>

ኢትዮጵያን እየገዛ ያለው ከፋሽስት ጥሊያን የከፋ ጨካኝ አውሬ አይደለምን? (አቻምየለህ ታምሩ)

የተከዘ ማዶ የሙሶሎኒ ርዝራዦች በኢትዮጵያ ምድር የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ   ያውለበለቡ ጀግኖችን  ሲያስገድሉና ሊያንገላቱ  ትናንትና በነ እስክንድር ነጋና በነ ተመስገን ደሳለኝ  ላይ የሆነው የመጀመሪያ አይደለም።
ከሁለት አመት በፊት  «ለእውነት የተሰዋው ሰማዕት» በሚል ርዕስ በ2004 ዓ.ም.የታተመ የአበበ ይርጉን  መጽሐፍ  ማንበቤ ትዝ ይለኛል። መጽሐፉ  በሳይንቲስት ዶክተር ዳኛቸው ይርጉ የሕይወት ታሪክና  በሊቁን የሕይወት ፍጻሜ ዙሪያ በወንድሉ  የተደረገ ክትትል ውጤት ነው። የመጽሀፉ ደራሲ አበበ ይርጉ የዶክተር ዳኛቸው ይርጉ ታናሽ ወንድም እንደሆነ ይናገራል። አበበ ይርጉ የዶክተር ዳኛቸውን ታሪክ ማውሳት ከመጀመሩ በፊት ስለ አባታቸው ስለ ልጅ ይርጉ ወንድም ተገኝ ታሪክና የአርበኛነት ተጋድሎ ያወራል።
የስመ ጥሩ ሳይንቲስት የዶክተር ዳኛቸው ይርጉ አባት ልጅ  ይርጉ ወንድም ተገኝ በሸዋ የታወቁ አርበኛ ነበሩ።  በትውልድ አካባቢያቸው በአዲስ አለም እየኖሩ ቀን፣ ቀን በግብርና ተሰማርተው ይውሉና  ሌሊቱን   ከአርበኞች ጋር በመገናኝት የጸረ ፋሽስት ትግሉ የሚያስፈልገውን ትጥቅ፣ ስንቅና መረጃ  ያቀርቡ ነበር።
ጥሊያን አዲስ አበባን እንደተቆጣጠረ አዲስ አለም ከተማን መቀመጫው አድርጎ ወረዳውን እንዲያስተዳደር በፋሽስት  የተሾመው የጥሊያን ባሻ ወልደ ኪሮስ የሚባል የትግራይ ባንዳ ነበር።  ባሻ ወልደ ኪሮስ  ልጅ  ይርጉ ወንድም ተገኝን በሆለት ገነር፣ በአምቦና በባካ ከተማ ለረጅም ጊዜ እንዲታሰሩ ያደረገ ወደር የሌለው ባንዳ ነበር።  ባሻ ወልደ ኪሮስ  ልጅ  ይርጉ  ወንድም ተገኝን  በጥሊያኖች ችሎት ፊት ከሶ እንዲቀጧቸው የጠየቀባቸው  የሞት ፍርድ ነበር። የልጅ ይርጉን ጉዳን ለማስቻል በተዘረጋው የፋሽስት ጥሊያን ችሎት  ክርክሩ የተካሄደው በከሳሽ ባሻ ወልደ ኪሮስና በተከሳሽ ይርጉ ወንድም ተገኝ መካከል ነበር። ባሻ ወልደ ኪሮስ በልጅ ይርጉ ወንድም ተገኝ ላይ ጥሊያኖች እንዲያስተላልፉ የጠየቀው ውሳኔ የሞት ቅጣት ነበር ብያለሁ። አስገራሚው ነገር ባሻ ወልደ ኪሮስ ጥሊያኖች በልጅ ይርጉ ወንድም ተገኝ ላይ የሞት ቅጣት እንዲወስኑባቸው ፈጽመውታል ብሎ ያቀረበው «ወንጀል» ነው።
ባሻ ወልደ ኪሮስ ፋሽስት ጥሊያን በልጅ ይርጉ ወንድም ተገኝ ላይ የሞት ቅጣት እንዲፈጸምባቸው ያቀረበው  ክስ  « በሰላዮቼ እንዳረጋገጥሁት  በይርጉ ወንድ ተገኝ ቅጥር ጊቢ  ውስጥ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አለማ  ሲውለበለብ ተገኝቷል» የሚል ነበር። ይህንን ባሻ ወልደ ኪሮስ በልጅ ይርጉ ላይ ያቀረበውን  የግፍ ክስ  የሰሙት ጥሊያኖች  ተገርመው «ይርጉ ወንድም ተገኝ የአገሩን ሰንደቅ አለማ በማውለብለቡ የሞት ቅጣት አንፈርድበትም» በማለት  የቅጣት ማቅለያ አድርገውላቸው   የተጠየቀባቸውን የሞት ቅጣቱ ወደ እስር  ለውጠውላቸው  መጀመሪያ በሆለታ፣ ቀጥሎም  ደግሞ በአምቦና በባካ ታሰሩ።
በአምስቱ አመቱ   የፋሽስት ወረራ ዘመን  እልቆ ቢስ የኢትዮጵያ አርበኞች በባንዳ የተከዘ ማዶ የጥሊያን አገልጋዮች እየታነቁ የተገደሉትና የታሰሩት በግቢያችሁ ኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ ስታውለበልቡ ተገኝታችኋል እየተባሉ ነበር። ዛሬም  እየሆነ ያለው ይሄው ነው። የግራዚያኒ አገልጋይ የነበሩ ባንዶች የወለዷቸው ፋሽስት ወያኔዎች ዛሬ እያሰሩን ያሉት ጀግኖች አባቶቻችን ከባንዶች አባቶቻቸው ጋር  የተፋለሙበትን  የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ለምን ተውለበለበት እያሉ ነው።
ሰው ለማጥቃት የሰለጠኑት  የትግራይ ወታደሮች የሚያንገላቱት የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ የኢትዮጵያን ዳር ድንበር ለማስጠበቅ የዘመቱ የኢትዮጵያ ጀግኖች ሁሉ የተዋደቁለት  የኢትዮጵያ አርበኞች ምልክት  ነው። እነ ተመስገንና እስክንድር የታሰሩበት የኢትዮጵያ ሰንደው አላማ የረጅም ጊዜው ይቅርና በቅርቡ ከ20 ዓመት በፊት ፋሽስት ወያኔና የመንፈስ አባቱ ሻዕብያ የበላይነትና የበታችነት ጦርነት ባደረጉ ጊዜም የተውለበለበ ብቸኛ ሰንደቅ አላማ ነው። ልብ በሉ! በዚህ የሁለቱ የኢትዮጵያ ጠላቶች ጦርነት ወቅት ከ80 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች አልቀዋል።  ዛሬ የትግራይ ወታደሮች እንዳይውለበለብ የሚከለክሉን   የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ባድመ ላይ ሳይቀር የረገፉት 80ሺህ ወጣቶች እያውለበለቡት የተዋደቀለትን ሰንደቅ አላማ ነው።
ወያኔ  የትግራይ ሪፑብሊክን ለመመስረት ከኢትዮጵያ ጋር ሲዋጋ  60 ሺህ የትግራይ  ወጣት እንደገበረ ደጋግሞ ነግሮናል። በፋሽስት ወያኔዋ ኢትዮጵያ ግን ኢትዮጵያ በማፍረስ የታላቋን ትግራይ ሪፑብሊክ ለመመስረት የታገለው ወያኔ ከራሺያና ከቻይና የኮምኒስት ምልክቶች አውጣጥቶ የደረተው የባዕድ ባንዲራ ሕጋዊ ሆኖ ባድመ ላይ  ሳይቀር ወያኔ የትግራይን  ሪፑብሊክን ለመመስረት ከኢትዮጵያ ጋር ሲዋጋ  ገበርሁት ከሚለው ወጣት በላይ በላይ የሚሆን 80 ሺህ ወጣት ዳር ድንበር ለማስከበር የተዋደቀበትን የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ግን ኢትዮጵያ ውስጥ ማውለብለብ ወንጀል ነው። ሌላው ቢቀር እነሱ የትግራይ ዳር ድንበር ተደፍሯል ብለው የኢትዮጵያን ወጣት ቀስቅሰው 80 ሺህ ወጣት ባድመ ላይ በማገዱበት የጦርነት አውድማ ላይ እንኳ የተውለበለበውን ሰንደቅ አላማ በኢትዮጵያ ምድር ማውለብለብን ወንጀል ያደረጉ ምን አይነት ጉዶች ናቸው?
ዛሬ እነ እስክንድርና ተመስገን የታሰሩበት የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ትናንትና እነ ደጃዝማች ገረሱ ዱኪ ከፍ አድርገው እያውለበለቡ ከፋሽት ጥሊያን ጋር የተፋለሙበት የጀግኖች አርማ ነው። ትናንትና  እነ ደጃዝማች ገረሱ ዲኪ፣ እነ ደጃዝማች በላይ ዘለቀ፣ እነ ጀኔራል ጃገማ ኬሎና እልቆ መሳፍርት የኢትዮጵያ ጀግኖች የተዋደቁለትን የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ዛሬ በወያኔዋ ኢትዮጵያ ማውለብለብ ወንጀል ነው።  ቁጣችንን ማወቅ አለብን። ትናንት እነ ደጃዝማች ገረሱ ዲኪ፣ ደጃዝማች በላይ ዘለቀ፣ ጀኔራል ጃገማ ኬሎና እልቆ መሳፍርት የኢትዮጵያ ጀግኖች የተዋደቁለት  የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳይውለበለብ ከታገደ ያለነው በፋሽት ጥሊያን ወረራ ውስጥ ነው ማለት ነው። ዛሬ እየኖርን ያለነው ከዚህ በተለየ ሁኔታ አይደለም። ለነገሩ እነሱ እኛ ጋር ያሉት በቦርድ የሚመሯትን ኢትዮጵያ የምትባል የቢዝነስ ኮርፖሬሽን አልበው እስኪያነጥፏትና የዘረፉትን ሀብታችንን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እያወጁ ወደ ተስፋይቷ ምድራቸው አጓጉዘው እስኪጨርሱ ድረስ  ብቻ ነው እንጂ ወራሪነታቸውንና ኢትዮጵያንም  እንደ ቅኝ ግዛት ኩባንያ እንደሚያዩዋት ስተውት አያውቁም።
ከታች የታተሙት ሁለት ፎቶዎች  የጸረ ፋሽስቱ አርበኛ የገረሱ ዱኪ ሰራዊት የኦሞን ወንዝ በእግሩ ሲያቋርጥ የሚያሳዩ ናቸው። በፎቶዎቹ ላይ እንደሚታየው የደጃዝማች ገረሱ ዱኪ ሰራዊት ፋሽስትን ለመፋለም የኦሞን ወንዝ ሲያቋርጥ እነተመስገንና እስክንድር  በማውለብለባቸው የታሰሩበትን የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ተሸክሟል። በተንቀሳቃሽ ምስሉ ላይ የሚታዩት  ደግሞ ታላቁ ጀግና ራስ አበበ አረጋይና  አብረዋቸው የተሰለፉት አርበኞች ናቸው። በተንቀሳቃሽ ምስሉ ላይ እንደሚታየው በራስ አበበ አበረጋይ የሚመራው የኢትዮጵያ ጀግና አርበኞች ከፋሽስት ነፃ ባወጡት ምድር እነተመስገንና እስክንድር  በማውለብለባቸው የታሰሩበትን የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ያውለበልባሉ።
እንግዲህ! በወያኔዋ ኢትዮጵያ እንዳናውለበልብ የተከለከልነው በፋሽስት ጥሊያን ዘመን  ሳይቀር በአርበኞቻችን ተጋድሎ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ የተደረገውን የጀግኖች አንደቅ አላማ ነው!
Filed in: Amharic