>

ዶ/ር አብይ ስልጣኑን ሳይሸራርፍ በመጠቀም ወያኔ የምትባለዋን በግ ፀጉሯን መሸለት ሳይሆን ቆዳዋን መግፈፍ አለበት! (ቬሮኒካ መላኩ)

ከሁለተኛው የአለም ጦርነት በኋላ የአሜሪካ ፕሬዚደንት የነበረው ድዋይት አይዘንሀወር  ፖለቲካን Dirty game ( ቆሻሻ ጨዋታ) በማለት ይጠራው ነበር  ። አይዘንሀወር ፖለቲካን በዚህ መጠሪያ የጠራው በጊዜው የነበረው የፖለቲካ  ተለዋዋጭነት አስቸጋሪነት በተጋፈጠበት ወቅት ነበር ።
ይሄን “Dirty game ” የሚለውን ሀይለ ቃል ዛሬ እኛ ኢትዮጵያውያን የተጋፈጥነው ይመስለኛል።
የኢትዮጵያም ፖለቲካ እንደ አየሩ ፀባይ እየተቀያየረና  እየተለዋወጠ ” Dirty game “እየሆነ  ነው። አሁን እንደምንመለከተው ወያኔ በአብይ አህመድ አማካኝነት የባሪያ ምልመላ ላይ ነች።ወያኔ በታላቅ ትራጀዲና በህይወት አውሎ ነፋስ በምትናወጥበት ሰአት የአብይ ወርቃማ ንግግር ትንፋሿን ለመቀጠል ችሏል። በለውጥ ማእበል ሲንተከተክ የከረመው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ለጊዜውም ቢሆን ረግቷል።
አብይ አህመድ ምን ማድረግ አለበት?  
1~አቢይ አህመድ አሁን ፈረንጆቹ እንደሚሉት የመሪነት ስነልቡናን  statemanship መሸከም አለበት እንጅ “politician “የፖለቲካ ሰውነት አይጠቅመውም።
2~በዚህም መሰረት አብይ የራሱን ታሪክ መፃፍ ከፈለገ  በህገመንግስቱ አንቀፅ 74 ከንኡስ አንቀፅ 1 እስከ ንኡስ አንቀፅ 13 የተሰጠውን ስልጣን ሳይሸራርፍ በመጠቀም ወያኔ የምትባለዋን በግ ፀጉሯን መሸለት ሳይሆን ቆዳዋን መግፈፍ አለበት።
 እንደ የጦር ሀይሎች ጠቅላይ አዛዥነቱ የጨረጨሰውን፣ የሻገተውንና የጡረታ ጊዜው ከአመታት በፊት ያለፈውን  ሳሞራ የኑስን በቀጭን ትእዛዝ ጡረታ ማስወጣት ።
..
3~በአማካሪነት ስም ሀይለማሪያም ደሳለኝን ተብትበው ትግሪኛ ሲያስጨፍሩት የከረሙትን ሽማግሌዎች መበተን።  4~ካቤኔውን ፐውዞ የራሱን አዲስ ካቤኔ ማዋቀር።
 አቢይ ይሄን ወሳኝ ምእራፍ ለመግለጥ እንደ ተኩላ ብልጥ እንደ አንበሳ ደፋር መሆን አለበት ትከሻውንም  ግማደ መስቀሉን ከነመከራው ለመሸከም የተዘጋጀ መሆን አለበት። ይሄ የጨዋታው ህግ ነው ። አብይ አህመድ በፍጥነት ቀልጠፍ ብሎ  ጨዋታውን ካልቀየረው ወደ ታች በመስጠም ላይ ካለችው ወያኔ ከምትባለው ጀልባ ጋር  አብሮ  መስጠሙ አይቀርም።
Filed in: Amharic