>

የደቡብ አፍሪካ ጥቁሮችና : የኦሮሞ ፖለቲከኞች ተመሳሳይነት !!!  (ሀይለገብርኤል ሀይሉ)

የደቡብ አፍሪካ ጥቁሮችና : የኦሮሞ ፖለቲከኞች ተመሳሳይነት !!! 

ሀይለገብርኤል ሀይሉ


በደቡብ አፍሪካ  ያሉ ጥቁሮች ትላንት በባርነት ሲማቅቁ ሲጮህና ሲታገልላቸው የኖረውን አፍሪካዊ ወንድማቸውን በተለይም ኢትዮጵያውያን ስለመሆናቸው ታሪክ ምስክር ነው:: ያ የመከራ ግዜ ተረስቶ ዛሬ የደቡብ አፍሪካ  ጥቁር እጁን የሚያነሳው በላብ በወዙ ጥሮ ግሮ በሚያድረው የእሱ ብጤ ምስኪን ጥቁር አፍሪካዊ ስደተኛ ወንድሙ ላይ ነው::

የበደሉት እንደ እንስሳ የሸጡት የለወጡት ለምድራዊ ስቃይ የዳረጉት ነጮች ላይ እንኳን ሊያምጽ ቀና ብሎ ማየት አይደፍርም::

የባርነት ሰንኮፍ የተዋራጅነት ሕይወት : የተሰበረ ሕሊና : የማንነት ምክነት : የክብር ድቀትና የበታችነት ስነልቦና ጥሎት የሚያልፈው ጠባሳ ከባድ  መሆኑ እርግጥ ቢሆንም ዋናውን በዳይን ትቶ የገዛ ጭቁን ወገንን መታገል ግን የባርነት ባርነት ነው::

በደቡብ አፍሪካ እንዲሁም በሰሜን አሜሪካ ጭምር ነጮችን የማክበርና የመፍራት ልማድ በአንጻሩ ጥቁር ጥቁርን ማጥቃት ጎልቶ ማየት የተለመደ ነው:: ይህ ከትንሽነት ስሜት የሚመነጭ እርኩስ መንፈስ ሃገራችንም ገብቶ በሃሰት ስብከት በታሪክ እስረኝነት እግረ ሙቅ የተጠፈረው የኦሮሞ ኤሊት በታሪክ አጋጣሚ ያገኘውን እድል መጠቀም አቅቶት የሚዝና የሚጨብጠው አጥቶ በስስት በጥላቻና በበታችነት ስሜት ተውጦ የነውጥ አዙሪት  ውስጥ መግባቱን እያየን ነው::

ቤተመንግስት ገብቶ በረት የሚያምረው ስጋጃ ሲነጠፍለት ቁርበት የሚያሰኘው: ወገኔ የሚለውን ጠልቶ : ጠላት ያደረገውን የረገጠና ያዋረደውን የገደለና ያስረውን የሚወደው : የኦሮሞ ኤሊት ዛሬ ሕወሃት ጫማ ስር የሚያደርገውን መርመጥመጥ ላየ ከደቡብ አፍሪካ ጥቁሮች ባህሪ ጋር ቢመሳሰልበት አይፈረድበትም::

የኦሮሞ ደም ደሜ ነው! በቀለ ገርባ መሪዬ ነው! ብሎ በመከራ ቀን የጮህው ወገን ጠላት ተደርጎ በቀለልን እስረኛ ኦሮሞን በጅምላ ጠላት ያደረገው ወያኔ ሲወደስ አጋር ሲደረግ ማየት የባርነት ጥማት የበታችነት ስሜት ካልሆነ ምን ሊባል ይቻላል!

Filed in: Amharic