>
5:14 pm - Wednesday April 30, 4955

"ኦሮሙማ ክርስቲያኒቲ አይደለም፤ ኦሮሙማ ኢስላማይዜሽንም አይደለም፤ ኦሮሙማ ወራሪነት ነው!!!" አንጋፋው ጋዜጠኛ ዜናነህ መኮንን 

 
 
“ኦሮሙማ ክርስቲያኒቲ አይደለም፤ ኦሮሙማ ኢስላማይዜሽንም አይደለም፤ ኦሮሙማ ወራሪነት ነው!!!”
አንጋፋው ጋዜጠኛ ዜናነህ መኮንን 
በጋዜጠኛ ዳንኤል ገዛኸኝ

     ጋዜጠኛ ዜናነህ መኮንን በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ የሚያጠነጥን ዘለግ ያለ ቃለ-ምልልስ አካሂዶዋል። ጥልቅ ትንታኔም አድርጎዋል።  እንደሚታወቀው ጋዜጠኛው በመካከለኛው ምስራቅ ጂኦ ፓለቲካዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ ፣ ባህላዊና አጠቃላይ ቀውስ እና ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያቀርባቸው በነበሩ ዘጋቢ ትንታኔዎቹ የዶቸ ቪሌ ስራዎቹ እናውቀዋለን፣ ፕሮግራሞቹም ግንዛቤ አስጨባጭ ነበሩ።
ጋዜጠኛው ከሬድዮው አዘጋጅ ለቀረበለት የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ በተለይም ሀገሪቱ እንደ ሶሪያ የመሆን እድል እንዳላት የሚያመላክት ሁኔታ አላት…ለሚለው ጥያቄ ጋዜጠኛ ዜናነህ በሳል ግንዛቤ ሰጭ ማብራሪያ የሚሆን ምላሽ ሲሰጥ የናዚ ጀርመን አይሁዶችን ሆለኮስት የታሪክ ዳራ በማስታወስ የግል ተሞክሮውን በማንሳት ላለፉት ሀያ አምስት አመታት ሀገሪቱ ላይ የዚህ አይነት ሁኔታ ሊከሰት እንደሚችል በዩቱብ ሳይቀር መወትወቱን በቁጭት አውስቶዋል። ጋዜጠኛው በመሻገር የአፓርታይድ /የዘር ልዩነት/ ስሜቶች በሀገሪቱ መታየት ሲጀምሩ  ከጅማሬው እንደተነተነ እና የጎሳ ፓለቲካ ሂደቶች በይበልጥም የአንቀጽ 39 ለዛሬው ላለንበት እውነታ እርሾ መሆኑንም አስረድቷል። ይሁን እና ዜናነህ መለስ በማለት ከሶስት አመት በፊት ለውጥ መምጣቱን እንደ መልካም አጋጣሚ መቆጠሩን አስታውሶ በሌላ በኩል የአጣዬን እና የወለጋውን ክስተቶች፣ ብሄርን መሰረት ያደረጉ ግጭቶችን እና ጭፍጨፋን  ስንመመልከት በእርግጥም ሀገሪቱ እንደ ሶርያ  የመሆን ሁኔታ እንዳለ ፍርሀቱን ያነሳል።  ወደ ባቢሎን የመግባት  ነገር ግን ዜናነህ ተስፋ ማድረጉን አልሸሸገም ችግሮቹ በመንግስት መዋቅር ውስጥ እስካሉ ድረስ ችግሩን ለማረም ደግሞ አልረፈደም መንግስት እድል አለው ችግሩን ለመፍታት ይችላል ።የሚነሱ የእኩልነት የኢኮኖሚ የሀብት ክፍፍል በቋንቋ የመገልገል የመብት ጥያቄዎች ፍትሀዊም ሎጂክም መሆናቸውን የሚያረጋግጠው ዜና ነህ  በኢትዬጵያ አደጋ መኖሩን ያስረዳል።
በሌላ በኩል በኢትዮጵያ አሁናዊ ሁኔታ በተለይ በኦሮሚያ እና ተጎራባች ክልሎች የሚካሄደውን እና ከድርጊቱ እንጻር የጀርመንን የአይሁዶች ፍጅት እንዲሁም የሩዋንዳውን እልቂት በማስታወስ በነዚህ ግዙፍ እልቂቶች ባለ መማር ብቻም አይደለም ከውጤቶቻቸው አንጻር በኢትዮጲያስ ገዥ መሆን ይቻላል ? አሸናፊ ሆኖ መውጣትስ ይቻላል ወይ ? ለዚህ ሀሳብ የጋዜጠኛ ዜናነህ ትንታኔ ጥልቅ እና ግንዛቤ ሰጭ ነው።
በኢትዮጵያ ስላለው የኦሮሙማ አይዲዮሎጂ ስጋት ሲያስረዳ “ኦሮሙማ ክርስቲያናኒቲ አይደለም ኦሮሙማ ኢስላማይዜሽንም አይደለም ኦሮሙማ ማርኪሲስት ሌኒኒዝምም አይደለም። ኦሮሙማ የሚታወቅ ርዕዮት አለምም አይደለም ኦሮሙማ ወረራ ነው “
አካባቢን እንደ ቡድን መውረር ብቻ አይደለም ቅኝ ገዥዎችም መሄድ የሚችሉት እስከተወሰነ ጋት  ድረስ መሆኑን ነው  የምንገነዘበው።  የኢትዬጵያ ወቅታዊ የፓለቲካ ተግዳሮት፣ የንጹሀን ዜጎችን እልቂት እና መፈናቀል ምንጭ የሆነውን ቡድን የሚተቸው አንጋፋው ጋዜጠኛ ደግሞ ደጋግሞ ችግሮችን  ለመፍታት መንግስት እድል እንዳለው ያስታውሳል። በተቃራኒው ለኢትዮጵያ ዲሞክራሲ የሚታገሉ ጠንካራ የፓለቲካ ድርጅቶች አለመኖራቸው የሀገሪቱን ችግሮች ፈርጀብዙ እንዳደረገው በቁጭት ይናገራል። የህዝብን ጥያቄ ላለመመለስ ጥቂቶችን በማሰር መፍትሄ ማምጣት አይቻልም የሚለው ዜናነህ ይልቅም እንድሚታየው እየተጠቁ ያሉ ህዝቦች ራሳቸውን ከመከላከል ይልቅ መዘናጋት ይታያል እንደ አማራ ያለው ህዝብ መደራጀት እንደሚገባው ቀደም ብዬ በሰባዎቹ ስናገር ነበር ይላል ።
    ዜናነህ ሻገር ብሎም ይመለከታል የፓለቲካ አይዲዮሎጂያችን ችግር አለበት ግብጽ ውሀ ነው የጠየቀችው። ሱዳን ግን የአባይ ግድብ የተሰራበትን መሬት እየጠየቀች ነው ሀገሪቱ የኢኮኖሚ ልዩ ልዩ ችግር አለባት ነገርግን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አንድነት መፍጠር አለባቸው የህዝብ አንድነት ከሌለ ደግሞ ልማቱም ሆነ ማንኛውም ጉዳይ ውጤት እንደማያመጣ በምሬት የሚናገረው ዜናነህ ፦የወቅቱ ጥያቄ ሰላም መሆኑን በአጽንኦት ያስረዳል። የዚህን በሳል ጋዜጠኛ ጥልቅ ትንታኔ ያቀረበበትን ሰፊ ቃለ-ምልልስ እንድትከታተሉ እጋብዛችሁዋለሁ።
Filed in: Amharic