>
5:14 pm - Sunday April 30, 3730

አዲስ አበባም እስክንድርን ድንጋይ ተሸክሞ ማሩን የሚሉበት ቀን... (ዘመድኩን በቀለ)

የኩርቱ ፌስታሏ ግፍ…! 

ዘመድኩን በቀለ

“…የእስክንድርን ኩርቱ ፌስታል ባየሁ ቁጥር እጅግ አድርጌ እደመማለሁ። ሁሉ እያለው፣ ሁሉ ሞልቶት ነገር ግን ራሱን ዝቅ አድርጎ እንደ ድሀ እንደ የኔቢጤ ተገልጦ ለሕዝብ በተሟገተ፣ በተከራከረም በብዙዎች ተወቀሰ፣ ተሰደበም፣ ተዋረደም። አንድም የሚረዳው የሚረዳውም ሰው አጣ።

“…በዚህ በእስኬው ኩርቱ ፌስታል ያላሾፈ፣ ያላላገጠ፣ ያልቀለደ አልነበረም። የሂዊና የድሮ ገረዶቿ የኦነግ፣ የብአዴንና የኦህዴድ ካድሬዎች ቢቀልዱበት እንኳ ምንም አልነበረም። አዲሱ አረጋና ታከለ ዑማ ቢቀልዱ ኅብለ ሰረሰራቸውን ስለነካው፣ የእስክንድር አካሄድ በመንገዳቸው ላይ ጋሬጣ እንቅፋትም እንደሆነ ስለሚያውቁ፣ ስለሚረዱም ነው። የሚያሳዝነው የሚያም የነበረው የሌሎቹ የጓደኞቹ ልግጫ፣ የቅርብ ሰዎቹ ቧልትና ፌዝ ነበር።

“…እስኬው ነቢይ ነበር። ፌስታል ይዞ ወደፊት ሕዝቡ ሁሉ ሀብት ንብረቱን በፌስታል አንጠልጥሎ እንደሚንከራተት አስቀድሞ ትንቢት የተናገረ ነቢይ። የሆነውም እየሆነ ያለውም ይኸው ነው። አሁን ኦነግ ቤትህን አፍርሶ ንብረትህን በፌስታል እንኳ ይዘህ እንዳትወጣ ሲፈርዱብህ ስታይ የእስክንድር ነቢይነት ያበደውስ ማን እንደነበር ይገለጥልሃል። አዳሜን አጨለሉት እኮ። እንሰባሰብ፣ እንደራጅ፣ ዋጋ ከፍለንም ቢሆን ነፃነታችንን እናረጋግጥ ባለ ሰደቡት። አዋረዱትም።

“…ጓደኛው ሲሳይ አጌና፣ ፋሲል የእኔዓለም፣ መሳይ መኮንን፣ ደረጀ ሀ/ወልድ፣ ኢዜማ ግንቦት ሰባቶች ለኦህዴድኦነግ ገሌ ሆነው የትግል አጋራቸውን አጣጣሉት። በናትናኤል መኮንን አፍ አሰደቡት። ስዩም ተሾመ፣ ብሩክ አበጋዝ ከኦነግና ሂዊ እኩል ወቀጡት። እርሱ ግን ነቢይ ነበር።

• ዐማራ ጄ/ል አሳምነው መቃብር ላይ ተንከባልሎ፣ አዲስ አበባም እስክንድርን ድንጋይ ተሸክሞ ማሩን የሚሉበት ቀን መጥቶ ስላየሁ አምላኬን አመሰግናለሁ።

•እህዕ…!

Filed in: Amharic