ቅንጣት ቅንነት የጎደለው የአንድ ማንኪያ ቅንነት ሴራ ብዙም ሳይገፋ ጭንብሎ ተገላልጦ ጸረ አንድነት አላማን ይዞ ብቅ ብላል!!!!
“አንድነትን” ለገንዘብ መሸቀያ የማድረግ ጸያፍ አካሄድ
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ሲምፖዚያም – ተብሎ ሰሞኑን ሲተዋወቅ የነበረው ፕሮግራም በትናንትናው እለት ፕሮግራሙ ገንዘብ የማሰባሰቢያ ፕሮግራም ለመሆኑን በማብሰር ተጀምራል።
ለአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች አንድነት እና ብሎም የአማራ ፋኖ ወደ እርስ በርስ ጦርነት እንዳይገባ ብርቅዬ ጀግኖቹን እየሰዋ ቅንጣት ቅንነት ብቻ ሳይሆን ታላቅ የህይወት ዋጋ እየከፈለ ያለው እውነተኛው የአማራ ፋኖ አንድነት የሚቃትተው የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) ይህንን የአፋብኃን ሲምፖዚየም ስኬታማ ይሆን ዘንድ በትናንትናው እለት ሊያካሂድ ያቀደውን ሕዝባዊ ውይይትን በመሰረዝ የተለመደ ተግባራዊ ቅንነትን አስመስመሰከረ።
የፋሕድ ከፍተኛ አመራሮች ታላቁ አርበኛ እስክንድር ነጋ፣ አርበኛ ጌታ አስራደ እና አርበኛ አበበ ጢሞ በአማራ ፋኖ አደረጃጀቶችን ወደ አንድነት በማምጣቱ ጉዳይ ላይ ሕዝባዊ ድርጅቱ በ 2018 እፈጽመዋለሁ ብሎ ከሰምንታት በፊት ባወጣው መግለጫ ባሰፈረው ጉዳይ ላይ ማብራሪያ ለመስጠት ለትናትና እለት መስከረም 6 ቀን 2025 ፕሮግራም አዘጋጅቶ ነበር። (ማስታወቂያውን ይመልከቱ) የሶስቱ አመራሮች ፕሮግራም ለቀንት ያህል ሲተዋወቅ ከሰነበተ በሃላ በመጨረሻው ሰአት ላይ ብልሆቹና እውነተኛ ቅኖቹ የአፋሕድ አመራር አፋብኃ የጠራውን ሲምፖዚየም ያሳካ ዘንድ ለህዝባችን ተደራራቢ ፕሮግራም ከማቅረብ የእኛን ፕሮግራም ስርዘነዋል በማለት Practical የሆነ ተጨባጭ ቅንነትን በመፈጸም አሳይቶናል።
በእርግጥ የአፋሕድን ለአማራ ፋኖ ሀይሎች እንድነት ያለውን ታላቅ ቅንነትና መቃተትን በዚህ በትናትናው እለት አዘጋጅቶት በነበረው የህዝብ ለህዝብ ስብሰባና ውይይትን ለአፋብኃ ሲምፖዚየም ብሎ በመሰረዝ ብቻ የሚገለጽ አይደለም። አፋሕድ ስለ አማራ ህዝብ አንድነት ብሎ ብርቅዬ ታጋይና አታጋይ መሪዎቹ በግፍ ሲገደሉበት የአጸፋ ምላሽ ባለ መስጠት ስለአማራ ህዝብ አንድነት የህይወት ዋጋ የከፈለ ታላቅ አማራዊ ድርጅት ነው።
ማንም ተቀበለ አልተቀበለ የአማራ ፋኖ ሀይሎች ወደ እርስ በርስ ጦርነት ያልገቡበት ዋና ሚስጥር የአፋሕድ ምትክ የለሽ ህይወትን እየገበረ – የጉደኞችን ጸረ አንድነትን ጥቃት እየተሸከመ ዝም የማለቱ ውጤት ነው እንጂ በግልብ አስተሳሰብ በሚሾፈረው የአፋብኃ ሀይሎች ቅንነትና አስተሳሰብ የተገኘ አይደለም። ቢያንስ የአማራ ፋኖ ዛሬ ወጥ የሆነ አንድ ድርጅታዊ መዋቅርን መፍጠር ባይችል እንካን ሁለት አማራዊ ድርጅት ሆኖ ግን የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ እንዳይገባ የተደረገው በእውነተኛው የአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ታግሎ አታጋይ ድርጅት አፋሕድ የህይወት ዋጋ ከፋይነት ነው። ይህ 100% Fact የሆነን ሀቅ እያንዳንዱ አማራ ማወቅና መረዳት ያለበት እውነታ ነው።
አፋሕድ እየተተኮሰበት መልሶ ያልተኮሰ ነው። አፋሕድ እንደነ አርበኛ ከፍያለው ደሴ አይነቱን እንቁ ጀግናን እየተነጠቀ የአጸፋ ምላሽ ያልሰጠ ነው። አፋሕድ በአንዲት ጀንበር ዘጠኝ ያህል አመራሮቹ ተገድለውበት ፈጽሞ ምላሽ ያልሰጠ ድርጅት ነው። አፋሕድ በዘመቻ አንድነት ስም ግልጽ ጦርነት በወሎ፣ በጎጃም፣ በጎንደር እና በሸዋ ተከፍቶበት ብርቅዬ ጀግኖቹ ተሰውተውበት ስለአማራዊ አንድነት ብሎ ታላቅ የህይወት ዋጋ ከፍሎ የአጸፋ ምላሽ ባለ መስጠት የአማራን ፋኖ ከእርሰበርስ ጦርነት መታደግ የቻለ ታላቅ ሆደ ሰፊ አማራዊ ድርጅት ነው። ለዚህም የድርጅቱ ሰብሳቢ ታላቁ አርበኛ እስክንድር ነጋን ጨምሮ የህዝባዊ ድርጅቱ በሳል አመራሮች ታላቅ የሞራል ልቀትና ስብእናን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።
ወደ ትናንትናው የአፋብኃ ሲምፖዚየም ጉዳይ ስንመጣ ሲምፖዚየሙ የተዘጋጀው አርበኛ ዘመነ ካሴ ከሰምንታት በፊት አንድነት የምርጫ ጉዳይ ሳይሆን የግዴታ ጉዳይ ነው የሚል አይነት እድምታ ያለውን የአንድነት ጥሪ ባስተላለፈ ማግስት የተጠራ ሲምፖዚየም በመሆኑ ዋና አጀንዳው የአንድነት ጉዳይ ይሆናል ተብሎ ነው የተጠበቀው እንጂ ሙሉ በሙሉ የህዝባችንን ኪስ ለማራቆቻነት ገንዘብ ለመሰብሰቢያነት የታሰበ ነው ብሎ የገመተ አልነበረም። አፋሕድን ጨምሮ ድርጅቶች ገንዘብ የማሰባሰብ ስራን ሲያካሂዱ ይታወቃሉ። ሁሉም አደረጃጀት በየፊናው ድጋፍ ያሰባስባል። ድጋፍ ማሰባሰብ በራሱ ምንም ችግር የለውም። የሚሰበሰብበት መንገድ ግን በማያሻማ ሁኔታ የአፋሕድ የድጋፍ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ወይም የአፋብኃ ድጋፍ የማሰባሰቢያ ፕሮግራም ተብሎ በመተቃወውቅ ነው እንጂ የአንድነት ጥማት እንጥሉን የቆረጠውን ሕዝብ ስነልቦናን ታክኮ በእድንድነት ስም በተዘጋጀ የአንድነት ሲምፖዚየምን የገንዘብ ማሰባሰቢያ በማድረግ አይደለም።
አፋብኃ በአንድነት ስም ባዘጋጀው ገንዘብ መሰብሰቢያ ሲምፖዚያም መድረክ ላይ ቀርበው መልእክታቸውን ያስተላለፉት እነ አስረስ ማረ ዳምጤ፣ ምሬ ወዳጆ፣ ሀብቴ ወልዴና አስቻለው ስለአማራ አማራ ፋኖ አንድነት ፈጽሞ ትንፍሽ አላሉም። ስለአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች አንዲትም ቃል ትንፍሽ ሲሉ አልተደመጡም። ስለራሳቸው ውስጣዊ “አንድነት” ከመዘብዘብ ባሻገር ስለ መላው የአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች አንድነት ትንፍሽ አይሉም። አይደለም አንድ ማንኪያ ቅንነት ይቅርና ቅንጣት ታህል ቅንነትን ነጥፎባቸው ላዘጋጁት ሲምፖዚየም መሳካት ብሎ የራሱን ፕሮግራም የሰረዘውን አፋሕድን ስም ጠቅሰው ለአንድነት የሚሰጥ ቅንነት ከዚህ ጀምራል፣ አፋሕድ ስለአፋብኃ ሲምፖዚየም ብሎ ያዘጋጀውን ፕሮግራም በመሰረዙ እናመሰግናለን በማለት እውቅና ሲሰጡ አልተሰሙም። በአጠቃላይ ፕሮግራሙ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ስለአፋሕድ ቅንጣት ቃል አልተነፈሱም።
አስረስ ማረ ዳምጤ ከሌሎች አመራሮች በተለየ ሁኔታ በሰጠው ዘለግ ያለ ንግግር ይህንን የፋሺስቱን የብልጽግናን ስርአት ከተቻለ ከሌሎች ኢትዮጲያዊያን ሀይሎች ጋር በጋራ ተባብረን ለመጣል እንታገላለን ብሎ በገለጸበት አንድበቱ ከሌሎች የፋኖ አደረጃጀቶች አፋሕድ ጋር በጋራ አንድነትን ፈጥረን ፋሺስቱን እንታገላለን ለማለት አልደፈረም። ስለሆነም የሰሞኑ የአንድነት ነጠላ ዜማ የተለቀቀው ስለአማራ ፋኖ አንድነት ከመጨነቅና ከማሰብ ሳይሆን የህዝባችንን ኪስ ለመፈተሽና ገንዘቡን ለመቃረም ታስቦበት የተለቀቀ አሳሳች የአንድነት ነጠላ ዜማ መሆኑን የትናንትናው ሲምፖዚየም በገሀድ አሳይቶናል።
ስለአንድነት ስናወራ፣ አንድነት ማለት የማይታይ፣ የማይዳሰስና የማይገለጽ አበስትራክት ረቂቅ የሆነ ማለት አይደለም። The building blocks of unity ተብሎ የሚገልጹት የአንድነት ጡቦች የሚታዩ፣ የሚጨበጡ፣ የሚዳሰሱና የሚገልጹ የአንድነት ጡቦች ናቸው እንጂ ድብቅና አበስትራክት አይደሉም። ለአብነትም ያህል አፋሕድ ይህንን የአንድነትን መገንቢያን ጡብ Boldly በመጠቀም ፊት መሪ ሆኖ እያሳየ ይገኛል።
፩ኛ- ባለፈው ግንቦት ወር ጎንደር ላይ አፋብኃ በተመሰረተ ማግስት እውቅና በመስጠት እንካን ደስ ያላችሁ በማለት ደስታውን ገልጻል።
፪ኛ- አፋሕድ አፋብኃ በተመሰረተ ማግስት ባስተላለፈው የእንኳን ደስ ያላችሁ መልእክቱ ላይ ለአንድነት ጥሪ በማቅረብ መልሳችሁን በጉጉት እንጠብቃለን በማለት ጥሪ አቅርባል
፫ኛ- አፋሕድ በአፋብኃ በኩል ለተከፈተበት ተደጋጋሚ ጥቃት የአጸፋ ምላሽ ባለ መስጠት የህይወት ዋጋ እየከፈለ ስለአማራ ፋኖ አንድነት እጅግ ታግላል፣ ከፍተኛም ዋጋ ከፍላል
፬ኛ- አፋሕድ የትናትናውን የእፋብኃ ሲምፖዚየም ይሳካ ዘንድ አዘጋጅቶት የነበረውን ፕሮግራሙን በይፋ ሰርዛል ።።
ይህን ሁሉ ለአንድነት የሚጠቅሙ ግብአቶችን በአፋሕድ በኩል ሲፈጸሙ ብናይም በአፋብኃ በኩል ግን በዚህ በተቃራኒ መንገድ በረቀቀ ሴራ የልዩነትን መንገድ እያሰፋ ከመጋዝ በስተቀር አንዲትም ቀን ለአፋሕድ ታላቅ ቅንነት ቅንጣት ታህል ቅንነታዊ ምላሽ ሲሰጥ እስከዛሬ ፈጽሞ አላየንም። አልሰማንምም።
የማይተማመኑ ባልንጀራሞች በየወንዙ ይማማላሉ
አራቱ የአፋብኃ መስራችና አባል ድርጅቶች በራሳቸው ድርጅታዊ አንድነትን መፍጠር የተሳናቸው እና በዚህም እርስ በርስ መተማመን ያለመቻል ሁኔታ አፋብኃን መሪ አልባ አድርገው አንዴ በባለ 13 አባላት የቡድን መሪዎች የሚመራ፣ሌላ ግዜ ደግሞ በአራቱ ድርጅቶች መሪዎች የሚመራ ድርጅት ነው እያሉ ከመግለጽ የዘለለ የድርጅቱን ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴን አዋቅረው፣ የድርጅቱን ሰብሳቢ፣ ምክትል ሰብሳቢ፣ የፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ፣ የወታደራዊ ዘርፍ አዛፍ፣ ቃለ አቀባይ •••••ወዘተ የስራና የሀላፊነት ድልድል አድርገው መንቀሳቀስ ያልቻሉት እጅግ ስር የሰደደ እርስ በርስ ያለመተማመን በውስጣቸው የሰፈነ በመሆኑ ነው አፋብኃ መሪ አልባ ድርጅት አድርገው ሲንቀሳቀሱ ማየት የቻልነው። እጅግ የሚገርመው ደግሞ የአፋጎ ጥሎት ከወጣው ወደ አፋብኃ መመለስን ልክ እንደ የአፋብኃ እና አፋሕድ በጋራና በአንድነት ለመታገል እንደ ተስማሙ አይነት እድምታ እንዳለው አድርገው እንካን ደስ ያላችሁ እያሉ ሲገልጹ መስማት ነው። አፋብኃ የተመሰረተው በአፋጎና ሶስቱ ድርጅቶች ነው። በስልጣን ይገባኛል ጥያቄም ከመሰረተው አፋብኃ አፋጎ ለቆ ከወጣ በሃላ ብቻውን ቅርቃር ውስጥ ሲገባ አንገቱ ተይዞ ወደ አፋብኃ የተመለሰ ነው። ይህንን ሂደት ልክ በመላው የአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች መካከል እንደተደረገ አንድነት አድርጎ ማስተጋባት የድንቁርና ጥግ መገለጫ ሆኖ ከማሳየት የዘለለ ስለአንድነት የሚያሳየን ቅንጣት ሂደት የለም።
ቢፈጸምም ፣ ባይፈጸምም የአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች አንድነት በሚከተለው መንገድ የሚፈጸም ይሆናል
፩ኛ- አፋብኃ – ድርጅት ሆኖ ለመውጣት በቅድሚያ የራሱን መሪና ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴን በአስቸካይ በይፋ መርጦ መሰየም ይጠበቅበታል። ( አፋብኃ ከአራቱ አመራሮች ዘመነ፣ሀብቴ፣ምሬና ደሳለኝ መካከል በአስቸካይ አንዱን መሪ አድርጎ መምረጥ ይገባዋል)
፪ኛ- አፋብኃ ለአፋሕድ ይፋዊ ጥሪ ይፋዊ መልስ መስጠት ይጠበቅበታል
፫ኛ- አፋሕድ እና አፋብኃ ኮሚቴ ያዋቅራሉ
፬ኛ- አፋሕድ እና አፋብኃ ጠላትን በጋራ ለመታገል ድርጅታዊ ህልውናቸውንና ነጻነታቸውን ይዘው በጠላት ላይ የጋራ ግንባር በመፍጠር ጎን ለጎን በጋራ ይታገላሉ። በዚህ ሂደት ወደፊት ወደ አንድ ድርጅት የመምጣትን እርስ በርስ መተማመንን ለመፍጠር Mutual Trust ይሰራሉ። ከተሳካም መጨረሻ ላይ ወደ አንድነት ይመጣሉ። ከዚህ የዘለለ Over night የሚከሰት አንድነት ፈጽሞ አይታሰብም። ለጊዜው የስሞኑ የአንድነት ነጠላ ዜማ አፋብኃዎች አጀንዳውን ለገንዘብ መሰብሰቢያነት እንደመዘዙት መረዳት ይገባል። አበቃሁ።
ጋዜጠኛ ወንድወሰን ተክሉ (ጋሻ ሚዲያ)