>
5:29 pm - Wednesday October 10, 3066

"እስረኛው ሰንደቅ" (ያሬድ ሹመቴ) 

የቄሮን መሬት አንቀጥቅ የፈራው ሁሌም ተሸባሪው ህወሀት የነበቀለን መውጣት እግር ጠብቆ ፖለቲከኞች ጋዜጠኞች እና ብሎገሮችን አፋፍሶ ወደ ማጎሪያው ወስዷቸዋል።
ከአንድ ሳምንት በፊት የጎንደሩ ማርቆስ አብርሐም በኮከብ አልባ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ምክንያት ለእስር መብቃቱን ሰምተን ነበር። ዛሬ ደግሞ ጀግኖቹ ጋዜጠኞችና የነፃነት ታጋዮች በተመሳሳይ ክስ መታሰራቸውን ሰማን። ይህ ነገር “የፖለቲካ ምህዳሩን አሰፋለሁ” ብሎ የፖለቲካ እስረኞችን የለቀቀን መንግስት ባህሪ በጉልህ የሚያሳይ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።
የፒለቲካ ምህዳር “ለማስፋት” በሚል ምክንያት ለረዥም ግዜ ሲገዘትበት የነበረውን “የፖለቲካ እስረኛ የለም” የሚል አቋም ቀይሮ (ተሸንፎ ማለትም ይቻላል) እስረኞቹን ፈትቷል። በዚህም የ’ታጋሽነት’ ባህሪ ያመጣ መስሎን፤ የንፁሐኑንም መፈታት ምክንያት አድርገን ደስታችንን ገልፀን ነበር። ያሁኑ እስር ያሳየን ምስጢር ቢኖር ግን ሰንደቅ አላማው ከፍተኛ የማስጨነቅ አቅም ያለው መሆኑን ነው።
“በጥልቅ ታድሼ ተፀጽቻለሁ” ብሎን የነበረው መንግስት በዚህ ጉዳይ ግን ወደ ቀደመ ግብሩ መመለሱ የሰንደቁን ኃይል የሚያሳይ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።
ጣሊያን በ1928 ኢትዮጵያን ለሁለተኛ ግዜ በወረረበት ሙከራው ወቅት ትልቁ የሚፈራው ምልክት የኢትዮጵያን ሰንደቅ እና የዳግማዊ አፄ ምኒልክን ምስል ነበር። በዚህም ምክንያት አዲስ አበባ አራዳ የሚገኘውን የዳግማዊ አፄ ምኒልክ ኃውልት ከቦታው ነቅሎ መቅበሩን በታሪክ እናውቃለን። ከነፃነት በኋላ ግን የዳግማዊ አፄ ምኒልክ ኃውልት ወደ ቦታው በክብር ሊመለስ ችሏል።
ይህ የአሁኑ አካሔድ የዚህ አምሳያው የሆነ ያህል ተሰምቶኛል። አሳሪዎቹ አርቀው ማየት አልቻሉም እንጂ አይያዛቸው፤ መጪው ምኞት ሰንደቁን ወደ ቦታው የመመለስ ስለመሆኑ መገመት አይቸግርም።
ማርቆስ የሀገር ፍቅር ስሜት ያነዘረው ሰው መሆኑን መስክረን፤ ‘እባካችሁ ፍቱልን’ እያልን መለመናችንን ሳናቆም፤ የዛሬውን እስር ሰማን። በጣም ያሳዝናል። ዛሬም ስለ ሁሉም እንማልዳለን። እባካችሁ ሰንደቁን ፍቱልን።
ሁለትም ሦስትም ሆናችሁ በተሰበሰባችሁበት እኔ አለሁ ባዩ ኮማንድ ፖስት በቅርብ ተፈተው  ከቤተሰቦቻቸው  ጋር የተቀላቀሉትን ጋዜጠኞች ÷ የለውጥ አራማጆችንና ፖለቲከኞችን ያለኔ ፍቃድ በኢትዮጵያ ሰንደቅ ስር ሊያውም በኮከ እልባው ባንዲራ ስር ስለምን ተሰባሰባችሁ ብሎ ካሰራቸው ውስጥ፦
1) ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ
2) ጋዜጠኛ ፍቃዱ ማህተመ ወርቅ
3)ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ
4) አቶ አንዱዓለም አራጌ
5) አቶ አዲሱ ጌታነህ
6) ጦማሪ ዘላለም ወርቅ አገኘሁ
7) ጦማሪ ማህሌት ፋንታሁን
8) ጦማሪና ጋዜጠኛ በፍቃዱ ኃይሉ
9) ወይንሸት ሞላ
10) ይድነቃቸው አዲስ
11) ስንታየሁ ቸኮል
12) ተፈራ ተስፋዬ
በምጥ ላይ ያለ ገዢ ሥርዓት የሚችለው ይቺን ብቻ ነው፡፡
Filed in: Amharic