ከአዳባይ
አፋብን የሚባል የአማራ ህዝብን የህልውና ትግል የሚመራና ለውጤት የሚያበቃ ድርጅት ከመመስረቱ በፊትና ከተመሰረተም በኋላ ፀረ-ትግል አቋም ያለው የብአዴንና ህወሓት የእጅ ሥራ ነው ብለን በመረጃም በማስረጃም ስንሞግት ጥግ ይዘህ የቆምከው ሁሉ ዛሬ ለአፍሪካ ህብረት የአደራድሩኝ ደብዳቤ ፃፈ ብለህ ለምን ታለቅሳለህ።
ይህ ሰብስብ የዘመነ ካሴን የመሪነት ቅዠት ከማሟላትና አስረስና ቤተሰቡ ከብአዴን የተሰጣቸውን ፋኖን የመቆላለፍ ስልት ከማሳካት በዘለለ ትርጉም እንደማያመጣ ደጋግመን ስንጠቁም ሙድ ይዘህ የነበርክ ዲያሰፓራ ዛሬ እንዴት ከእንቅልፍህ ነቃህ?
ብታምንም ባታምንም አፋብን እነ ሻለቃ መከታውን በመሐል ያቀላቀለው የፋኖን እምነት ለማግኘትና ካለ አንዳች ግርግር ወደ ብአዴን ጠቅልሎ ለመግባት እንጂ 13 ሆኖ አንድ ሰብሳቢ መመረጥ ያልቻለ የጠላት ወኪል እንዴት አማራን መርቶ ለድል ሊያበቃ ይችላል ብለህ ደጋግመህ ጠይቅ?? መልሱን እዛው ታገኛለህ
ዘመነ ካሴና አስረስ ማረ የጎጃምን ጠንካራ ሰራዊት በመከፋፈል እና እንደ ኮሎኔል ጌታሁን ያሉ ብርቅዬ የፋኖ መሪዎችን ወይ እኛን ምሰል ካልሆነም ወደ ብልፅግና ግባ እያሉ ያዋከቡ በዙ ጀግኖች የጎጃም ታጋዬችን የረሸኑ ያሰሩ :አካል ያጎደሉ :የህወሓት ጀነራሎችን በክብር ፈትተው ሸኝተው ካኪ ቱታ ሲቀበሉ የጎጃም ህዝብ አገልጋይ የሆኑትን መምህራን ሰብስበው የፈጁ:በስለላ ስም 3 የአማራ እንስቶችን በጥይት ደብድበው ሰላዬችን ገደልን ብለው በአደባባይ በመናዘዝ የአማራን ህልውና ትግል በማጠልሸት ሌላ ስያሜ እንዲሰጠው ሲታትሩ የነበሩና አሁንም የተሻለ የማፍረስ እድል የተሰጣቸው ተረፈ ብአዴን ወህወሃት ናቸው ።እውነቱን መቀበል ሳትችል አታልቅስ ?
እንደ አባይ ጠንቋይ(ቃልቻ) 5 ቱም ጣቱ ላይ ቆርቆሮ የሚያንጠለጥለው ዘመነ ካሴ በመጀመሪያ አፋህድ ሲመሰረት ቀጥሎም አፋብሃ ሲሰባሰብ መሪ ካልሆንኩ ብሎ የአማራን ህዝብ መከራ ያራዘመ ከህወሓት የጃጁ ፓለቲከኞችና ከሚጠነቁሉሉት ጋኔል ጎታች ደፍተራዎች (ደብተራ አላልኩም ) ውጪ ማንንም የማይሰማ የወያኔ እጅ ሥራ ሲሆን በአፋብሃ ውስጥ ሰብሳቢ የሚለው ማዕረግ በሌለበት የተቸረው በህወሓት ፍላጎት በአንዳርጋቸው ፅጌ:ሻለቃ ዳዊት :መአዛ መሐመድ እና በዋናው የብአዴን ተወካይ አስረስ ማረ አመቻችነት ነው ።ለዚህም ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ ሰሞኑን በሚዲያ ላይ ቀርበው 320 ስአት ከአስረስ ጋር ተወያይተናል ሲሉ ምስክርነት ሰጥተዋል።ከዚህ በላይ እውነታ ከየት ተፈልጎ ነው ዘመነና ቡድኑን የአማራን ትግል ቸርችረው እስኪጨርሱ እያለቃቀስን የምንጠብቀው?? ዘመነስ የትኛውን ፋኖ ሲመራ ታይቶ ነው አሁን መሪ የተባለው?
በቀላል አገላለጽ በአፋብሃ አመራር ውስጥ
1.ቁልፍ የህወሓት ወኪሎች ሆነው አማራን ለመሸጥ የተሰለፉት
ዘመነ ካሴ :ሄኖክ አዲሴ: ጀነራል ተፈራ ማሞ :ምሬ ወዳጆ :አበበ ፈንታውና በሃብቴ ወልዴ ከሚመራው ሃይል ውስጥ ጎልተው ለመውጣት የፋኖን በትር ፈርተው የሚጥመለመሉ ግለሰቦችን ጨምሮ
2.ዋነኛ ብአዴኖችና ትግሉን የባህርዳር ስልጣን ፍለጋ አድርገው ለመሸጥ የሚሰሩ
አስረስ ማረ ከነ ቡድኑ (ማርሸት ፀሐዬ:እሸቱ የሚባል የብአዴን ወጣት ክንፍ የነበረ:የግንቦት ሰባቱ ጥላሁን አበጀ ወዘተ) :ጌታ አስራደ ( ይህ ሰው ለአሸናፊው በመሰለፍ ልምዱን ያሳዬና አፋህድን ከውስጥ አስሮ ከጅዎችን በማበረታታት ድርጅት ያፈረሰ የእያሱ አባተ ተከታይ ነው) የመሳሰሉት ፀረ ህልውና ትግል ጠላፊዎቹ የአንድነት ሰብስብ የፈጠረውን የፋኖ ጀግኖች በሥነ ልቦና በማዳከምና ከጀርባ በማስመታት አማራውን ዘላለማዊ ባሪያ አድርጎ ከማለፍ የዘለለ ሚና ስለሌላቸው ታጋዬ በሙሉ ይህን አውቆ የራሱን ትግል በራሱ ታማኝ መሪዎች በማስቀጠል ወደ አራት ኪሎ መገስገስ አለበት በሚለው ልንግባባ ይገባናል ።አፋብሃ የፋኖን አንድነት አምጥቷል የምትሉ የአሰረስ ተጠርናፊዎች መረዳት ያለባችሁ የፋኖ እርስ በእርሱ ግጭት ምንጭ የሆኑት ግለሰቦች የሚፈልጉትን ስልጣን ስላገኙ እንጂ ታጋዮች እርስ በእርስ ተጋጭተው አያውቁምና ሌላ ጨዋታ ቀይሩ ።ሁልጊዜም እምነታችን በግንባር በሚዋደቁት የአማራ ልጆች ትግል ነው።
ከዚህ በተረፈ ዘመነ ካሴ ሊደራደር ነው ።ባህርዳር ሊሾም ነው አስረስ ምርጫ ሊወዳደር ነው ወዘተ እያሉ ማለቃቀስ ለጠላት ግብአት ከመሆን የዘለለ ፋይዳ አይኖረውም ።በነገራችን ላይ እነ አስረስና ጌታ አሰራደ ለአፍሪካ ህብረት የላኩት ደብዳቤ የተዘጋጀው የሚዲያ ካውንስል (የአፋብሃ እጅ ሥራ)በሚባለው የመአዛ መሐመድ ቢሮ ከመሆኑም በላይ አንድነት ለአማራ ህልውና የሚባል እዛው አሜሪካ የተቋቋመ ድርጅት ለህብረቱ መሪዎች ጭፍጨፋውን እንዲያወግዙ የተፃፈውን ከተመለከቱ በኋላ ነው በችኮላ የተዘጋጀው ።መአዛ ምናለበት የአንድነት ሰዎችን እንዲያግዟት እዛው አማክራ ብትፅፈው??
መቼም የዚህ ስብስብ አይን አውጣ ባህሪና የአርበኛ እስክንድር ነጋ ፀሎት ይገርማል ።ቡድኑ አፋህድ ዳውንት ላይ ከአብይ አህመድ ጋር ተደራደረ ብሎ ነጠላ ዜማውን ለአንድ አመት ሲደሰኩር ከርሞ በተቋቋመ በአንድ ወር ውስጥ የባህርዳር ዳር ወንበር ናፈቀኝ የሚል ፈጣጣነት ከየት ይመጣል ።
ለማንኛውም ይህ ሰብስብ ሳይቃጠል በቅጠል በሚባለው የወላጆቻችን ብሂል መሰረት ትግሉን ለእውነተኛ መሪዎች በጊዜ መልቀቅ እንዳለበት ተግባብተን የተናበበ ትግል ማድረግ ካልቻልን ይህ ሁሉ በአሃዝ የማይገለጽ ወንጀል የተፈፀመበትን የአማራ ህዝብ እስከወዲያኛው እንዲጠፋ መደረጉን በአይናችን እያየን ነውና የአማራ ህልውና በሥር ነቀል ለውጥ ብቻ እንደሚመጣ የሚያምን አማራ ሁሉ በውሰጥ የዘመነ ትግል ሻጭ ስብስብ በፊት ለፊት ደግሞ በጦር ሜዳ የገጠመንን ጠላት ተረባርበን ወደ ነፃነት ማማዋ የምኒልክ ከተማ ለመገስገስ እንሰለፍ!
አይናችን እያዬ በሴረኞች የሚጠለፍ የአማራ ትግል የለም።
መልካም ሰኞ
ከአዳባይ
የካቲት 9/ 2018P























