የአማራ ሕዝብ በራሱ አማራዊያን ልጆቹ የሚመራና የሚወከል ታላቅ ሕዝብ ነው

 

ይድረስ ለኤርትራው የሻእቢያ መንግስት

የነገደ አማራን ሕዝብ ነገዳዊ ህልውናን የካደና የኦሮሞ ተወላጅ የሆነውን አንዳርጋቸው ጽጌን የአማራ ሕዝብ ተወካይ ብሎ ለተሰበሰበ ሕዝብ በመድረክ ላይ ማስተዋወቅ በአማራ እና በኤርትራ ሕዝብ መካከል የልዩነት ግንብ መገንባት ማለት ነው

ጋዜጠኛ ወንድወሰን ተክሉ

📌 የሻእቢያ መንግስት ስለምንድነው None Amhara  እና Anti -Amhara  የሆነን ግለሰብ የአማራ ተወካይ ብሎ ሊያስተዋውቅ የፈለገው???

ከሁለት ቀን በፊት አንዳርጋቸው ጽጌ በሱዳን ለተሰበሰበ ሕዝብ ስለጽምዶ መልእክት  ሲያስተላልፍ የሚያሳይ የምስልና ድምጽ ቪዲዮ በማህበራዊ ሚዲያ ሲንሸራሸር ተመልክተናል።

ስብሰባውን ያዘጋጀው የኤርትራ መንግስት ሲሆን ተሰብሳቢዎቹም በሱዳን የሚኖሩ ኤርትራዊያን እና የትግራይ ተወላጆች  የሆኑ ሲሆን ኤርትራዊያኑ የስብሰባው አዘጋጅና መሪ አንዳርጋቸው ጽጌን የአማራ ሕዝብ ተወካይ ብለው ወደ መድረክ በመጥራት ከተሰብሳቢው ጋር ሲያስተዋውቁት አይተናል።

📌 -ለመሆኑ አንዳርጋቸው ጽጌን የአማራ ሕዝብ ተወካይ ያደረገው ማን ነው??? 

አንዳርጋቸው ጽጌን የአማራ ተወካይ የሚያደርግልን የሻእቢያ መንግስት ነውን???

📌- አንዳርጋቸው ጽጌ የአማራ ተወካይ ተብሎ የተነገረው የየትኛው የአማራ ድርጅት መሪ ሆኖ ነው???

📌 -ሲጀመር በየትኛው እሳቤ ነው አንድ ጸረ አማራ ኦሮሞ የአማራ ሕዝብ ተወካይ ተብሎ በድፍረት ሊለፈፍ የተቻለው ???

ለመሆኑ ኤርትራዊው የሻእቢያ መንግስት ከአማራ ሕዝብ ጋር ጦርነት ለመግጠም እራሱን እያማማቀ ነው እንዴ ብድግ ብሎ በአማራ ውስጣዊ ጉዳይ ላይ አንድን ጸረ አማራን አንዳርጋቸው ጽጌ የሚባልን የኦሮሞ ተወላጅን የአማራ ሕዝብ ተወካይ ብሎ የሚያስተዋውቀው ??? ይህ እርምጃ ሻእቢያ የአማራን ሕዝብ ላይ የወረራ ጦርነት ለመክፈት ያሰበበትን እቅድ ያሳየበት እርምጃ ነው ብለን እንቀበለው???

Although አማራው ከኤርትራ ጋር በጠላትነት የምዋጋበት የድንበር ይገባኛል ውዝግብ የለኝም፣ ሻእቢያ as long as  ከብልጽግና ጋር ጠላት እስከሆነ ድረስ አማራው ከሻእቢያ ጋር ታክቲካልና ስትራቴጂካል ትብብርና አጋርነትን መፍጠር ይቻለኛል እያለ በማሰብ ላይ እያለ ባለበት ሁኔታ  የሻእቢያው መንግስት ብድግ ብሎ በአማራ ውስጣዊ ጉዳይ ያገባኛል፣ የአማራንም መሪ የምመርጠው እኔ ነኝ በሚል ነገደ አማራ የሚባል ብሔር የለም፣ እኔ እስከ ሰባት ቤት ቆጥሬ ኦሮሞ ነኝ ብሎ የተናገረን ጸረ አማራን ብድግ አድርጎ  የአማራ ተወካይ ብሎ እንዴት ሊያስተዋውቅ ቻለ ???

መላው የአማራ ሕዝብ እና መላው የፋኖ አደረጃጀት ኤርትራን እና የሻእቢያን መንግስት በጠላትነት  የፈረጀ አይደለም። እንደ ሀገር አማራው ከኤርትራ ጋር የሚጎራበት ሕዝብ እንደመሆኑ መጠን በመካከላችን Cordial የሆነ Relationship መገንባት አለብን ብሎ በጽኑ በሚያምንበት ሰዓት ሻእቢያ ብድግ ብሎ አንዳርጋቸው ጽጌ ነው የአማራ ተወካይ፣ የአማራ መሪ ብሎ ማስተዋወቅና ይህንን እሳቤውን ለመተግበር ማሰብ በሁለቱ ሕዝቦች መካከል – ማለትም በአማራ እና በኤርትራ መካከል የጠላትነት ግንብ መገንባት ማለት ነው።

ነገዳዊ ህልውናውን በክንዱ ታግሎ ለማስከበር  ነፍጥ መዞ እየታገለ ያለው ይህ የዛሬው ትውልድ ከአስመራው ሻእቢያም ሆነ ከባሕር ዳሩ ብአዴንና ከአራት ኪሎው ብልጽግና የሚላክለትን “መሪ”  ተብዬ ምስለኔዎችን  ተቀብሎ የሚሸከምበት ጫንቃ ፈጽሞ የሌለውና እራሱን በራሱ መምራት የሚችል፣ እራሱን በራሱ ለመምራት ቆርጦ የተነሳ ትውልድ ነውና የሻእቢያን ምርጫ አይደለም ታግሶ ለመቀበል ይቅርና ከሻእቢያ ጋር በጋራ ልንሰራ እንችላለን ብሎ ያመነውን ስራዎችን በማቆም ግንኙነቶቹን ሙሉ በሙሉ በመበጠስ በሩን በሻእቢያና በኤርትራዊያን ላይ የሚዘጋ ትውልድ ላይ ነን ያለነው።

When you respect me, i respect you,  ስታከብረኝ፣ አከብርሃለሁ፣ ሳከብርህ ልታከብረኝ ይገባል። እኔ ሳከብርህ አንተ ግን Disrespect በማድረግ ስለእኔ ከእኔ በላይ አውቃለሁ ብለህ በህይወቴ ጣልቃ ለመግባት የምትቃጣ ከሆነ  በእኔ ዘንድ ያለውንና ለአንተ የሰጠሁትን አክብሮት መልሼ በመግፈፍ አንተን እንደ አንድ ወሮበላ intruders በማየትና  በማስተናገድ መብቴን የምጠብቅበትን  ሽመሌን እመዠርጥብሀለሁ ነው የምልህ።

📌  በጽምዶ ጉዳይ ላይ የአማራ ሕዝብ እና የአማራ ፋኖ ግልጽ አቋም!

ጽምዶ ማለት የትግራይ እና የኤርትራ ሕዝብ  የጋራ ጥምረት ወይንም ጥማድ እንደማለት መሆኑን ሲገለጽ ሰምተናል። 

እንደ ሕዝብ- የነገደ አማራ ሕዝብ ፣ ከኤርትራ ሕዝብ፣ ከሱዳን ሕዝብና ከመላው የኢትዮጲያ ሕዝብ ጋር አብሮ ለመስራት፣ አብሮ ለመኖርና አብሮ እርሰበርሱ ግንኙነት ለማድረግ ምንም ችግር የለበትም፣ ኖሮትም አያውቅም።

ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ከእነዚህ ሕዝቦች የፖለቲካ ኤሊቶች ማለትም ከህወት፣ ከሻእቢያ፣ ከብልጽግና እና መሰል  የፖለቲካ ኃይሎች ጋር የሚኖረን ግንኙነት:-

📌 1ኛ-  የአማራ ሕዝብ እና የአማራ ፋኖ ከኤርትራው ሻእቢያ ጋር ለመስራት የማይስችል የመሬት ይገባኛል እና መሰል ውዝግብ የለብንም ብሎ የአማራ ሕዝብና የአማራ ፋኖ ያምናል። As long as  ሻእቢያ አሁን እንደሞከረው ጸረ አማራውን አንዳርጋቸው ጽጌን የአማራ ተወካይ ብሎ ለመጫን አማራን እስካልደፈረ ድረስ፣ የአማራን ውስጣዊን ጉዳይ ለአማራ የመተውን መብት እስካከበረና ከብልጽግና ጋር ወዳጅ እስካልሆነ ድረስ የአማራ ሕዝብና የአማራ ፋኖ ታክቲካልና ስትራቴጂካል ከሻእቢያ ጋር መስራት ይቻላል ብሎ ያስባል።  ይህ ተፈጻሚ ሆኖ ለማየት የሻእቢያ በአማራ ውስጣዊ ጉዳይ ጣልቃ ገብነትና መሪያችሁን የምመርጥላችሁ እኔ ነኝን አካሄድ እርግፍ አድርጎ የእኛን Sovereign Right Respect ማድረግ ይጠበቅበታል።

📌 2ኛ- የአማራ ሕዝብ እና የአማራ ፋኖ ከትግራዪ ህወሃት ጋር ያልጨረስነው የቤት ስራ Unfinished Political Business አለን፣ የመሬት ይገባኛል ውዝግብ አለን፣ ህወሃት በ1967 ማንፌስቶዋ ላይ አማራ ጠላቴ ነው ብላ የፈረጀቺው ፍረጃ እስካሁን ያለና የቀጠለ በመሆኑ ከትግራዪ ህወሃት ጋር መስራትም ሆነ መተባበር አይቻልም ብሎ  ሕዝባችን ያምናል ። 

📌 3ኛ-  የአማራ ሕዝብ ከትግራዪ ህወሃት ጋር መተባበርና አብሮ መሰለፍ አይቻልም ብሎ እያመነ  As long as  ህወሃት በአማራው ላይ በወልቃይት ጠገዴና ራያ ቀጠና ጦርነት እስካልከፈተችብን ድረስ ከህወሃት ጋር ጦርነት ውስጥ መግባት የለብንም ብሎ ያምናል።  

ለምሳሌ  ህወሃት በአማራ ላይ ጦርነት ሳትከፍት ከብልጽግና ጋር ጦርነት ውስጥ ብትገባ አማራው ከብልጽግና ጋር እያደረገ ያለውን ጦርነት ሳያቆም ከብልጽግና ጋር የሚያደርገውን የራሱን የህልውናን ጦርነት ይቀጥላል እንጂ ከብልጽግና ጎን ለጎን ሆኖ በህወሃት ላይ ጦርነት አይከፍትም። ይህ ማለት አማራው በአሁኑ ሰዓት በህወሃት በኩል ጦርነት እስካልተከፈተበት ድረስ በህወሃት ላይ ጦርነት ሳይከፍት ወዳጅም ጠላትም ሳይሆን ገለልተኛ ሆኖ የራሱን ትግል ያሳልጣል ማለት ነው። ይህ እውን መሆን የሚችለው ግን ህወሃት በወልቃይት ጠገዴና ራያ ላይ ጦርነት እስካልከፈተች ግዜ ድረስ ብቻ ነው።

📌 4ኛ- አማራው በጽምዶ ጉዳይ ላይ ያለው ወጥ የሆነ አቃም የሻእቢያ መንግስት as long as  የአማራን Sovereign Power, Right  Respect እስካደረገና ከብልጽግና ጋር ግብግብ ውስጥ ከገባ ህወሃትን ያላካተተ ከኤርትራ መንግስትና ሕዝብ ጋር Cordial የሆነ Relationship መፍጠና መገንባት ይቻላል ብሎ ያምናል።

ከእነዚህ ከላይ ከተጠቀሱት አራት ነጥቦች ውጪ የኤርትራው የሻእቢያ መንግስት የአማራ ተወካይ እና የአማራን መሪ የምወክለውና የምመርጠው እኔ ነኝ ብሎ በእብሪት በአማራው ላይ እንደ አንዳርጋቸው ጽጌ አይነቱን ጸረ አማራ ኦሮሞን በአማራው ላይ ለመጫን የሚጥር ከሆነ በሁለቱ ሕዝብ መካከል የሚለያይ ግንብ የሚገነባ መሆኑን ሕዝባችን ለኤርትራ መንግስት በግልጽ ለማሳወቅ ይወዳል።

ስለሆነም የኤርትራው መንግስት በሱዳን ያደረገውን አንዳርጋቸው ጽጌን የአማራ ተወካይ አድርጎ ያቀረበበትን ሁኔታ ስህተት መሆኑን በመግለጽ ይፋዊ ይቅርታና ማስተካከያ መስጠት አለበት።አበቃሁ።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.