>

እንደ ቢዝነስ ኩባንያ ኢሕአዴግ በሚባል ቦርድ የምትተዳደር ብቸኛ «አገር» !?! (አቻምየለህ ታምሩ)

አንድ የቢዝነስ ኮርፖሬሽን የሚመራው በቦርድ ነው። ቦርድ በቀላል አገላለጽ ቡድን ማለት ነው። አገር ደግሞ የሚመራው  በንጉስ፣ በጠቅላይ ሚንስትር ወይንም በፕሬዝደንት ነው። በቤተ ወያኔ ግን  ኢትዮጵያ «የምትመራው» እንደ አገር «በጠቅላይ ሚኒስትር» ሳይሆን እንደ  ቢዝነስ ኮርፖሬሽን «ኢሕአዴግ» በሚባል ቦርድ ነው። በዚህም የተነሳ የወያኔዋ ኢትዮጵያ  እንደ ቢዝነስ ኩባንያ ኢሕአዴግ በሚባል ቦርድ የምትተዳደር ብቸኛ «አገር» ሆናለች ማለት ነው።
ከዛሬ በፊት ባንድ ጹሁፌ ፋሽስት ወያኔ ኢትዮጵያውያንን እየገዛዝ  ያለው በስሩ ለሚተዳደሩ ሰራተኞች ምንም ደንታ እንደሌለው ትርፍ አግበስባሽ የቅኝ ገዢ የንግድ ኩባንያ ነው የሚል ነገር አንስቼ ነበር። እነሆ  ዛሬ እነሱ ራሳቸው ኢትዮጵያን የሚያዩዋት  እንደ ቅኝ ተገዢ የንግድ ኩባንያ እንጂ እንደ አገር አለመሆኑን በቦርድ እንደሚመሯት እየነገሩን ነው።
በቤተ ወያኔ አገር በቦርድ[(በቡድን)ወይንም (በፓርቲ ማዕቀፍ ስር)]አይመራም፤በቦርድ የሚመራው ቢዝነስ ኮርፖሬሽን ብቻ ነው የሚለው ሰሚ የሌለው ለነሱ ኢትዮጵያ አገር ስላልሆነች ነው። የነሱ አገር ከተግባራዊነቱ በመለስ ምንም ያልቀረው የተስፋይፏ ምድራቸው ከመረብ እስከ ባሮ የተዘረጋችዋ ታላቋ የትግራይ ሪፑብሊክ ናት። እነሱ እኛ ጋር ያሉት  በቦርድ የሚመሯትን  ኢትዮጵያ የምትባል  የቢዝነስ ኮርፖሬሽን  አልበው እስኪያነጥፏትና የዘረፉትን ሀብታችንን  የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እያወጁ ወደ ተስፋይቷ ምድራቸው  አጓጉዘው እስኪጨርሱ ድረስ ነው።
_____________
By this post they are also saying, whoever is appointed to the position of the PM, by the Tigrian kleptocrats, he will be another puppet like Hailemariam Dessalegn whether he is Manchurian candidate or  the “Messiah”.
Filed in: Amharic