የኢትዮጵያውያን አሜሪካን ሲቪክ ካውንስል ተወካይ ዲ .ዮሴፍ
HRes128 በሚቀጥለው ወር አፕሪል 9 ወይም አፕሪል 16ኛው ሳምንት ላይ ለድምፅ አሰጣጥ እንደሚቀርብ የኮሎራዶው ተወካይ ማይክ ኮፍመን ዛሬ በላኩት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል። ይህ ለኢትዮጵያኖች ትልቅ ድል ነው ሲሉ ገልፀውታል። ይሁን እንጂ ኮስፖንሰር ያላደረጉ በየስቴቱ ለሚገኙ የአሜሪካ ምክርቤት ተወካዮች መደውላችንን እስከ መጨረሻው መዘንጋት የለብንም ሲሉ ተናግረዋል። እንደሚታወቀው የአሜሪካ መንግስት ለኢትዮጵያ መንግስት የአለም አቀፉ አጣሪ ቡድን እንዲገባ እንዲፈቅዱ የ28 ቀናት ጊዜ ገደብ ሰጥታ ነበር። የአሜሪካ ተሰናባች የውጭ ጉዳይ ስቴት ዲፓርትመንት ሃላፊ ቴሌርሰን በኢትዮጵያ ቆይታቸው ይህንን እንዲያደርጉ እና የጥምር መንግስት በአስቸኮይ እንዲመሰረት መንገራቸውንና ይህ ካልሆነ ግን አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ ያላትን ግንኙነት እንደገና እንደምትመረምር አስጠንቅቀዋቸው ነበር። ይህን ለ Hres128 ለድምፅ መቅረብ ሰነ ስርኣት የውጭ የስቴት ሴክረተሪን በኢትዮጵያ ያደረጉትን ጉብኝት ተከትሎ ያላቸውን ሃሳብ እንዲሰጡ ሲጠበቅ ነበር። በዚህም መሰረት የማጆሪቲው መሪ ኬቨን ማካርቲ የኢትዮጵያን ጉዳይ የሰበአዊ መበት ጥሰት የሚያየውን ረቂቅ ህግ ወደ ድምፅ እንዲቀርብ ዛሬ ወስነዋል።