>
5:18 pm - Tuesday June 15, 8562

ለመስማት ቀርቶ ለማየት የሚዘገንኑ ወንጀለኛ ባለስልጣናትን ተሸክሞ የለዉጥ ጉዞ አይታሰብም!?! (ተክሌ ደስታ)

• አቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝ በቀድሞዉ ጠሚ ጫማ የተሰፈሩ ባለስልጣን ነበሩ፡፡ጫማዉ ሰፍቷቸዉም ይሁን ጠብቧቸዉ ሳያምርባቸዉ በተፈጠረዉ ቀዉስ አቅም አጥተዉ/አሳጥተዋቸዉ ከስልጣናቸዉ ወረዱ፡፡ያለፈዉን የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ አዉጥተዉ በህዝባቸዉ ላይ ጦርነት በማሳወጅ በርካታ ንፁሃን ዜጎችን አሳስረዋል፤አስገድለዋል፤አሰድደዋል፤አካለ ጎዶሎ አስደርገዋል፡፡ፓርቲያቸዉና እሳቸዉ ተጠያቂ እንደሆኑ አሁን ሁለተኛዉን አዋጅ “በኔ መሪነት አላሳዉጅም’ በሚል መልኩ ሁለተኛዉ የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ሲታወጅ ቢያንስ በመሪነት የሉበትም፡፡ድፍረቱ ካላቸዉ ነገ የሚሉንን የምንሰማዉ ቢሆንም ከዚህኛዉ ሰቆቃ እንደመሪ የለሁበትም ያሉ ይመስላል፡፡
• በቅርቡ በዚሁ ቤተ መንግስት የበኩር ልጃቸዉን እንደዳሩ ሰምተናል፡፡ያኔ እንደ ከትናንት በስቲያዉ የስልጣን ሽግሽግ ሲፍነከነኩ አልታዩም፡፡ኮትኩተዉ ያሳደጉት ሰዉ ስልጣን ስለተረከባቸዉ፤አለያም “የሚወዷት” ሃገራቸዉ በታሪክ ለመጀመሪያ ግዜ ዲሚክራሲያዊ ምርጫ አካሂዳ ከአንዱ ፓርቲ ወደ ሌላዉ ፓርቲ አለያም ከአንዱ ርእዮተ-አለም ወደ ሌለዉ ሽግግር ስለተደረገ አይደለም፡፡ይልቅስ የስልጣን ሽግሽጉ ከገቡበት ማጥ እንዳወጣቸዉ ያሳብቅባቸዉ ነበር፡፡እዚህ ቅርቃር ዉስጥ የከተትዋቸዉ የቀድሞዉ “ታላቁ መሪያቸዉ” እና አሁንም በህይወት እዛዉ ቦታ ያሉት ባለስልጣኖች ነበሩ፡፡እዚህ ቅርቃር ዉስጥ የከተታቸዉ ድርጅትና ሌሎች ባለስልጣኖች ዛሬም ዶ/ር አብይ አህመድ አጠገብ መኖራቸዉ ሌላዉ ቀጣይ ችግር ለመሆኑ  ከፊት የሚታይ እዉነት ይመስላል፡፡
• ዶ/ር አብይ አህመድ ህዝቡ ባደረገዉ ትግል፤ህወሓት/ኢህአዴግ ላይ በደረሰ ጫና በዉስጥ ትግል ወደዚህ የስልጣን እርከን በራሳቸዉና በተገኙበት ድርጅት በሌሎችም ድጋፍ እንደመጡ ግልፅ ነዉ፡፡የህዝቡ ትግል አሁንም እየተፍለቀለቀ ነዉ፡፡የተዳፈነ እሳተ ጎመራ ነዉ፡፡መልስ አላገኘም፡፡የአቶ ኃ/ማርያም ከስልጣን መዉረድ የዶ/ር አብይ አህመድ ወይ ሌላ ሰዉ ወደ ስልጣን መዉጣት ጥያቄ ዉስጥ ገብቶ አያዉቅም፡፡እናም ወደ ስልጣን መጥተዉ እርካቡን ሲጨብጡ ይሉኝታና ዉለታ ያለባቸዉ አይመስልም፡፡ካለባቸዉ ከወደ አቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝ ና ትቂጥ “ጓዶቻቸዉ” ሊሆን ይችል ይሆናል፡፡ከጎናቸዉ ቁመናል የሚሉት አሜሪካኖችም ሆነ ቅርብ የፓርቲያቸዉ ሰዎች ስር- ነቀል የዉስጥ ለዉጥ ይፈልጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
• የአቶ ኃ/ማርያም ዉለታና ይሉኝታ ተፅእኖ ፈጥሮባቸዉ በእጃቸዉ ያለዉን ስልጣን አሳልፈዉ ከሰጡ ተአማኒነታቸዉ መሸርሸር ይጀምራል፡፡በግንባሩ ለተለመደዉ የብሄር ተዋፅኦ የሚቸገሩ አይመስለኘም፡፡አንደኛ በድርጅቱ ዉሰኔ መሰረት ብቃት የመይፈለግ ከሆነ ማመጣጠን ይኖርባቸዋል፡፡ለዚህ የሚመጥን አዳዲስ ሰዎችንም የሚያጡ አይሆንም፡፡ስለሆነም የኃ/ማርያምን ከብኔ ቀይጦ መምጣት ከህዝብ ጋር ተስፋን ማሳጣት አንዱ ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡አቶ ኃ/ማርያምን ያልደገፈ ካብኔ፤አገሪቱ ለሁለተኛ ግዜ በአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ስር እንድትወድቅና ለታጠቀ ሃይል ራሱንና ህዝቡን አሳልፎ የሰጠ ከብኔ የአዲሱ ካብኔ ኣባል ከሆነ የቃሉ መሸርሸር መጀመሪያ ይሆናል የሚል ስጋት በብዙዎች ይታያል፡፡
• በእዉነትም አቶ ኃ/ማርያም ሲሰበስቡ ሲበትኑት የኖረዉ ካብኔ ሁሉ “የታላቁ መሪያቸዉ” ተቀጥላ በመሆኑ የህዝቡ ጥላቻ ቢቀጥል የሚፈረድበት አይሆንም፡፡ለብዙዉ ሰዉ ለመስማት ቀርቶ ለማየት የሚዘገንኑ ወንጀለኛ ባለስልጣናትን ተሸክሞ የለዉጥ ጉዞን መቀጠል ይቻላል ብሎ ማሰብ የዋህነት ይሆናል፡፡
Filed in: Amharic