ጋይስ….. አገራችን እንዳትፈርስ…!!! (አሳዬ ደርቤ) September 2, 2020 ጋይስ….. አገራችን እንዳትፈርስ…!!! አሳዬ ደርቤ ከንቲባው ዘርፎ አይከሰስ- ሽመልስ ዘልፎ አይወቀስ ድሆች በቆጠቡት ብር- የካድሬ ጎጆ ይቀለስ ታከለ ወረደ ስንል- ታከለች በቦታው ትንገስ ሸገር ቤቷን ተነጥቃ- በሰላም ዳቦዋን ትጉረስ . ጋይስ…. አገራችን እንዳትፈርስ ለትምህርት የሄዱ ሴቶች- ጫካ ውስጥ ቀልጠው ይቅሩ የዘር ጭፍጨፋ ፈጽመው- ‹‹ግጭት›› በማለት ይጥሩ ኀዘን፣ ንዴታቸውን- አንገት በማረድ ይግለጹ ቤታችንን በማቃጠል- ንብረት በማውደም ይመጹ . ጋይስ…. አገራችን እንዳትፈርስ የመኮነን ሐውልት ይንኮት- እንዳሻቸው ያፈናቅሉ ኦሮሞ በያዘው ወንበር- አማራን ዳውን ይበሉ መሬቱንም ሰማዩንም- በጎጥ ቀላድ ይካፈሉ ጃዋር የታሰረ እለት- አጃቢው ሆነን እንታሰር ፖሊስ የከበበው ቀን- ሟቾች ሆነን እንቀበር የነፍጠኛውን ሥርዓት እናውግዝ- የገዳ ሥርዓት እንማር ልማት ይጥፋ- ምርጫው ይቅር . ጋይስ- አገራችን እንዳትፈርስ ሲመቷችሁ አታልቅሱ- ሲቀሟችሁ አትክሰሱ ዝም ብላችሁ ቀበሮ ጋር- ከዐቢይ ፓርክ ተናፈሱ፡፡