>

የኢትዮጵያ የኅልውና አደጋ የኦሮሞ ብል[ጽ]ግና እንጂ የውጭ ወረራ ኃይል አይደለም! (አቻምየለህ ታምሩ)

የኢትዮጵያ የኅልውና አደጋ የኦሮሞ ብል[ጽ]ግና እንጂ የውጭ ወረራ ኃይል አይደለም!

አቻምየለህ ታምሩ

የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር ፕሬዝደትን የሆኑት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፈን 80ኛውን የሚያዚያ 27 የድል በዓል አስመልክተው ዛሬ ለብዙሐን መገናኛ በሰጡት ጋዜጣዊ  መግለጫ ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ከ80 ዓመታት በፊት የገጠማት አይነት የውጭ  ወረራ ኅልውናዋን እየተፈታተነው መሆኑን ገልጠዋል።
ይህ የልጅ ዳንኤል አስተያየት  መሰረታዊ ችግር ያለበት ነው። የውጭ ጠላት ለኢትዮጵያ አዲስ ነገር አይደለም። ኢትዮጵያ እንደ አገር በዙሪያዋ የበቀሉና ከሩቅ የሚመጡ የውጭ ጠላቶች ተለይተዋት የማታውቅ አገር ነች። ኢትዮጵያ እንደ አገር ቆማ የኖረችው እነዚህን መቼም ሊጠፉ የማይችሉ የሩቅና  የቅሩብ ጠላቶቿን በውስጧ በፈጠረችው ሥርዓቷ፣ የስነ መንግሥት አስተሳሰቧና በገነባችው ጥንካሬዋ በመቋቋም ነው።
ስለዚህ በታሪኳ ሁሉ የመጡባትን የውጭ ጠላቶች በውስጥ ጥንካሬዋ ስትከላከል የኖረችን አገር ዛሬ ላይ  አዲስ የውጭ ጠላት መጥቶ የኅልውናዋ ፈተና እንደሆነ አድርጎ ማቅረብ ዋናውን የኢትዮጵያ የኅልውና አደጋ ፈረንጆቹ “The Elephant in the Room” የሚሉትን እንዳናይ የሚያደርግ አደገኛ አስተሳሰብ ነው። ከዛሬ 80 ዓመታት በፊት ለዘመናት ሲዘጋጅ የኖረው ቄሳራዊ ኃይል ኢትዮጵያን ቢደፍራትም  የያኔዋ አገራችን አለቀላት፣ ጠፋች የምትባልበት ደረጃ ላይ ግን አልነበረችም።
ይህም የሆነው ከዛሬ 80 ዓመታት በፊት በውስጧ በፈጠረችው ጥንካሬ ስትቋቋመው የኖረችው  የውጭ ጠላት ቢደፍራትም የፈጠረችው ሥርዓቷ፣ የስነ መንግሥት አስተሳሰቧና የገነባችው የውስጥ አንድነት ግን ጥያቄ ውስጥ የገባ ስላልነበረ በንጉሠ ነገሥቱ ዙሪያ የተደራጁ የኢትዮጵያ ጀግና አርበኞች ያደረጉት በነበረው አስደናቂ ተጋድሎ ኢትዮጵያን ለፋሽስት ጣሊያንም ይሁን ለማናቸውም ቄሳራዊ ጠላት ungovernable  ስላደረጓት ወድቆ የነበረው ሰንደቋ ተነስቶ ወደ ስፍራዋ መመለሷ  አይቀሬ ነበር።
በመሆኑም ዛሬ ላይ ዋናው የኢትዮጵያ የኅልውና አደጋ ወይም “The Elephant in the Room” በጥንካሬዋ ስትመክተው የኖረችው  የውጭ ጠላት ሳይሆን ከውጭም ከውስጥም ያጋጠሟትን ጠላቶቿን እንዳትመከት የኖረውን ጥንካሬዋን በኦሮሙማ እየሰበረ ያለው በመንግሥትነት የተሰየመው የኦሮሞ ብል[ጽ]ግና ነው።
በመንግሥትነት የተሰየመው የኦሮሞ ብል[ጽ]ግና ለኢትዮጵያ ያለው ጥላቻ ከአንዳንድ የውጭ ጠላቶቻችን ሁሉ ይከፋል። ሱዳን ታላቁ የዓባይ ግድብ የሚገነባበትን የጎጃም ክፍል የነበረውን መተከልን ጨምሮ ወያኔ ግማሹን ጎጃምን ወስዶ የፈጠረውን “ቤንሻንጉል ጉሙዝ” የሚባለውን ክልል ባጠቃላይ ይገባኛል ማለቷ ተሰምቷል። የኦሮሞ ብል[ጽ]ግና መተከል ወደ ጥንት  ይዞታው ወደ ጎጃም ተመልሶ የኢትዮጵያ ክፍል ከሚሆን ሱዳን ግድቡ የሚገኝበትን መተከልንና ክልሉን ባጠቃላይ ብትወስደው ይመርጣል።
በሌንጮ ለታና ገላሳ ዲልቦ ይመራ የነበረው ኦነግ ከ1983 ዓ.ም. በፊት ሱዳን ውስጥ  ዋና ጽሕፈት ቤታቸውን አቁመው ኦሮምያ ሪፑብሊክን ለመመስረት ሲታገሉ ሱዳን ለምታደርግላቸው ውለታ እንከፍላለን ብለው ቃል የገቡት ሱዳን በኢትዮጵያ ላይ ያላትን የመሬት ጥያቄ እናውቅልሻለን የሚል ብቻ ሳይሆን ናይሎቲክ ያሏዘው ጉሙዞችና በርታዎች ወደ ሱዳን እንዲጠቃለሉ በሚደረገው የሱዳን ጥረት ዋና ተዋናይ ለመሆን ነበር። በተግባርም ሱዳን ዛሬ ላይ እንዲህ  በይፋ አካባቢውን ይገባኛል ከማለቷ በፊት አካባቢው የሱዳን እንደሆነ በመጽሐፍ ጽፈው ያሳተሙ የኦነግ ዶክተሮችና ፕሮፈሰሮች አሉ። ሱዳን በጎንደር በኩል ወደ ውስጥ ከ50 ኪሎ ሜትር ገብታ የኢትዮጵያን መሬት እንድትይዝ ያደረገውም ዐቢይ አሕመድ ራሱ መሆኑን የሱዳኑ ኢታማጆች በአደባባይ የተናገረውን ልብ ይሏል። ይህ የዐቢይ እርምጃ  የመንፈስ አባቶቹ እነ ሌንጮ ለታና ገላሳ ዲስሎ ለሱዳን በገቡት ቃል ማዕቀፍ የተፈጸመ ይሁን አይሁን ወደፊት የሚታይ ይሆናል።
ከዚህ በተጨማሪ ኦሮምያቸውን ኦሮሞ ካልሆኑ ሰዎች ለማጽዳት ንጹሐን ሲጨፈጭፍ  የሚውለው የኦነግ ጦር እስካፍንጫው ያስታጠቀው የኦነግ ሰላይ የነበረው በላዔሰብ ዐቢይ አሕመድ ራሱ ነው። በሌላ አነጋገር የአማራ ተወላጆች በየቀኑ በጅምላ ሲፈጁና የዘር ማጥፋት ሲካሄድባቸው የሚውለው አማራንና አማርኛን እናጠፋለት ብለው በተነሱት በነዐቢይ አሕመድ ነው። አጣዬና ሸዋሮቢት የወደሙት ዐቢይ አሕመድ ባቀናበረው ወረራ ነው። አጣዬና ሸዋሮቢትን ሲያወድሙ እጅ ከፈንጅ የተያዙ ከሰማኒያ በላይ የኦነግ/ብል[ጽ]ግና ጦረኞች ባስቸኳይ እንዲለቀቁ የተደረገው በዐቢይ አሕመድ ቀጥተኛ ትዕዛዝ መሆኑን አዲስ ማለዳ ባሳለፍነው ቅዳሜ አስነብቦናል።
አዲስ አበባን ጨምሮ ኦሮምያ በሚባለው ክልልና በዙሪያው የሚገኙ የኢትዮጵያ ክፍሎች በኦሮሙማ በብርሀን ፍጥነት እየተሰለቀጡ ነው። ከተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ወደ ዋና ከተማችን ወደ አዲስ አበባ መግባት ድንበር አቋርጦ ወደ ጎረቤት አገር ከመሄድ ከብዷል። ኦሮምያ የሚባለው ክልል ኦሮሞ ያልሆኑ ኢትዮጵያውያን በቋንቋ እየተለዩ የሚታረዱበት ቤርሙዳ ሆኗል። ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ኦሮምያ ወደሚባለው ቤርሙዳ የሚገባ  ሰውም ሆነ መኪና አይመለስም። ይህ ሁሉ የሚሆነው በበላዔ ሰብእ  ዐቢይ አሕመድና በሚመራው በላዔል ድርጅት አማካኝነት ነው።
በተለያዩ ዘመናት የኢትዮጵያን ጥንካሬ የቀመሱት እነ ሱዳንና ግብጽ ዐቢይ አሕመድ ምን እየሰራ እንደሆነ ያውቃሉ። እነዚህ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች የነሱ ወኪሎች የነበሩ ሰዎች በዐቢይ አሕመድ ዘመን የኩራት ምልክቶች ሲሆኑ አይተዋል። በግብጽ ርዳታና በሶማሊያ ድጋፍ እየታገዘ ባሌን፣ ሐረርጌን፣ አርሲንና ከፊል ሲዳሞን ከሶማሊያ ጋር ለመቀላቀል በኢትዮጵያ ላይ የዘመተው የምዕራብ ሶማሊያው ጀኔራል ዋቆ ጉቱ በስሙ ፋውንዴሽና ትምህርት ቤት የተቋቋመለት በዐቢይ አሕመድ ዘመን ነው። በተቃራኒው ደግሞ ፋሽስት ጣሊያን ያረደው የታላቁ አርበኛ የደጃዝማች አበራ ካሣ ልጅ አርበኛው ደጃዝማች አምዴ አበራ ካሳ በአርበኛነት ለተዋደቁበት ውለታ ለስማቸው መጠሪያ ይሆን ዘንድ የተሰራ ቅርስ በዐቢይ አሕመድ ትዕዛዝ በኦሮሞ ብል[ጽ]ግና ሲፈርስ አይተዋል።
ይህ ሁሉ በኢትዮጵያ ላይ ያላቸውን ፍላጎት ለማስፈጸም ምቹ ሁኔታ እንደተፈጠረላቸው እንዲያስቡ አድርጓቸዋል። በመሆኑም ኢትዮጵያ በጥንካሬዋ ስትከላከላቸው የኖረቻቸውን የውጭ ጠላቶች እንዳትከላከል አድርጎ የውስጥ ጥንካሬዋን በኦሮሙማ የሰበረው የኦሮሞ ብል[ጽ]ግና መሪውና የኦሮሞማው ዋና ስራ አስፈጻሚ ዐቢይ አሕመድ ነው።
ባጭሩ ኢትዮጵያ የተዳከመችው በውስጥ ጥንካሬዋ ስተከላከላቸው የጥንት ጠላቶቿ ዛሬም ላይ በመኖራቸው ሳይሆን ጠላቶቿን ስትከላከልበት የኖረችው የውስጥ ጥንካሬዋ ምንጭ  የሆኑ ስልጣኔዎቿ ሁሉ በኦሮሙማ እየተሰበረ በመሆኑ ነው።
Filed in: Amharic