>

ማሳሰቢያ! ለአማራ ፋኖና የነፃነት ታጋዮች በሙሉ! (ዳግማዊ ጉዱ ካሣ)

ማሳሰቢያ! ለአማራ ፋኖና የነፃነት ታጋዮች በሙሉ!

ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

ለኢትዮጵያ ትንሣኤ ትግሉ በአማራው ክፍላተ ሀገራት ይጀመር እንጂ ኃይልና አቅም እየተጠናከረ ሲመጣ ምንም ዓይነት ወያኔሠራሽ ድምበር ሊያግደው እንደማይችል መታወቅ አለበት፡፡ ወያኔ ለኢትዮጵያ ያቆመው ውሽልሽል ህገ መንግሥት በራሱ በወያኔና በልጁ ኦህዲድ-ኦነግ-ሸኔ እንደተፈለገው እየተጣሰ በ”ሲሞቅ በማንኪያ ሲቀዘቅዝ በእጅ” የብልጦች አካሄድ አሁን ላይ ደርሰናል፡፡ ከአሁን በኋላ ግን አቅም ያለው ወገን ከተጻፈበት ወረቀት እጅግ ያነሠ ዋጋ ያለውን ያን ሸፋፋና ሀገር ያፈረሰ ህገ መንግሥት ተብዬ በጣጥሶ የመጣል መብቱ በእጁ ነው፡፡ ይሄ አቅም ያለው ኃይል ደግሞ በሚሊዮኖች ኢትዮጵያውያን ልብ ውስጥ በፍቅር የተቀመጠውና አራት ኪሎን እስኪቆጣጠር እስካሁን ታይቶ በማይታወቅ ጉጉት የሚጠበቀው በአማራው የተጀመረው የነፃነት ትግል ነው፡፡ በዚያ ትግል ውስጥ ደግሞ የዘር ልክፍት ሊኖር እንደማይችል ሁሉም ወገን ሊገነዘብ ይገባል – አማራጭ በማጣት ለሥልታዊ የትግል ጅማሮ ከሚቀነቀን ኢትዮጵያዊ አማራነት ውጪ ለጎጥና ለሸጥ ብሎ የተነሣ፣ ለዚህ ወይ ለዚያ ሃይማኖት ብሎ በረሃ የገባ አንድም ሰው የለበትም – በዚያ ጎራ ውስጥ፡፡ ትግሉ የዘርና የጎሣ ሳይሆን የኅልውና ነው፡፡ እንደሰው ቁጠሩኝ ብሎ የመለመን ያህል፡፡

ይህ ትግል ኢትዮጵያን ከሙታን ሀገራት ቀስቅሶ የሚያስነሣ፣ ዜጎቿን ከርሀብና ከርዛት፣ ከሞትና ከስደት፣ ከመፈናቀልና ከገዛ ቀዬ ባይተዋርነት፣ ከብልት ሰለባና ጅምላ ፍጂት፣ ከድንቁርናና ሰይጣናዊነት ወዘተ. የሚታደግ በመሆኑ አንድም ክልላዊ ወይም ሥነ ልሣናዊ ድምበር አያግደውም፤ ሊያግደውም አይገባም፡፡ በዚያ ላይ የኦሮሞ ልዩ ኃይልና ሚሊሺያ በዘመኑ አነጋገር  በመከላከያ ስም አማራ ክልል ገብቶ እንዳሻው ካጓራና ሴት ሕጻን ሳይል ዓለም አይታውና ሰምታው የማታውቀውን ግፍና በደል ከፈጸመ የአማራ ፋኖ ጎሬና ደምቢዶሎ ሄዶ ይህን በሰው አምሣል የተፈጠረ ሦዶማዊ ዐውሬ ማንቁርቱን በመያዝ ለፍትኅ አደባባይ ማብቃት ጽድቅ እንጂ ኩነኔ የለውም፡፡ ለዚህ የተቀደሰ ተግባር ደግሞ ዘርና ቋንቋ ሳይለይ ሁሉም መተባበር አለበት፡፡ ይህ በኦሮሞ ስም እየነገደ ያለ በላዔሰብኣዊ የሦዶማውያን መንጋ ከአራት ኪሎ እስከወለጋ ጫካ ምን እየሠራ እንደሆነ ሌላው ቀርቶ ለሱም ያልተመለሰለት ኦሮሞውም ያውቃል፤ ካላወቀም ማወቅ አለበት፡፡ የምንገኝበት ዘመን እንኳን አንድ ቋንቋ መናገር የገዛ ልጅም ለውርስ ሲል አባት እናቱን የሚያርድበት እጅግ አስጠሊታ የመጨረሻ ዘመን ነው፡፡ ስለሆነም ኦሮሞውም ለራስህ ስትል ንቃ፡፡ አቢይና ሽመልስ የሚባሉ ዘመናዊ ሸኔዎች ጫካ ከሚገኘው “barbaric” (ዐረመኔ) ሸኔያቸው ጋር በስልክ እየተገናኙ አማራን ከማጥፋት ጎን ለጎን ኦሮሞውንም ምን ያህል ቁሉቁል እንደጎተቱት የሚታወቅ ነው፤ ኦሮሞም በሸኔ እንደሚገደል የማያውቅ ሰው ካለ ብዙ መረጃ አምልጦታል፡፡ ስለዚህ ሁሉም ከተኛበት ይንቃና መጪውን ወርቃማ ዘመን ለመቀበል ዝግጁ ይሁን፡፡

ያለ የሚመስለውም እንደሌለ ይቁጠረው፡፡ መኖር ማለት ቆንጆ ቤት ውስጥ መኖር፣ ቆንጆ ትዳር መያዝ፣ ቆንጆ መኪና ማሽከርከር፣ ባንክን በገንዘብ ማስጨነቅ፣ ወቅት እየጠበቁ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ከነቤተሰብ እየተንሸራሸሩ መዝናናት፣ ስመ ጥር ሆኖ በየሄዱበት ሰውን ከመቀመጫ ማስነሣት… አለመሆኑን ለመረዳት በግድ ሦርያንና ሩዋንዳን ማስታወስ አይገባንም፡፡ በከፊልም ቢሆን እዚሁም መጥቷልና! በሙሉ ግርማ ሞገሱ ከተገለጠ ግን ማንንም ከማንም የማይለይ ሲዖላዊ ነበልባል በየቤትህ ይዘንብና አሣርህን ትበላለህ፡፡ ያንን ቅዠት መሠል ህልም ለማስቀረት ታዲያ ከዘረኝነት አሽክላ ራሳችንን ነፃ አውጥተን ምዕመን በጸሎቱ፣ ወጣት በጉልበቱ፣ ሀብታም በገንዘቡ፣ ዐዋቂ በውቀቱ፣ ባለሙያ በሙያው የነጻነት ታጋዮችን ማገዝና ማንም ፈለገ አልፈለገ ምናልባት በኛው ስህተት ሊዘገይ እንጂ በፍጹም ሊቀር የማይችለውን ትንሣኤ ለማምጣት ሁላችንም በየፊናችን መጣር አለብን፡፡ የነጻነቱ በረከት ለሁሉም እስከሆነ ድረስ በትግሉም ሁሉም ይሳተፍ፡፡ ፈረንጆች እንዲህ ይላሉ፤ There is no free lunch.

በነገራችን ላይ የአማራ ትግል አሁን ባለው ሙቀት የተጀመረው አማራ ስለፈለገ ወይ ስላልፈለገ አይደለም፡፡ ከ30 ዓመታት በላይ የተጮኸበትን የአደባባይ ምሥጢር ነው የምነግርህ፡፡ እናም ፈጣሪ ባለጌና ስድ አደግ ወያኔዎች ላይ ፈርዶ ድንገት ሳያስቡት ያንን ሁሉ የጦር መሣሪያና ሀብት ንብረት ይዘው የዶጋመድ አድርጓቸዋል፡፡ ጉራቸውም ሆነ ወታደራዊ ዝግጅታቸው ከዕልቂት አላዳናቸውም፡፡ የሠሩትን ግፍ ፈጣሪ ተበቀላቸው፡፡ ይህ ዓይነቱ የብድር አከፋፈል ዱሮም ነበር፤ አሁንም አለ፤ ወደፊትም ይኖራል፡፡

አሁን ደግሞ ተራው የኦሮሙማ ነው፡፡ ባላሰቡትና ባልጠበቁት ሰዓት፣ ባልገመቱት አቅጣጫ እንደ እቶን እሳት የሚዘንብባቸውና የሠሩትን ሁሉ የሚያስከፍላቸው የዕልቂት ዶፍ ይዘንብባቸዋል – ሊያውም የወያኔን የሚያስንቅ ፍዳ፡፡ እነዚህ ጭራቆችና ሆዳሙ አማራ ዕጣ ክፍላቸው አንድ ነው፡፡ እንዳለመታደል ሆኖ የአማራን የነጻነት ትግል በእጅጉ እያዘገዩት ከሚገኙ ነገሮች ውስጥ አንዱና ዋናው በውስጡ የተሰገሰገው የብአዴንና የሆዳሙ ብዛት ነው – ይሄ በፊት ለፊታችን ተሸክመነው የምንሄደው ሆድ የሚባል ነገር ብዙ ትንግርት እያሳየን ነው፡፡ ከይሁዳና ከዚያም በፊት ከእናታችን ከሔዋንና ከቃየል ጀምሮ ይህ የግል ጥቅምንና ፍላጎትን የማስቀደም አባዜ የሰውን ልጅ ክፉኛ እንደተፈታተነውና እንዳሰቃዬው አለ፡፡ የዕብለትና የማስመሰል ሊቀ ጠበብቱ ቃየሉ አቢይ አህመድ እንኳን እንዲህ እንቅልፍ አጥቶ የሚሰቃዬው ከ123 ሚሊዮን ሕዝብና ከአንዲት ታላቅ ታሪካዊት ሀገር ኅልውና ይልቅ የርሱ ሰይጣናዊ ፍላጎትና የሥልጣን ጥም በልጦበት መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ይገርማል፡፡ ለማንኛውም ለዚህ ዓይነቱ ደንቃራ አፋጣኝ መፍትሔ ካልተበጀለት ትግሉ የሚወስደው ጊዜና መስዋዕትነት ከሚጠበቀው እንዳይበልጥ ያሰጋል፡፡ በተረፈ በተጀመረው የነጻነት ትግል አሸናፊነት የሚጠራጠር ካለ በፈጣሪ ፍርድና በታሪክ የቅጣት ብትር የማያምን ጭፍንና ሞኛሞኝ ነው፡፡ 

ሁሉ ነገር አይነገርም፤ ሽል ስለፈለግኸው አለሰዓቱ አይወለድም፡፡ የአማራ ፋኖና የአማራ ሕዝብ ማድረግ ያለበት የግፍ ሥራን ተጸይፎ፣ በአያት ቅድመ አያቶቹ የሞራልና የሃይማኖት ሥነ ልቦናዊ ልዕልና ተመሥርቶና ሌሎች የወያኔና ኦሮሙማ ግፍና በደል ሰለባዎችን አስተባብሮ የጠፋችዋን ኢትዮጵያ ትንሣኤ ማብሠር ነው፡፡ ስለሌላው ቀስ በቀስ እናወጋለን፡፡ ዱቢን ያቡልቱ ይላል ወንድሜ ሂርጳሣ፡፡

Filed in: Amharic