>

የGenocide Watch ግኝቶች፣ የደረጃ ምደባና ምክረ-ሃሳብ...!!! (ኤርሚያስ ለገሰ)

የGenocide Watch ግኝቶች፣ የደረጃ ምደባና ምክረ-ሃሳብ…!!!

ኤርሚያስ ለገሰ

Genocide watch ኢትዮጵያን በተመለከተ አጣዳፊ የማንቂያ ደወል የያዘ መግለጫ አውጥቷል። ተቋሙ በምዕራባውያን ዘንድ ከፍተኛ ተሰሚነት ያለው ድርጅት እንደመሆኑ መጠን የሚያወጣቸውን ሪፓርቶች በጥንቃቄ መመርመር ያስፈልጋል። ሪፓርቱን በጄኖሳይድ ዋች ግኝቶች፣ የደረጃ ምደባና ያቀረበውን ምክረ-ሃሳብ እንደሚከተለው ቀርቧል።
1. የGenocide Watch ግኝቶች፣
1.1. Nov,2020 ጄኖሳይድ የመጀመሪያውን የማንቂያ ደወል የደወለበት ነው። በዚህን ጊዜ ዓብይ አህመድ Covid-19 ተገን አድርጎ ስልጣኑን ለማስጠበቅ ተጠቅሞበታል። ብሔራዊ ምርጫን ሁለት ጊዜ እንዲራዘም አድርጓል። አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማውጣት የመናገር ነጻነትን ገድቧል።
1.2. በየክልሉ የሚገኙ የጎሳ ሚሊሻዎች በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በቤኔሻንጉል ጉምዝ፣ አፋር፣ ሶማሌ እና ትግራይ ክልል ውስጥ ህዳጣኖችን ታርጌት ያደረጉ ጥቃቶችን ፈጽመዋል።
1.3. በኦሮሚያና አማራ ክልሎች በብዙሃንና ህዳጣን ሕዝቦች መካከል በነበረ ውጥረት ጭፍጨፉዎች ተፈጽመዋል። የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የአማራ ተወላጆችን ታርጌት ያደረገ ጭፍጨፋ ፈጽመዋል። በሚያዝያ 19 ቀን 2021 የኢትዮጵያ መንግስት በአማራ ክልል አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማወጅ የፌዴራል ኃይሎች እንዲገቡ አድርጓል።
1.4. በቤኔሻንጉል ጉምዝ ክልል የጉምዝ ሚሊሻ ታጣቂዎች የአማራ፣ የኦሮሞ፣ አገውና ሺናሻ ተወላጆችን ታርጌት ያደረገ ጥቃት ፈጽመዋል። በሚያዝያ 22, 2021 ታጣቂው ኅይል የህዳሴውን ግድብ የሚገኝበትን ሲዳል ወረዳን በመቆጣጠር ንጹሃን ዜጎችን ጨፍጭፏል።
1.5. በትግራይ ክልል በTPLF እና በኢትዮጵያ መንግስት መካከል ጦርነት ተካሂዷል። የኢትዮጵያ ፌዴራል ጦር እና የኤርትራ ጦር አሁንም በትግራይ ክልል ይገኛሉ። ዓብይ አህመድ እና የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የተቀናጁት TPLF የሚባለውን የጋራ ጠላታቸው ላይ ነው። እስከ ሚያዝያ 2021 ድረስ ወደ 2ሺህ የሚጠጉ የትግራይ ተወላጆች ተጨፍጭፈዋል።
1.6. Nov 23, 2020 የኤርትራ ሰራዊት በመቶዎች የሚጠጉ የትግራይ ተወላጆች በአክሱም ከተማ ተጨፍጭፈዋል። በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ሰራዊት “የደም ማጥራት” በሚል አስገድዶ መደፈሮች ተፈጽመዋል። 5.7 ሚሊዮን ህዝብ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል። እርዳታዎችን የማስተጓጐል ስራ ተሰርቷል። ከ62 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን በጦርነቱ ምክንያት ወደ ምስራቅ ሱዳን ተሰደዋል።
1.7. March 17, 2021 የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የተባበሩት መንግሥታት በትግራይ የተፈፀመውን ወንጀሎች ለማጣራት የጋራ የምርመራ ቡድን ለማቋቋም ተስማምተዋል።
2. የGenocide Watch የኢትዮጵያ ደረጃ ምደባ፣
በኢትዮጵያ የጄኖሳይድ ደረጃ አምስተኛ፣ ዘጠነኛ እና የመጨረሻው አስረኛ ደረጃ ደርሷል።
2.1.  ደረጃ አምስት : መደራጀት /Organization /
2.2.  ደረጃ ዘጠኝ፡ ፍጅት /Extermination /
2.3. ደረጃ አስር፡ ክህደት /Denial /
3. የGenocide Watch ምክረ  ሀሳቦች፣
3.1. አሜሪካ ፣ አውሮፓ ህብረት እና ሌሎች ለኢትዮጵያ የጦር መሳሪያ አቅራቢዎች ሁሉንም የጦር መሳሪያዎች ሽያጭ ማቆም አለባቸው ፡፡
3.2. ኤርትራ ወታድሮቿን በሙሉ ከኢትዮጵያ በአስቸኳይ ማውጣት አለባት ፡፡
3.3. የተባበሩት መንግስታት ፣ የአፍሪካ ህብረት እና አሜሪካ በኢትዮጵያ በተፋላሚ ወገኖች መካከል የተኩስ አቁም ስምምነት ማድረግ እንዲቻልና የእርስ በእርስ ጦርነት ለማስቆም ወደ ድርድር ጠረጴዛው ሊያመጧቸው ይገባል ፡፡
3.4. በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በአማራ ላይ እና በኤርትራ እና በኢትዮጵያ ወታደሮች በትግራይ ተወላጆች ላይ የተፈጸመ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተጣርቶ ወንጀለኞቹን ለህግ ማቅረብ አለባቸው ፡፡
3.5.  የኢትዮጵያ ሕገ-መንግስት ተሻሽሎ (በአንቀጽ ሰላሳ ዘጠኝ) የመገንጠል መብትን ማስወገድ አለበት ፡፡
3.6.  በክልል የተደራጁ የጎሳ ክልላዊ ሚሊሻዎች መበተን አለባቸው ፡፡ የህዳጣን መብት በጎሳ በተካሉሉ ክልሎች ውስጥ መከበርና መጠበቅ አለበት።
3.7.  በአሜሪካ እና በአውሮፓ የሚገኙ የኢትዮጵያ ዲያስፖራዎች የጎሳ ጦርነትን ለመደገፍ ገንዘብ መላክ ማቆም አለባቸው ፡፡
3.8. የኢትዮጵያ መንግስት ትግራይን በመክፈት የምግብና የመድሃኒት ስርጭት እንዲደረግ መፍቀድ አለበት፡፡
3.9. የኢትዮጵያ ምርጫ እንደገና ለሌላ ጊዜ መተላለፍ የለበትም ፣ ስለዚህም ነፃ እና ፍትሃዊ መሆን አለባቸው።
Filed in: Amharic