>

በትግራይ ህዝብ ስም እናመሰግናለን!!! (ወዲ ሻምበል)

እውነት ነው ህወሓት በትግራይ ህዝብ ስም የሚነግድ የጥቂት ማፍያዎች ድርጅት ነው፣ ህወሓት በትግራይ ህዝብ ስም በሌሎች ህዝቦች እና ቢሄሮች ብዙ ወንጀል ሰርተዋል ፣ ህወሓት በትግራይ ህዝብ ስም የአገሪቱን ሃብት ለመዝረፍ እንዲያመቸው ኢፈርት የሚባል ካምፓኒ አቋቁሞ የኢትዮጲያን አንጡራ ሃብት ዘርፈዋል! ህወሓት የትግራይ ህዝብ የቢሄር ጥቃት ይደርስበታል በማለት ለስልጣኑ ማራዘምያ ወታደራዊ ሃይሉን ተጠቅመዋል! በተለይ የኦሮምያን እና የአማራን ቢሄር ተወላጆች ገድለዋል አስረዋል!!! ለቢሄራቸው ጥብቅና የቆሙ በሙሉ ተገድለዋል ታስረዋል ተሰደዋል፣ ያለ ማስረጃ እናንተን አስሮ፣ ደብድቦ፣አሰቃይቶ ቤተሰቦቻች ሁን በትነዋል፣ ይህ በትግራይ ህዝብ ስም የሚፈጸም ወንጀል፣ የሚፈጽመው የትግራይ ህዝብ ሳይሆን፣ ህወሓት መሆኑን ተገንዝባቹ፣ ህወሓትን ከትግራይ ህዝብ ነጥላቹ፣ የግድያ፣ የአፈና፣ የእስራት ተዋናዩ ስርአቱ ህወሓት መሆኑን ለኢትዮጲያ ህዝብ ምስክርነታቹ በመስጠታቹ በትግራይ ህዝብ ስም እናመሰግናለን!!!

ትናንት ከህወሓት ጋር አብረው ሲሰሩ የነበሩ አሁን የትግራይን ህዝብ እንደ ህዝብ የሚጠሉ፣ ትናንት ከህወሓት ጋር ሆኖው እናንተን ሲያሳስሩ አገርን ሲዘርፉ የነበሩ አሁን መልአክ ለመሆን ሲሞኩሩ እኔ እንደ ትግራዋይ ለነሱ አፍራለሁኝ። በጓደኞቻቸው(ህወሓቶች) ታስረው ተደብድበው ሲያበቁ፣ ድብደባው እስራቱ እና ማገላታቱን የፈጸመብን የትግራይ ህዝብ ነው በማለት ደፍረው በአደባባይ ተናግረዋል፣መንጌ ሌባ ሲካፈል እንጂ ሲሰርቅ አይጣላም ነበር ያለው። በዚህም አላቆሙም፣ ጨው ለራስህ ስትል ጣፍጥ በማለት በጽሁፍ አስፍረዋል፣ ጨው የትግራይ ህዝብ መሆኑን ነው!!! ከህወሓት ጋር ሆነው የሰሩትን ወንጀል ለህወሓት ብቻ ትተው ህወሓትን ከመውቀስ ይልቅ የትግራይን ህዝብ ይወቅሳሉ።

እናንተ ትናት በትግራይ ህዝብ ስም በሚነግደው ህወሓት በደል ደርሶባቹ፣ በደሉ ያደረሰብን ህወሓት እንጂ የትግራይ ህዝብ አይደልም በማለታቹ በድጋሚ በትግራይ ህዝብ ስም እናመሰግናለን! የጥላቻ ሳይሆን የፍቅር ትውልድ ለምቅረጽ አልማቹ ሰው በቢሄሩ መጠቃት የለበትም በማለታቹ በትግራይ ህዝብ ስም እናመሰግናለን! የትግራይ ህዝብ ነገ ከምትፈጠረው ኢትዮጲያ ጋር አብሮ እንዲኖር ህዝብን ከገዢ ፓርቲ ጋር ነጥላቹ ስርአቱን በመተቸታቹ ብቻ በትግራይ ህዝብ ስም እናመሰግናለን፣ የነገዋ ኢትዮጲያ የሁላችንን መሆንዋን ምስክርነታቹ በመስጠታቹ አሁንም በትግራይ ህዝብ ስም እናመሰግናለን። ክብር እና ምስጋና የትግራይን ህዝብ እና ህወሓትን ነጥላቹ ለምታዩ ኢትዮጲያውያን በሙሉ።
አክቲቭስት ትግራዋይ ኢትዬጵያዊ ናትናኤል አስመላሽ ፖስት ቢያደርገውም ምድር ላይ ያለው የትግራይ ህዝብ ይደግፈዋ ህወሃት እና አምላኪዎች ግን እንዲሁም ትግራይና ህወሃት አንድ ናቸዉ ለምትሉ አይመለከታችሁም አራት ነጥብ ሳይሆን ሚልዬን ነጥብ።

Filed in: Amharic