>
5:13 pm - Sunday April 19, 8398

የብልጽግና ካድሬዎችም የህወሀት ጀሌዎችም ባልገባቸው አልያም አጣመው በተረዱት ጉዳይ ከፍየሏ በላይ እየጮሁ ነው...!!! (ጎበዜ ሲሳይ)

የብልጽግና ካድሬዎችም የህወሀት ጀሌዎችም ባልገባቸው አልያም አጣመው በተረዱት ጉዳይ ከፍየሏ በላይ እየጮሁ ነው…!!!

ጎበዜ ሲሳይ


ሰሞኑን በአንድ በቲዊተር ስፔስ ላይ በነበረኝ ውይይት አሁን በጦር አውድማ ውስጥ የሚገኘው የአማራ ሕዝብን ስሜት አስመልክቶ የተለያዩ ነጥቦችን አስቀምጨ ነበር። ከዚያ ውስጥ Tplf ውይይቱን ቀድተው የሚፈልጉትን ብቻ መዘው እና ቀጣጥለው ተጠቅመውበት ተመለከትኩ ።

እውነታው:-

የአማራ ሕዝብ በተለይ ከትግራይ ክልል ጋር የሚዋሰነው ህዝብ ጦርነት ሰልችቶኛል ፣ መንግስት በይደር በሚተወው ጦርነት በየአመቱ እያገረሸ ለሞትና ለስደት ዳርጎኛል ። ጦርነት አንፈልግም ዝመቱም አትበሉን የሚል አርሶ አደር አለ።

በኦሮሚያ ክልል በአንድቀን አዳር  በሺዎች የሚቆጠሩ አማሮች ታርደው ሲያድሩ መንግስት ብሔራዊ የሀዘን ቀን እንኳ ነፍጓቸዋል። ኦሮሚያ መሬታችሁ አይደለም ውጡ ስንባል፣  አዲስ አበባ ከተማችሁ  አይደለም አትገቡም እየተባልን መልሰው አገራችሁ ተወረረ ዝመቱ ይሉናል። ስለዚል  ብልፅግናም ይሁን ሕወሓት ለእኛ አንድ ናቸው ። ብሎ ያኮረፈ ሕዝብ አለ።

የአማራ ክልል ብልፅግና አንፃራዊ ሰላም አለ ብሎ ሲያስብ ደግሞ ራሱን ከጠላት ለመከላከል ወታደራዊ ስልጠና ሲወስድ የነበረን ወጣት   ኢ- መደበኛ የሚል ስም ሰጥቶ በሺ የሚቆጠሩ ወጣቶችን እስር ቤት ወርውሮ  በእጁ ያልገቡትን ሲያሳድድ ቆይቷል።

አሁን በተከፈተው ጦርነት ውስጥም ሕወሓትን ፊት ለፊት እተዋጉ የሚገኙት የፋኖ መሪዎችን  ምሬ ወዳጆን እና ደምሌ አራጋውን ለመግደል በተደጋጋሚ ከኋላ እየተተኮሰባቸው ህይዎታቸው ተርፏል። በዚህ ሁኔታ እንደት መንግስትን ተማምኜ ጦርነት እገባለሁ የሚል ወጣትም አለ ።

መንግስት ይህንን ጦርነት መቋጨት ከፈለገ እነዚህን ችግሮች ተገንዝቦ ይቅርታ የሚጠይቀውን ጠይቆ  እና ችግሮቹን ተማምኖ እና ተማምሎ ሕወሓቶች  እንደመጡበት መንገድ ሕዝባዊ መዓበል ካላስነሳን እና ሕዝቡን ወደ አንድነት ካላመጣን በሰተቀር ጦርነቱ አይቋጭም  የሚል መሬት ላይ ያገኘሁትን መረጃዎች አሰባስቤ ነው ያስቀመጥኩት ። ለምን ጦርነት በቃኝ አላችሁ ? የሚል የብልፅግና ሰዎች እየጮኹ ነው።ይሁን እንጅ እውነታውም አላማውም  ይህ ነው።

Filed in: Amharic