>

አቢዮት ለነጻነት: "ደም ሲፈስ ደም ይግላል!!" (በአምላክ ስሜነህ)

 እምቢ ማለት ከጥንት ከአያት ቅድመ አያቶቻችን የወረስነው፣ የነበረ!! ያለ!! የሚያኮራ የጀግንነት ሙያ ነው!! ትናንት አያት ቅድመ-አያቶቻችን ዘራፍ ወንዱ!! እምቢ ለሃገሬ!! እምቢ!! ለጥቁር አፈሬ!! ባይሉ ኖሮ ዛሬ እኛ ኢትዮጵያዊን የአድዋን የድል በአል ባላከበርን ነበር!!ሲቀጥልም  የአድዋ አኩሪ ገድል ባይፈጸም  ኖሮ የጥቁር ዘር ሁሉ በባርነት ቀምበር ተዘፍቆ እየማቀቀ ሊዘልቅ እንደሚችል የታሪክ ባለሙያዎች ተከራክረዋል።እናም ክብር እነሱ ተሰውተው ለእኛ ዘላለማዊ ህይወትን አውርሰው በወርቃማ የታሪክ ምንጣፍ ላለፉ የአድዋ ጀግኖች!!
ነገርግን አባቶቻችን አውርሰውን ባለፉት የድል እለት የደደቢቱ እና የባንዳ ልጆች ጥርቅሞች፣ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስም ህዝባችን በከፋ የባርነት አዘቅት ውስጥ ከተውና ቀጥቅጠው ለመግዛት!! ሃገሪቱንም ሙሉ በሙሉ ወደ ወታደራዊ አገዛዝ የሚለውጥ ህግ  ዛሬ በፓርላማ አጽድቀዋል።በእርግጥ ከዚህ ቀደምም ቢሆን አገራችን በህወሃት የበላይነት ቁጥጥር  ስር እንደ ነበረች አንዘነጋም።በዚህም የተነሳ አምባ ገነናዊ አገዛዝ  ህዝባችን ለ27 አመታት ያክል በጨለማ ውስጥ ከቶ፣ አማስኖና አባዝኖ!! ገዝቶታል!! በመግዛት ላይም ይገኛል።
ይሁን እንጂ አፓርታይዱን አገዛዝ የኢትዮጵያ ህዝብ ገና ከጅምሩ ጀምሮ አጥብቆ የታገለው ቢሆንም፣በተለይ ከሶስት አመት ወዲህ ደግሞ በተከታታይ፣ ምንም ፋታና መፈናፈኛ በማሳጣት ህዝባችን፣ህወሃትን አጥብቆና አምርሮ እየታገለው ይገኛል!! በዚህ የትግል ሂደትም ከመቼው ጊዜ በላቀ መልኩ የህወሃት ወንበር ርዷል!! ተንቀጥቅጧል!! በአጠቃላይ አገዛዙን ግብ-አተ ቀብሩ ተፋጥኗል!!
ነገግን ህወሃት ከተቀደደለት ከፈን!! ከተፈተለለት መግነዝ እንዲሁም ከተማሰለት የቀብር ጉድጓድ የወጣ መስሎት፣ከሞቀው የነጻነት ትግል ላይ ቀዝቃዛ ውሃ ለመቸለስ፣ከመቼውም ጊዜ በላቀ መልኩ ህዝቡን በመሳሪያ ጸጥ!! ረጭ!! አድርጎ ለመግዛት ወስኗል!!
ልብ ሊባል የሚገባው ጉዳይ ግን ይህ የስድስት ወር የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ህዝቡ ለነጻነቱ የሚያደርገውን ግብግብ በከፍተኛ እልህና ወኔ እንዲሁም ቁጭት ውስጥ ከቶ ትግሉን እንዲፏፏም ያግዘዋል እንጂ፣ የሚንቀለቀለውን ህዝባዊ ትግል ፈጽሞ እፍ!! ብሎ ሊያጠፋው አይችልም!!
ሌላው ጉዳይ ደግሞ የመሳሪያ ክምር!! የሰራዊት ሰልፍ ማሳመር!! የአምባ ገነኖች ድንፋታ!! በዓለም ታሪክ ህዝብን አሸንፎ አያውቅም!! “ደም ሲፈስ ደም ይግላል!! ወንድሞቹን፣ጓደኞቹን፣ወገን ዘመዱን አስገድሎ እንደ ሁልጊዜው አልቅሶና ቀብሮ የሚመለስ ወጣት የለም!!
መሞት ብቻ ሳይሆን መግደል ማለት እንዴት እንደሆነ የዘመኔ ትውልድ ከአገዛዙ ተምሯል!! ትውልዴ አምርሯል!! ጨክኗል!! የጭካኔውን ልክም ጠላቱን ገድሎ፣ ግዳይ ጥሎ ፎክሯል!!  ለዚህ ነው “ደም ሲፈስ ደም ይግላል!!” የሚለውን አባባል የተጠቀምኩበት።
እናም የዘመኔ ትውልድ ሆይ ከህወሃት ምንም አንጠብቅም!! ከዚህ በኋላ ነጻነትን ቆንጥሮና ሰፍሮ የሚሰጠን ማንም አካል የለም!! ትናንት አባቶቻችን እነሱ እየሞቱ ለእኛ ነጻነትን አቀናጅተውን አልፈዋል!! እኛም አገር በቀሉን ፋሽሽታዊ ቡድን አምርረን ለመታገል!! ታግሎም ለመጣል!! ብሎም ከተማሰለት ጉድጓድ ውስጥ ለመጨመር በአንድነት ሆ!! ብለን እንነሳ!!? ተጭበርብሮ ጸደቀ የተባለውን አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ፣ አዋጁ ጸደቀ በተባለ ማግስት  ከየካቲት 26 እስከ የካቲት 28/2010 ዓ.ም የተጣራውን ሁሉን አቀፍ ከቤት ውስጥ ያለመውጣት የተቃውሞ አድማ ተግባራዊ በማድረግ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የነጻነት ትግሉን ፈጽሞ እንደማያስቆመውና የመነመነውን የህወሃት እድሜ እንደ ማይቀጥለው እናሳይ?!!
 ያለን አንድ አገር!! ያለን አንድ ጠላት!! እናም ምንም ያክል ልዩነት ቢኖረንም የልዩ ነታችን ስፋትና ጥልቀት ከሰው ህይወትና ከአገር መፍረስ በፍጹም አይበልጥምና ልክ እንደ አያት ቅድመ አያቶቻችን በአንድነት በህወሃት ላይ ሆ!!…
ብለን በመዝመት፣በመስዋትነታችን ለልጆቻችን ነጻነትን አውርሰን እንለፍ!!
ድል ለኢትዮጵያዊያን
ሞት ለዘረኛው ህወሃት
የኢትዮጵያ ለውጥ ትውልድ ህዝባዊ እምቢይተኝነት አስተባባሪ ግብረ-ሃይል!!
Filed in: Amharic