>

የተኩላዎቹ ዓይነተኛ ኢላማ ሆኖ የቆየዉ የአማራ ሕዝብ ‹‹ አዉሬዉ ወደ ኦሮሞ ዘምቷል›› ብሎ መተኛቱ ዋጋ ያስከፍለዋል!!! (በፍቃዱ ሞረዳ)

የአስቸኳይ ጊዜ ግድያ አዋጅን ‹‹ፓርላማ›› በተባለዉ የእንስሳት ዕድር ዉስጥ ያሉት ‹‹ የአማራና የደቡብ ሕዝብን እንወክላለን›› የሚሉቱ ደግፈዉታል፡፡ ወይም አልተቃወሙትም፡፡

እንዲያ ማድረጋቸዉ በአዋጁ አስፈላጊነት አምነዉ ወይም ከአዋጁ የሚያገኙት የተለየ ጥቅም አማልሏቸዉ ላይሆን ይችላል፡፡ግን በትግርኛ ተናጋሪዎቹ ‹‹እምቧ››ባዮች ለየብቻ አስቀድሞ የተነገራቸዉ ነገር መኖሩ እዉነት ነዉ፡፡በአራዳ ልጆች አባባል፣‹‹ተጀንጅነዋል›› ፡፡
‹‹ ከእናንተ ጋር ሽግር የለንም፤ ሽግራችን ከኦሮሞዎቹ ጋር ነዉ፡፡ ዛሬ ይኼን እየፈላ ያለዉን አዲስ ትዉልድ ከወዲሁ ለእንትኑ ካላኮላሸነዉ ነገ ጣጣዉ ለእናንተ ይተርፋል፡፡ጎርፉ በእናንተም ላይ ይፈስሳል፡፡ ስለዚህ አዋጁን መደገፍ የእኛም የእናንተም ሕልዉና ጉዳይ ነዉ›› ተብለዋል፡፡ በማስፈራሪያና በመደለያ የታገዘ ቅስቀሳ ከአረቄ ቤት እስከ እንቅልፍ ቤት( ፓርላማ) ሲካሄድ እንደነበር መረጃዎች አሉ፡፡
  ሰዎቹ አዋጁን ሲደግፉ ምክንያቱና ትኩረቱ በኦሮሞ ላይ ብቻ እንደሆነ አዉቀዉታል፡፡ በማወቃቸዉም በወያኔ ለተወጠነዉ የዘር ማጥፋት እርምጃ ይፋ እዉቅና ሰጥተዋል፡፡ በእርግጥ ይህ የጥቂት እንትኖች ድጋፍ የመላዉ የአማራና የደቡብ ሕዝብ ድጋፍ መሆን ስላለመሆኑ ዉለን አድረን የምናየዉ ይሆናል፡፡ ማረጋገጫዉም ተግባራዊ የአጋርነት ምላሽ ነዉ፡፡ ልክ የጉራጌ ሕዝብ እያሳየ እንዳለዉ ተግባራዊ የትግል ትብብር፡፡
  ተወደደም ተጠላም ይህ የትግርኛ ተናጋሪ ቀበሮዎችና ተባባሪዎቻቸዉ ዘመቻ የኦሮሞን ሕዝብ ማኅበራዊና (ባሕላዊ) አስተዳደራዊ መዋቅሮችን ከማፍረስ ጀምሮ እየበቀለ ያለዉን የነገ ተስፋ የሆነዉን ትዉልድ የማጥፋት ተልዕኮ ነዉ፡፡ አዋጁን ከተራ የሠላምና ፀጥታ ጉዳይ ጋር ብቻ አያይዞ ማየት የማይቻለዉም ከዚህ ሀቅ በመነሳት ነዉ፡፡
 ለዚህ አዋጅም የሚሰጠዉ ወይም ሊሰጥ የሚገባዉ አፀፋ ትዉልድን ከእልቂት የማዳንና ማንነትን ከጥፋት የመከላከል ሕጋዊም ሞራላዊም እርምጃ ነዉ፡፡
እዚህ ዉስጥ ቢያንስ ሁለት እዉነታዎችን ልብ ማለት የግድ ነዉ፡፡
አንደኛዉ፣ ዛሬ ከዳር ቆሞ የሚመለከተዉና ‹‹ በእኔ እስካልመጣ ድረስ…›› የሚለዉ ወገን ሞኝ እንዳይሆን ማሳሰብ ያስፈልጋል፡፡ ምክንያቱም ተኩላዎቹ ቢያንስ ቢያንስ ለመቶ ዓመት የሀገሪቱን በትረሥልጣን ይዘዉ ያሻቸዉን ሁሉ የማድረግ ዓላማ አላቸዉ፡፡ ይህን ዓላማቸዉን ፍፁም ለማድረግ ደግሞ የተቃወማቸዉን ሁሉ በየተራ ማስገበር ስለሚፈልጉ ልምጩ ለማንም በየተራ የሚቀርለት አይደለም፡፡ ይህ በእዉን ሊሆን እንደሚችል በማወቅ የአማራና የደቡብ ወገኖቻችን ወይ ጀርባችሁን ለኮሪቻ አዘጋጁ፣ አለያም አራት ኪሎ ሳር እየጋጡ ያሉ እንስሶቻችሁን ካዱ፡፡ በእናንተ ስም በተቀመጡበት ወንበር ላይ ሆነዉ በሌላዉ ሕዝብ ላይ የተላለፈዉን የሞት አዋጅ ማስፈፀም የለባቸዉምና፡፡በተለይም ወትሮዉንም የተኩላዎቹ ዓይነተኛ ኢላማ ሆኖ የቆየዉ የአማራ ሕዝብ ‹‹ አዉሬዉ ወደኦሮሞ ዘምቷል›› ብሎ ሁለት ዐይኑን ጨፍኖ ባይተኛ እንላለን፡፡ ያለጥርጥር የሚቀጥለዉ ኢላማ እርሱ ነዉና፡፡ ደግነቱ…
ሁለተኛዉ፣ የተኩላዎቹ እምቡጥ ወጣቶችን የመብላት ዓላማ ከቶዉንም እዉን ሊሆን እንደማይችል የማወቅና የማሳወቅ አስፈላጊነት ነዉ፡፡ ትግሉ ሊረዝም ይችላል፤ መስዋዕትነቱም ይበዛ ይሆናል፡፡ምንም ይሁን ምን  ቄሮ ራሱን ከእልቂት፣ ሀገሩንም ከጥፋት የመከላከልና የማዳን አቅም  አለዉ፡፡ በኢነርጂም፣ በሞራልም ቄሮ ፣ቄሮ ነዉ፡፡ከመላጣዬ ፀጉር ይነቀል፣ ትግሉ አሥርም፣ ሃያም ዓመት ይፍጅ የወያኔ ቀብፀተስፋ ግባተመሬቱ በኦሮሚያ ዉስጥ ይሆናል፡፡
 ምናልባትም ይህ እዉን እስኪሆን ድረስ ከአሁን ወዲያ በኦሮሚያ ዉስጥ የልማት፣የትምህርት…የመሳሰሉ ጉዳዮች አሳሳቢ ላይሆን ይችላል፡፡ የወቅቱ ጥያቄ እንደሕዝብ የመጥፋትና ያለመጥፋት የሕልዉና ጥያቄ ነዉና፡፡ ሀ ፣ ራስን ማዳን፡፡
ማንኛዉም ዋጋ ተከፍሎ የእነዚህ እንትኖች እብሪት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ አደብ መግዛት አለበት፡፡ እንጂ ጥጋብ በወጠራቸዉና በመረቀኑ ቁጥር እየተነሱ በሕዝብ አናት ላይ እየኮሱ መቀጠል ከእንግዲህ አይችሉም፡፡ ትግሉ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተቃዉሞ ባሻገር ነዉ፡፡ ይልቁንስ የሀገርን ነቀርሳ፣ የሀገርን ሸክም… ጨርሶ የመገላገል ፍትሃዊ ፍልሚያ ነዉ፡፡ Vamos a hacerlo!
Filed in: Amharic