>

ትርክተ የአማራ ኤሊት...!!! (ሔቨን ዮሀንስ )

ትርክተ የአማራ ኤሊት…!!!

ሔቨን ዮሀንስ 

ሰሞነኛ የህውሃት ቅሪቶች የመዘዙት እና አጀንዳ የያዙት የአማራ ኤሊት በሚል ስም ማጥፋትን ነው። ለብዙ ነገር ተጠያቂ የአማራ ኤሊት ነው እያሉ ሲተነትኑ ተገረምነ! እውነት የአማራ ኤሊት እንዳሉት አሁን በዚህ ዘመን የሚያስወቅስ ስራ ሰርቷል ወይስ? 
#የአማራ_ኤሊት የሚያስወቅሰው ስራ የሰራው:-
* ትናንት ህውሃት በትረ ስልጣን ስጨብጥ አገር አፍራሽ መሆኗን እያወቀ ዝም ብሎ መቀመጡ
* ትናንት ህውሃት እና ኦነግ የኢትዮጵያ መበታተኛ ህገመንግስት ሲያፀድቁ የህግ መንግስቱን ሰፊ ችግር እያወቀ ለህዝብ ይፋ ባለማድረጉና ባለመሟገቱ
* ትናንት ህውሃቶች አገርና ህዝብ ሲደፍቁ፣ የትምህርት ፓሊሲውን ሲመቱ፣ የኢኮኖሚ አሻጥር ሲሰሩ፣ ድፕሎማሲውን ሲገረስሱ፣ ዳር ድንበር ሲሸነሽኑ ዝም ማለቱ
* የአማራ ህዝብ እንደ አማራ ሲገፋ፣ የለም ሲባል፣ የጨቃኝ ትርክት ሲሸልሙት ዝም ማለቱ
* አማራ ርስቱን እና ማንነቱ በአደባባይ ሲዘረፍ ዝም ማለቱ
* ትናንት ህውሃቶች አገር ያቀናውን አማራ እንደ ባይተዋር እንዲታይ ትምክህተኛ ነፍጠኛ ወዘተ እያሉ ስም ሲሸልሙትና ሲያሳድዱት ዝም ማለቱ፣
* የአማራ ህዝብ ምንም ባልሰራው #የሀሰት_ትርክት ሲጭኑበት እና ሀውልት ሲያቆሙ እያየ ዝም ማለቱ እንዲሁም መሰል ነገሮች በህውሃት አገዛዝ ሲፈፀምብን ዝም ማለቱ ያስጠይቀዋል ካስጠየቀውም ይህ ብቻ ነው። እስኪ ዛሬ የአማራ ኤሊት ምን አጥፍቶ ነው ዘመቻ የተከፈተበት?
ትናንትም የአማራ ኤሊት ዝም ያለው ህዝብ ማስነሳትና ማሳመፅ ጠፍቶት ሳይሆን #ኢትዮጵያ እንዲትቀጥል ብሎ ነው። ምክንያት ህውሃት የማንን አጀንዳ ልታስፈፅም ወደ ስልጣን ሽኮኮ ተብላ እንደገባች ስለሚያውቅ እና ኢትዮጵያ እንዳትፈራርስ ብሎ የአማራን ህዝብ የመከራ ገፈት አስቀምሷል፤ ራሱም የገፈቱ ቀማሽ ሆኖ ኖሯል።
ትናንት ህውሃቶች እና ግብረ አበሮቻቸው የአማራን ህዝብ እና ከአማራ አብራክ የወጣውን ተፅኖ ፈጣሪ ለመድፈቅ እና ለማሸማቀቅ ሲፈልጉ ያወጡትልን ስም ነፍጠኛ፣ ትምክህተኛ፣ የድሮ ስርዓት ናፋቂ የሚል ነበር። ዛሬ ደግሞ የህውሃት ቅሪቶች #የአማራ_ኤሊት የሚል ማልቀሻ እና ታርጋ ይዘው መጡ። ስትነፋረቁ ውላችሁ ታድራላችሁ እንጂ ለእናንተ የሚሸማቀቅ ወይም ጎንበስ የሚል የለም። የሚበጀው ይልቅስ የአማራ ህዝብ እና የትግራይ ህዝብ ወደ ቀደመው ወዳጅነት መመለስ ነው። ይህ የሚሆነው ደግሞ ይህንን ስልጣን ናፈቂ ማንነታችሁን እና የውሸት ካባችሁን አውልቃችሁ ወደ እውነታው ስትመጡ ብቻ እና ብቻ ነው።
 በህውሃት እብሪትና በተከታዮች ውሸትና ማስመሰል ብሎም ሀሰትን እውነታ በማስመሰል ወሬ በማራገብ የትግራይን ህዝብ ዋጋ አስከፍላችሁታል። የትግራይ ህዝብ ትናንትም ስልጣን ይዛችሁ አልጠቀማችሁትም ዛሬም በእናንተ ውሸት ዋጋ ከፍሏል። ለዚህ አለማዘን አልችልም። በእኔ እንዲሆን የማልፈልገውን በንፁሃን ሲሆን ማየት እጅጉን ያመኛል። ለዚህ ሁሉ ምስቅልቅል መነሻ እና መዳረሻ ተጠያቂ #ህውሃት ብቻ ናት። ይህንን ደግሞ ታሪክ ለትውልድ ትውልድ ያስቀምጠዋል
በመጨረሻም:- ለሞት ያመቻቻችሁት የትግራይ ወጣት፣ ለመቅበር የታተራችሁለት የአማራ ወጣትና ህዝብ የነገ አብሮነቱን የሚያስቀጥልበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም። የውሸት ጀንበር ስጨላልም የእውነት ፀሀይ ስትወጣ ያኔ ሁሉም ይገለጣል።
Filed in: Amharic