዛዜ መርፌ የቆየባቸውና አሁን ድረስ ያልለቀቃቸው ብዙ ሚሊዮን ዜጎች እንዳሉ ሁሉ: ከማደንዘዣው መርፌ ቀድመው የነቁም, ጭራሽ ማደንዘዣው ያልሰራባቸውም ሚሊዮን ዜግች አሉ! በዚህ ገጽ የሚቀርቡ ጽሁፎች የማደንዘዣው መርፌ ያልሰራባቸውና ለጊዜው ሰርቶ ነገር ግን በሳምንትም በወርም ከድንዛዜው መንቃት የቻሉ ዜጎችን ብቻ የሚመለከት እውነት ነው!

የማደንዘዣ መርፌው ለሳምንት ያህል ከሰራባችው ዜጎች ውስጥ አንዱ እኔ ነበርኩ::ነገር ግን የድፍን አገሪቱን ድጋፍና የመላውን ዜጋ ፍቅርና ይሁንታ ሲያገኝ የተሰጠውን ተልእኮ ክዶ ከህዝቡና ከአገሪቱ ጎን ይቆማል ብየ በማሰብ ነበር!ከህዝቡና ከአገሩ ጎን በመቆም ተልእኮ ሰጥተው ስልጣን ያስያዙትን አካላት ክዶ አገሩን በሃቅ መምራት ይቀጥላል ብየ ገምቸ ስለነበር ነው!እርሱ ግን አላደረገውም!

ከትግራይ እስከ አማራ ከኦሮሚያ እስከ ደቡብ ከአፋር እስከ ሶማሌ ከቤንሻንጉል እስከ ጋምቤላ አልፎም እስከ ኤርትራ ሁሉም ህዝብ በአንድ ድምጽ ሲደግፍህና መላው ህዝብ,መላው ፓርቲ,ፍቅሩን ሲያሳይህ አንተ ብቻ ምራን ሲልህ,እንዴት ባእዳን የሆኑትን የሲ አይ ኤን እና የሃያል አገራት መንግስታትን ተልእኮ ወደ ጎን አድርገህ ከዚህ ካልጠበከው 100% ድጋፍ ከሰጠህ ከራስህ አስደሳች ህዝብ ጋር አትቆምም?እንዴት “እነሱ የራሳቸው ጉዳይ!አገሬ ትሻለኛለች!”ብለህ አትክድም? 100% ድጋፍ!?
ኢየሱስ ክርስቶስ ምድር ላይ በነበረ ጊዜ ስለ ፍቅር እየሰበከ እንኩዋን ተቃዋሚ ነበረው::ነብዩ መሃመድ ተቃዋሚ ነበራቸው::ሁሉም ተቃዋሚ ነበራቸው::ሁሉም ዓለማዊ መሪም ተቃዋሚ ነበረው::አብይ ግን የስልጣኑ ሰሞን ተቃዋሚ ነበረው ሊባል በማይችል መልኩ 100% ሊባል የሚችል ድጋፍ ነበር ያገኘው::በዚህም የመጀመሪያው ተቃዋሚ አልባ መሪ ሊባል ይችል ነበር!በቃሉ ቢቀጥል ደግሞ ብቸኛው ተወዳጅ መሪ ሊባል ይችል ነበር!

ያን ሊያደርግ እንደሚችል ተስፋ ጥየ ነበር!ምክንያቱም ይህን የህዝብ ተልእኮ እንዴት ከእነሱ ትልእኮ አስበልጦ ያየዋል ተብሎ ይገመታል? አይገመትም!
አንድ እምነት የተጣለበት ሃያል ሰላይ እኮ ለስለላ ትልኮ ሄዶ ድንገት በሴት ፍቅር ተነድፎ ፍቅሩን ሲያስቀድምና ተልእኮውን ወደ ጎን ሲል ማየት የተለመደ ነው!ጭራሽ የህዝብና የገዛ አገርህ ፍቅር ሲሆንስ?ሺ ተልእኮን አያስተውም?!በዚያ ሁኔታ ሆኖ ይህን ህዝብ መካድ ነበረበት? ይህን ማን ሊገምት ይችላል? ለስልጣን ከሆነ ግዛን ተብሎዋል!ለዝና ከሆነ መሪነት በቂ ዝና ነው!ለገንዘብ ከሆነ እንደማንኛውም የአፍሪካ ሌባ መሪ ሁሉ በእጁ ነው!ታዲያ እነሱ ሌላ ምን ሊሰጡት ይችላሉ?ቅድሚያ ለእንሱ ተልእኮ የሰጠው ለምን ሊሆን ይችላል? የዚህን ጥያቄ “ግላዊ” ምላሽ ከዓመት በፊት በዚሁ ገጽ ለጥፌላችሁ ነበር!

ስለዚህ ተልእኮውን ወደ ጎን አድርጎ 100% ፍቅርና ድጋፍ ለሰጠው ለዚህ ህዝብና ለገዛ አገሩ ፍቅር ይረታል ብየ ተስፋ አድርጌ ነበር!ለዚያ ነው ለአንድ ሳምንት ማደንዘዣው ይስራብኝ ብየ ፈቅጀ ደንዝዠለት የነበረው::

እነሆ ዛሬ በሞግዚትነት አገሪቱን ሲመራ ሁለት ዓመት ሞላው!በ2 ዓመት ውስጥም በሃያ ዓመት ተሰርቶ የማያልቀውን ብዙውን ስራ ሰራላቸው!በየእለቱ ለዚህ ምስኩን ህዝብ ጥቃቅን አጀንዳ እየሰጠ እርሱና ግብርአበሮቹ ለእነሱ ሲሰሩ 25ኛ ወራታቸውን ያዙ::

በአህኑ ወቅት የሚያሳዝነው የእርሱ ሴራ ሳይሆን የደንዛዦች አለመንቃት ሆኖ ተገኘ!2 ዓመት ሙሉ የማደንዘዣ መርፌው ያልለቀቃቸው በርካታ ዜጎች!
እስቲ ተመልከቱ! በአብይ ዘመን የርኩሰት ሰንደቅ ዓላማቸው በይፋ በየኤምባሲያቸው እንዲውለበለብ ተደርጎዋል! ይህ የርኩሰት ተግባር በስልጣኑ ማግስት ነው የተፈቀደላቸው! ተመልከቱ!በኢትዮጵያ ምድር እየመጡ ህዝብና ባለስልጣናት ካህናት ሳይቀሩ የሰገዱላቸውን ግብረሰዶማዊ መሪዎች!

ጭራሽ የመስቀል ፍላወሩ አደባባይ በ LGBT (lesbian gay by sexual transgender) ህግ ጾታውን ከወንድ ወደ ሴት ያስቀየረውን አሜሪካዊውን የዲሲ ከንቲባ ሃውልት!በዋና ከተማችን ላይ ለዚህ በቀዶ ጥቀና ጾታውን ለለወጠና ከወንድ ወደ ሴት ለተቀየረ የሰው ዝቃጭ Mayor Muriel Bowser street!ተብሎ የተሰየመለትን!በስሙ የተተከለለትን የባእድ አምልኮፒራሚድ! እስቲ ተመልከቱ ስልጣናቸውን ተገን አድርገው የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻን ህግ ያስጸደቁና ያጸደቁ ርከሶች በኢትዮጵያ ምድር እንዴት እንደነገሱ!እነዚህ በህጉ መጽደቅ ምክንያት ተደስትው በአደባባይ የደስታ እንባቸውን ያፈሰሱ እርጉማን በዚች ቅድስትና ምስኪን አገር እንዴት ክብር እንደተሰጣቸው?!እና የአብይ መንግስት የኢትዮጵያ መንግስት ነውን?የኢትዮጵያ ህዝብስ በዚህ ተግባር የሚፈነድቅ ህዝብ ነውን?ምን ስለሰሩ?ለኢትዮጵያ ምን ውለታ ስለፈጸሙ ይህ ሃውልት ይቆምላቸዋል?
አዎን!ወደፊት መላውን ህዝብ እንደ ፈቃዳቸው ያደርጉት ዘንድ መሉ ፈቃድ የተሰጣቸው ናቸው!የአዲሱ መንግስታችሁ የጎን ለጎን ስራም እነሱን የሚቃወሙትን ከአገሪቱ ማጥፋት ነው!ዋና ተልእኮውም ትውልዱን ለእነሱ ዓላማ የማዘጋጀት ተግባር ነው!የኖቬሉም የድጋፉም ሚስጥር ይህንና ይህን መሰል ተልእኮ በአግባቡ የመወጣት ጉዳይ ብቻ ነው! ሽልማቱን ያበረከተችው አሮጊት ሴትዮ እንኩዋን የዓለማችን ታዋቂ ሌዝቢያን ናት!

ስለዚህ በቤተመንግስቱ ሚስጥራዊ እድሳትና ላይ በላይ ማንም እንዲያየው ስለተደረገው በፒኮክ ምስልና ዓርማ አትገረሙ!ከቤተመንግስት አልፎ በቅዱስ ቤተመቅደሶች ካባ ለብሰው በሃይማኖታዊ ስርዓት አጀብ ታጅበው እንዴት እንደነገሱ ተመልከቱ!!

የኖቬል ፒስ ፕራይዝ ሜዳሊያ(Nobel peace prize medal) በዚህ ዘመን ለማንና ለምን እንደሚሰጥ የታወቀ ነው!

እንዴትና ለምን እንደሚሰጥ ለማወቅ የሽልማት ሜዳሊያው ላይ በግልጽ ሰፍሮዋል!ያንን ዓርማ ማየት ያስፈልጋል!ከስር እዩት!እርቃን ወንድና ወንድ ሲዳራ ታያላችሁ!የ “ሰላም” ሽልማቱ ይህን የሚያሳይ ሜዳሊያ ነው!ሸላሚዎቹ ሰላም የሚሉት ይህንን ነው! ይሄው ነው!ኢትዮጵያን እንደልባቸው እንዲዘውሩዋት የተፈቀደላቸው እነዚህ ናቸው!ዘላለማዊ ሃውልት በዋና ከተማዋ የሚቆምላቸው!በስማቸው አደባባይ የተሰየመላቸው!ለትንንሽ ገንዘብ ሲባል የሚሰገድላቸው!አገሪቱ ላይ በየዘርፉ እንዲነግሱ የተፈቀደላቸው!
በዚህ ገጽ የስድብ ኮሜንት የሚለጥፉትን የእኛዎቹን ተለካፊዎች ልብ ብላችሁ ስታዩ ደግሞ እነዚህ እርጉማን ምን ያህል ስር እየሰደዱ እንዳሉ ይገባቹሃል!!!እንደ ሰው ልብስ ለብሰው በከተማ የሚዘዋወሩ ነገር ግን የመጸዳጃ አካላቸውን ለወሲባዊ እርካታ ጥቅም ላይ ያዋሉ በቁማቸው የበሰበሱ መክረህ የማትመልሳቸው እሳት ቢዘንብባቸው ከቆሻሻ ተግባራቸው የማይመለሱ የሰው ዝቃጮች ርካሽና እርኩሶች ናቸው!!!ይህም በምእራባውያን ፍላጎት እየሆነ ያለ ነው!!!

••••••••

…..እንደተባለው አዲሱ መንግስት በየእለቱ ለህዝቡ አንድ አንድ የሽፋን አጀንዳ የመስጠት ተግባሩንና ከመጋረጃው ጀርባ የሚፈጽመውን አደገኛ ሴራ እንደቀጠለ ነው:: ዛሬም እንደልማዱ “እንቆቅልህ” ብሎ “ምን አውቅልህ” ሲባል “የፒኮክና የአንበሳ….” እያለ ጠይቆ ማጠያየቅን የእለቱ አጀንዳ ብሎ ለእኛ ሰጥቶዋል::

እኛ የእሱን የፒኮክ እንቆቅልሽ መልስ እንድናፈላልግ አድርጎ እርሱ ሌላ ዓላማውን ሰሞነኛውን የኢትዮጵያ ምግቦች እንዲመረዙ የፈቀደውን ፈቃድ ማረሳሳትም ይሆናል!ብቻ ግን ሌላ ሴራውን እየከወነ እንዳለ ግልጽ ነው!

ፒኮክ ብቻ አይደለም!የቤተመንግስቱ እድሳት ለምን እንዳስፈለገ ከዚህ ቀደም በሰፊው ዳሰሳ አድርገን ብዙ የስድብ ኮመንቶች አስተናግደናል::እርሱ የያዘው ዓላማ ግልጽ ነው!አገሪቱን ከእነ ቤተመንግስቱዋ ለእነሱ እያሸበረቀ እንጂ ለቀጣዩ የኢትዮጵያ መንግስት አስቦ አይደለም ያደሰው!ፒኮክን እንደ ቀልድ የጌጥ ታፔላ የለጠፈበትን ምክንያትም አያውቀው ይሆናል::አለቆቹ ግን ተራ ታፔላ እንዳልሆነ አሳምረው ያውቃሉ!

እርሱ የታዘዘውን ይፈጽማል!ሳጥናኤልንና ጭፍሮቹን ለማንገስ ስራውን ቀጥሎዋል! ቀስ እያለ ይገባሃል ወገኔ!ስንት መሰራት ያለበት አንገብጋቢ ጉዳይ እያለ እሱን ትቶ በብዙ ሚሊዮን ዶላር ቤተመንግስቱን ወደማደስ የታለፈበት ሚስጥር ሲገባህ በቤተመንግስቱ ስር ስለተገነባውና በውስጡ ስላለው ሚስጥርም አብረህ ትረዳለህ!ጠብቅ ትደርስበታለህ!የአብይ አህመድን ዓለም አቀፍ መሰሪ ተልእኮ እስክትረዳ ብዙ ማገዶ ትፈጃለህ እንጅ ማወቅህ አይቀርም አልኩህ እኮ!የዛሬ አደንዛዥ ፈገግታው ተለውጦ አስፈሪ አውሬነቱ እስኪገለጥልህና ደንግጠህ ዓይንህን እስክታፈጥ ግን በድጋፍ ትንጫጫለህ!ይህ እስኪሆን ምን ያህል ማገዶ ትፈጁ ይሆን?i don’t know how long will it take!
እርሱ ስልጣን የያዘው ኢትዮጵያን ሊመራ አይደለም! እርሱ የኢትዮጵያ መሪ አይደለም!

በአንድ በአንድ ኢሜል ስልጣኑን እንዲለቁና ለእርሱ እንዲያስረክቡ የተነገራቸው,ይህን ማድረግ ለእነሱ ምንም ችግር እንደሌለውና ኢህአዴግ የተባለው ፓርቲ እንደማይፈርስ የተገለጸላቸው,ታሪካችሁም ሆነ የፓርቲያችሁ ስም እንዳይበላሽ ለጊዜው ከህዝብ ተቃውሞ ገለል ብላችሁ ቆዩ ተብሎ የተነገራቸው,እነሱም ሲ አይ ኤ ን አምነው “እሽ እሽ” ብለው ስልጣኑን ለአብይ ያስረከቡት የህወሃት ባለስልጣናት እንኩዋን ነገሩ የገባቸው ቆይቶ ነው!በማፍያ ቁማር እንደተበሉ የተረዱት ዘግይተው ነው!አጅሬ ደግሞ ወደ ቀጣዩ ተልኮው ተሸጋግሮ “አሁን ጊዜው ደርሶዋልና እነሱንም ፈንግል,እነ እገሌንም እንዲህ አርግ…”በሚለው ትእዛዝ ይመራል!እየተመራም ያሉትን ፈጽሞዋል መፈጸሙንም ይቀጥላል!
አብይ አህመድም ሆነ በዙሪያው ያሉ ባለስልጣናት ስልጣን ያስያዛቸውን አካላት ብቻ ለማገልገል ቃል የገቡ ስብስቦች እንጂ የኢትዮጵያ ህዝብ መሪዎች አይደሉም! የሚለውን እውነት ጨልፌ ለጠፍኩልህ!ስለዚህ እውነቱን ተቀበል!ወይም መቀበል ጀምር!

የአብይ መንግስት የሚሰራው ለእነርሱ እና ለእነርሱ ብቻ ነው!እለታዊ ተግባሩም በየቀኑ በሚደርሰው ትእዛዝ ይፈጽማል እንጂ የዓላማው መዳረሻ አልተነገረውም!ሁሉም ሚስጥር ከስር ላለ አሽከር አይነገርም!ተልእኮህ የሚነገርህ እንደየ ደረጃህ ነው!እንደየ እርከንህ ነው!ጄኔራል የሚያውቀውን ተልእኮ እስር አለቃ አያውቀውም!አብይና ባለስልጣናቱም ከአለቆቻቸው ከሃያላኑ እንጻር ዝቅተኛ እርከን ላይ ያሉ አሽከሮች ናቸውና እንደ ትልእኮ ፈጻሚ ታማኝ ወታደር በ አድርግ አታድርግ ህግ ይመራሉ!ተልእኮውም በየእለቱ የሚወርድ እንጂ ሚስጥሩ ሁሉ ባንድ ጊዜ ተነግሮዋችው የተልእኮውን የመጨረሻ መዳረሻም አውቀውት የሚቀጥሉ አይደሉም! ስለዚህ እኛም ብቻ ሳንሆን እነሱም ድንዛዜ ውስጥ ናቸው ለማለት ነው!አውቀው ደንዝዘው ግን አይደለም!

ስለዚህ አንበሳን በፒኮክ የለወጡበትን ሚስጥር እንኩዋን ቢጠየቁ አይመልሱም!መልሱን ላያውቁት ይችላሉ!በዝቅተኛ እርከን ላይ ያለ ካድሬ ከአለቆቹ የተነገረውንና በአለቆቹ የተሞላውን ነገር ማፍሰስ እንጂ የተሞላውን አፍስሶ ሲጨርስ የሚናገረውም የሚመልሰውም መልስ አይኖረውም::ምናልባት “ቆይ ጠይቄ ልምጣ ሊልህ ይችላል”ወይም “እኔ እንጃ እንደዛ አድርጉ ስላሉን ነው” ይልሃል!አያውቁትማ! ስለዚህ እንደፈረደብን የፒኮክንም የአንበሳንም ሚስጥር አብራርተን እንነግራቸዋለን!ዘርዓይ ደረስ ያገሩ ሰንደቅ ዓላማ ጭቃ ላይ ውድቆ የሮም ህዝብ እየጨፈረ ሲረጋግጠው ያያል!በዚያ ላይ የወቅቱ የኢትዮጵያ ዓርማ የነበረውን አንበሳ የኢጣሊያ ዓርማ የሆነችው ድኩላ ስትጋልበው ያያል!ጣሊያኖች ይህን ያደረጉት የሞሶሎኒ ጦር ኢትዮጵያውያንን አሸንፎ አገሪቱን በቁጥጥር ስር ማዋሉ ይፋ ስለተደረገ ነው!በደስታ እየጨፈሩ መሆኑ ነው!ዘርዓይ ድረስ የወደቀውን ሰንደቅ ዓላማ አንስቶ ከእነ ጭቃው ሳመ!”አንተ ባንዲራ እንዲህ ተዋርደህማ አትቀርም!”ብሎ ከህዝብ መሃል ገብቶ አንስቶ ያዘ::በጣሊያኖች ዓርማ በድኩላ የሚጋለበውን የኢትዮጵያ የአንበሳ ህውልት አይቶ አዘነ!ድኩላዋን ከአንበሳው ጫንቃ አውርዶ ጣለ!ስሜቱን መቆጣጠር ተሳነው!እያለቀሰ ሰንደቅ ዓላማውንም ከኢትዮጵያ የተወሰደውን የአንበሳ ሃውልትም ከነጣቂዎች እየተከላከለ ታጥቆት የነበረውን ጎራዴ መዘዘ!በጋራ ተሰብስቦ ይጨፍር የነበረውን በሺ የሚቆጠር ህዝብ በስሜት ከታትፎ ከታትፎ ጣለ!ብዙዎችን ገደለ!በመጨረሻ ግን በጥይት መትተው ገደሉት!”ሮምን ሲንጣት የዋለው ኢትዮጵያዊ ጀግና”ሲል bbc ዘገበ::ያን ጊዜ የኢጣሊያ ህዝብ ብዛት 40 ሚሊዮን ነበርና
“አንድ ዘርዓይ ደረስ ለ 40 ሚሊዮን ህዝብ” ተብሎ በእነ ቢቢሲ ተዘገበለት!የአገሩ አንበሳ በጠላት ድኩላ ሲጋለብ አይቶ ፈጅቶዋቸው ሞተ!ዛሬ በፒኮክ አማልክት የሚጋለብ አንበሳ ባይኖርም….ታሪኩን ላስታውሳችሁ በሚል ነው!በነገራችን ላይ ያ ዘርዓይ ደረስ የሞተለት የአንበሳ ሃውልት የተወሰደው ከአዲስ አበባ ነበርና ከነጻነት በሁዋላ ወደ አገሩ ተመልሶ ለገሃር ባቡር ጣቢያ በር ላይ ይገኝ ነበር::አብይ ስልጣን እስኪይዝ ድረስ::አሁን ለገሃሩም ባቡር ጣቢያውም አንበሳውም ለኢምሬትስ ነገስታት በይፋ ተሸጦዋል!!!ታሪክን የሁዋሊት ይሉሃል!

እና…ተራ ታፔላ ስለመሰለው ስለ ፒኮክም ከ “ምን ችግር አለው ጌጥ ነው,ወፍ ነው,ፒኮክ ተወዳጅ ወፍ ናት,” ባዮች በላይ ከሰቃዮቹ በላይ የዓርማውን ሚስጥር የምስሉን ትርጉም የአስፈላጊነቱን ጥግ የምክንያቱን መነሾ የአሰቃዮችን ማንነት የሚያውቅ ከፒኮክ ጀርባ ምን እንዳለ የሚገነዘብ ብዙ ህዝብ እንዳለ ይወቁት ለማለት ነው!ያልበላህን የምታክ መስለህ ለህዝቡ የለመድከውን እለታዊ አጀንዳ እየሰጠህ አታምታታ ለማለት ነው!

ሚሊዮን ተከታይ ባላቸው ባንተበተገዙት ገጾችና ግሩፓች የህንድ Royal family ዓርማ ምናምን እያሉ የሚደባብቁልህንና የሚያሳምኑልህን ብቻ ሳይሆን ምንም ተከታይ የሌላቸውን ገጾች የሚከተሉ ስለ ፒኮክ በርድ ትክክለኛ ትርጉም የሚያውቁ በህንድ ሮያል ዓርማ ብቻ ሳይሆን  በ አውስትራሊያ Devil birds,በሜዲትራንያን አዋሳኝ አገሮች The Messenger of Satan,  The end of the Father, the survivor of the Devil, the evil eye of the female demon, በወዘተ ትርጉሙዋ የሚያውቁ አንተና እናንተ የማታውቁዋቸው እነሱ ግን የሚያውቁዋችሁ ሚሊዮን አዋቂዎች አሉ! ምድረ መሰሪ! ጭፍን ደጋፊና ሆይ ሆይ ባይ ህዝብ ብቻ ሳይሆን እንዲህና እንዲያ የሚያስብ ማን በማን እንደሚታዘዝ የሚረዳ ብዙ ዜጋ እንዳለም ያውቁት ዘንድ ደርሶዋችውም ያነቡት ዘንድ ሼር በማድረግ ተባበሩ::

Filed in: Amharic