>
5:14 pm - Sunday April 30, 3015

ሩሲያ፣ ህንድና ቻይና ተመሳሳይ አቋም በማራመድ በአሜሪካና በእንግሊዝ መሪነት የተራመደውን ሐሳብ ተቀወሙ‼ (አወድ መሀመድ)

ሩሲያ፣ ህንድና ቻይና ተመሳሳይ አቋም በማራመድ በአሜሪካና በእንግሊዝ መሪነት የተራመደውን ሐሳብ ተቀወሙ‼

አወድ መሀመድ

በተለይም ሩሲያና ህንድ ከዚህ ቀደም ካራመዱት ሙግት በተጨማሪ፣ ሽብርተኞች በሰብዓዊ ቀውስ ሽፋን እንዳያደናግሩ መጠንቀቅ እንደሚያስፈልግና ሰብዓዊ ቀውስን አስመልክቶ በሚያሠራጩት ሐሰተኛ መረጃ ምክር ቤቱ እንዳይጠለፍ ሩሲያ አሳስባለች።
የሽብር ቡድኖች በሰላማዊ ሰዎች ደኅንነት ላይ ከፍተኛ አደጋ መደቀናቸውን የጠቀሰችው ሩሲያ ለአብነትም በሶሪያና በኢራቅ ያሉ ክስተቶችን አውስታለች። ይኼንን መነሻ በማድረግም የፀጥታው ምክር ቤት በተመድ ማዕቀፍ ውስጥ ሆኖ ሽብርተኝነትን በጋራ እንዲዋጋ የጠየቀች ሲሆን፣ ኢሰብዓዊ ወንጀሎችን በፈጸሙ ላይ በዓለም አቀፍ ሕግ መሠረት ተጠያቂ ሊሆኑ እንደሚገባ፣ ነገር ግን ይህ ጉዳይ ለፖለቲካ ጥምዘዛ አለመዋሉን መጠንቀቅ እንደሚያስፈልግ አሳስባለች።
የህንድ መንግሥትም በተመሳሳይ በሲቪል ሰዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ የሚገኘው አንዱ ጉዳይ የሽብርተኝነት እንቅስቃሴ በመሆኑ፣ የፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ይህንን የሽብርተኝነት ጉዳይ ሊዘነጋ እንደማይገባ አስታውቋል።
የሰላማዊ ሰዎችን ደኅንነት የመጠበቅና ደኅንነቸውን የማረጋገጥ ጉዳይ በመሠረታዊነት መተው ያለበት ለሚመለከታቸው መንግሥታት እንደሆነ፣ የሰላማዊ ሰዎችን ደኅንነት በዘላቂነት ለማስጠበቅ የሚቀመጡ ብሔራዊ መፍትሔዎችን ሊተካ የሚችል ቋሚ አማራጭ እንደሌለ ተከራክሯል።
የቻይና መንግሥትም በተመሳሳይ ዘላቂ መፍትሔ ሊመጣ የሚችለው ለችግሩ ሥር የሆነውን ፖለቲካዊ ጉዳይ መፍትታት እንደሚገባ፣ ይህ መፍትሔ ደግሞ ከሚመለከታቸው መንግሥታት ከውስጥ ብቻ መምጣት አለበት የሚል አቋም አራምዷል።
ተጨማሪ ለማንብቡ ሊንኩን ይጫኑት ..http://bit.ly/2Tu6XPf
Filed in: Amharic