>

በአሲድ የተቃጠለችው ወጣት "የፍትህ ያለህ!?" ትላለች (አርአያ ተስፋ ማርያም)

አፀደ ትባላለች። አገር ቤት የምትኖረው ይህቺ ወጣት ዘግናኝ ግፍ እንደተፈፀመባት በሚዲያ ቀርባ እንባዋን እያፈሰሰች ተናግራለች። ልጅ የወለድችለት ጨካኝ አረመኔ አሲድ ደፍቶባት ከፊቷ መበላሸት ባሻገር አንድ ጆሮዋ የለም። ፊስቡክ ላይ ድርጊቱ ይፋ ከተደረገ በኋላ ይህ ጨካኝ “እሰይ” እያለ እንደሚፅፍ የገለፀችው አፀደ “እባካችሁ ያዙትና ለፍርድ አቅርቡልን” እያለች የስልክ አድራሻውን ጭምር በማያያዝ እሷና ቤተሰቧ ፖሊስን ቢጠይቁና ቢመላለሱም “የእኛን ስራ እናንተ አትነግሩንም” እያሉ ተስፋ አስቆራጭ መልስ እንደሰጧቸው እያለቀሰች ተናግራለች። በህግ አምላክ!..ወንጀለኛው በህግ ይጠየቅ!..የሴቶች ጉዳይና የሚመለከታቸው አካላት ለምን ዝም አሉ!?..ጎዝበ ይህን ጭካኔ ምን ይሉታል!??.በእውነት ያማል!!ፍትህ ለዝች ወጣት! (ፎቶው ልጅቷ ራሷ የለቀቀችው ነው)
Filed in: Amharic