>
5:21 pm - Thursday July 21, 8760

ሰላይ ማለት ምን ማለት ነው ?የስለላ ስራስ መቼ ተጀመረ? (ሔቨን ዮሐንስ)

ጸላዕኩ ማኀበረ እኩያን ፦ ፳፭ ፥ ፭
የክፋዎችን ማኀበር ጠላሁ ፦ መዝ 25 ፥5
ሰላም ለእናንተ ይሁን ። በፆም ምክንያት ያው ትንሽ ከአለማዊ ፁሁፍ ራቅ ብየ ነበር ።የነፍስ ምግብ ይቀድማል በማለት ነው ። ይቺን ፁሁፍ መጨረሻዋ ድረስ አንብባችሁ አስተያየታችሁን አስቀምጡ ።
የመፅሀፍ ሁሉ እራስ መፅሀፍ ቅዱስ ነው ። መፅሀፍ ቅዱስ ላይ አንዱ የፃፈው አንዱን ያግዘዋል ።ወንጌላዊ ዮሐንስ የማቴዎስን ያጠናክረዋል ። ማቴዎስ ማርቆስ ያጠናክረዋል ማርቆስን ዮሐንስ ያጠናክረዋል ሉቃስን ማርቆስ ማቴዎስ ዮሐንስ ያጠናክሩታል እንጂ አንዱ ከአንዱ አይፋለስም ። ብሉይ ኪዳን ላይ ያሉ ትንቢቶች ሀድስ ኪዳን ላይ ተተግብረዋል ።ሀድስ ኪዳን ላይ ሆነው ብሉይ ኪዳን ላይ የነበረውን በራዕይ ያዩት ነበር ። እንድህ እያለ እውነትን ተማርን ። የእውነት እውነት የፍቅር ፍቅር እግዚአብሔር ነውና
እውነት እውነቱን እንነጋገር ።
አባታችን ኖህ በሰራው መርከብ ላይ ሆኖ ከጥፋት ውሃ ከመረጣቸው እንስሳዎችና ልጆቹ ጋር ከመጥፋት በእግዚአብሔር ፍቃድና ትዛዝ ድኗል ። ነገር ግን ለእግዚአብሔር አልታዘዝ ያሉ ጠፍተዋል ። ኖህ ያንን ጥፋት መብረዱን ማቆሙን እንድሰልልለት ቁራን ላከው ። ቁራ ለስለላ ከተላከበት ሄዶ ሳይመለስ ቀረ ። የቀረበት ምክንያት የሞቱትን እየበላ በቃ ሰፊ መና አገኘሁ ብሎ ትዛዙን ሰረዘ ።
አባታችን ኖህም ሲቀርበት እርግብን ላካት ። እርግባ ግን ስለላዋን በሚገባ ተወጥታ በአፏ ቀጤማን ቆርጣ ይዛ መጣች ። ሰላም ነው ሀገሩ ተረጋግቷል ስትል ነው ። ጥፋቱ ቆሞ እፅዋቶችን እያበቀለ እንደሆነ አበሰረችው ።
አባታችን ሙሴ እስራኤሎችን ከግብፅ ይዞ ወደ ከነአን ሲጓዝ ብዙ ፈተናዎን ያስተናግድ ነበር ። ያቺን የተስፋይቱን ምድር እየናፈቀ የሚመራቸውን ህዝቦች ይዞ ጉዞን ሲቀጥል ከፊቱ ያለችውን ሀገር ሰልለው እንድመጡ 12 አስራ ሁለት ሰዎችን መርጦ ላከ ። አስራ ሁለቱም ሰልለው መጡ ። አስሩ ለሙሴና ለህዝቡ የተናገሩት ያስፈራና ያስጨንቅ ነበር ። ይቺ ሀገር ጎበዞች የበዙባት ጦረኞች ያሏት አስፈሪ ናት ። በቃ አንችላቸውም አንተርፋምም አሉ ። ህዝቡ በጣም ጮሁ ሙሴን አንተ ሙሴ አሉት በግብፅ የመቃብር ስፍራ አጥተናል እንደ አሉት። እርስ በእራሳቸው አለቃ ተመራርጠው ወደ ግብፅ ሊመለሱ ወሰኑ ። ሙሴም ግራ ተጋባና በጣም አዘነ ። ይህንን ሁሉ መንገድ ተጉዘን እንደት ለመመለስ ይወስናሉ በማለት ነበር ። ከአስራ ሁለቱ አስሩ ሽብርን ሲለቁ ሁለቱ ግን ህዝቡን እየዞሩ አረጋጉ ። ያቺ ሀገር ሰላም ናት ።እዩ የወይን ፍሬን ብለው የያዙትን የወይን ፍሬን አሳዩአቸው ። ደስ የምትል ሀገርም ናት ።ብዙ መናን የያዘች የማትሰለች ሀገር ናት አሉ ። እግዚአብሔር ቢወድስ እዚህ ያደረሰንል አይችሉንም አሸንፈን የተስፋይቱን ምድር ማርና ወተት የሚፈልቁባትን እንወርሳለን። ስለዚህ ተረጋጉ ብለው ህዝቡን አረጋጉ። አስሩን ምድር ተከፍታ ዋጠቻቸው ። ህዝቡም ከሙሴ ጋር ታርቀው ጉዞ ቀጠሉ ።
ነገርን ነገር ያነሳዋል እንደተባለው ለምሳሌ ያህል ከመፅሀፍ ቅዱስ የወሰድናቸው ሰላዮች የቁራ መላክተኛ የከዳተኛ ሰላይ አለ ።የሰላም ዘማሪ ደግና ታማኝ እርግብን አየን ።ሙሴ ከላካቸው ሰዎች  የሀሰት ሰላዮች  አስሩን ምድር ተከፍታ ዋጠቻቸው ። ውሸታቸው ተንኮላቸው ለግዜው ሰውን ቢረብሽም በመልካሞቹ ውሸታቸው ተሸነፈ እነሱም ጠፋ። ስለ እውነት ስለ እግዚአብሔር ብለው ህዝቡን ያረጋጉትን እግዚአብሔር ሾሞ የተስፋይቱን ምድር እንድያዩ የእግዚአብሔር ሽልማት ሆነ ።
በአለማችን ላይ ሁሉም ሀገራት ሰላዮች አላቸው ። ነገር ግን ስለ እውነት የሚሰልሉ ይኖራሉ ። እንደ ቁራው ሄደውም ይቀራሉ ። እንደ እርግቧም ይሆናሉ ። እንደ አስሩም ክፋ ስራቸው የሚጥላቸው በአንዱ ወጥመድ ገብተው የሚጠፋ አሉ ። እንደ ካሌብና እንደ እያሱ አይነት መልካም ሰላይ አስታራቂ ፈርሃ እግዚአብሔር ያላቸው አሉ ።አለም ቅይጥ ናትና ። ሰላዮችን ለምን ይሰልላሉ ብለን መንቀፋ አንችልም ።
ለምን ቢባል ቀድሞ የነበረ ስራ ስለሆነ ግን እራሳቸው ለእራሳቸው ሊያውቁበት ይገባል ባይ ነኝ ።እንደ እያሱና እንደ ካሌብ ቢሆኑ እንደ እርግቧ ቢሆኑ መልካም ነው ። ይቺ አለም የግዜ ገደብ አላትና ። ወደ የማያልፈው አለም ስንሄዱ የዘሩትን ያጭዳሉና። የእግዚአብሔር መንግስት መውረስን ቢናፍቁ ብየ ግላዊ ሀሳቤን እለግሳለሁ ።
ይህንን እንድፅፍ ያደረገኝ የእናንተው ጥያቄ ነው ። ፈራሁሽ የወያኔ ተላላኪ ነሽ ወይ የምትሉኝም አላችሁ ። ሀሳባችሁን አልነቅፋም አትጠራጠሩ አልልም ። መጠርጠር መልካም ነው ግን ሀሳብን መመርመር እንጂ መወሰንን አትወውደዱ ሀሳቤን መርምሩ ። ብየ ፈቅጀ ዝም አልኳችሁ ።በውስጥ መስመር የምትልኩልኝ ጥያቄ እኔን አይገልፀኝም ። እኔ ሰላይ ብሆን እንኳ ሰላይ ነኝ አልላችሁም ። ሰላይ ነሽ እንደ የምትሉኝ ሰዎች ። ለማንኛውም እኔ እግዚአብሔር እንደሚያውቀው ሀገሬን የምወድ ልጅ ነኝ ። በሀገሬ በሀይማኖቴ ድርድር አላውቅም። ለዚህም ነው ስለሚያስጨንቀኝ ነገር መፍትሄን እናዋጣ ብየ ግዜ ሳይተርፈኝ የምፅፈው።እንኳን በሰው ሀገር ሆኘ በሀገርም ውስጥ ሆናችሁ ግዜ እንደሚያጥራችሁ አስቡ ።
የሰውን መከፋት , መታሰርን , ልጆቻቸውን አጥተው በሀዘን ሲኮራመቱ አይቼ መቻል አቅቶችን ነው ። የታፈኑ ድምፆች ድምፅ ለመሆን እንጂ እኔ ምንም አልሆንኩ ። ምንም አልተነካብኝ ። ነገር ግን እኔ ሰላም ነኝ በምሰራው ስራየ ደስተኛ ነኝ ከሀገር ውጭ ነኝ የራሳቸው ጉዳይ አልልም አልችልበትምም ። ችግራቸውን ማየት ይከብደኛል ሀዘናቸው እንባቸው ይረብሸኛል ። የነገይቱ ኢትዮጵያ እጣ ፋንታ ያሳስበኛል ። የታሪክ መፋለስ በእጅጉ ያሳዝነኛልም ያመኛል ሁሉ ።ስለዚህ ኢትዮጵያ ሀገሬ እስከሆነች ድረስ በምድር ስኖር ባስብላት ክፋት አለው እንደ ???
አንድነታችንን መናገር ወደ ቀድሞ ኢትዮጵያዊነት እንመለስ አንዱ ከአንዱ ቦታ ሄዶ ይስራ በትዳር ይተሳሰር ፍቅር ይበልጣል ብሎ መናገር ሀጢያት ነው ወይ??? የሚገርመው ከገዥው መደብ ያሉ ሰዎች አንቺ የግብፅ ተላላኪ ይላሉ አሸባሪ ነሽ ትመጫታለሽ ወዘተ ሲሉኝ ይገርመኛል ።እነሱ ያሉባት ኢትዮጵያ የእኔም እናት ሀገሬ ናት ። እግዚአብሔር የሰጠኝን እነሱ ሊነፍጉኝ ሲሞክሩ እያዘንኩ እገረምባቸዋሁ ።
ከተቃዋሚዎች ደግሞ የወያኔ ሰላይ ነሽ መሰል ወዘተ እነሱን አልፈርድባቸው ምክንያቱም ደሊላ ሶምሶምን ጥላዋለች ። ፀጋውን አሳጥታ ወፍጮ ፈጭ አስደርገዋለች ። ዋለልኝ መኮነንን እንድሁ ኤርትራዊታ ሴት መጥፊያውና ውድቀቱ ሆናለች ። ብዙ እንስቶች የብዙ ጀግኖች መጥፊያ ምክንያት ይሆናሉ ። ይሄን ደጋግሜ ስፅፈው ነበር ። ነገር ግን እኔ የእግዚአብሔር ህንፃ ቤተ መቅደስ የሆነው ሰውን ለማፍረስም ለማስፈረስም ምክንያት ከምሆን ብሞት ይቀለኛል ። አቅም የለኝም እንደዚህ አይነት አፀያፍ ስራን ለመስራት እና በበኩሌ ከፓለቲካ የፀዳሁ የማንም ፓርቲ ወይም ቡድን ደጋፊ አይደለሁም ግን በግሌ የመሰለኝ ሀሳብ ለማስቀመጥ እሞክራለሁ ። ፓለቲካ በፓለቲከኛ አዋቂ ለሀገር ጠቃሚ ነው ።ግን አንዳንድ እንዝላል ፓለቲከኛ ያለ ብቃት ሀገራችንን ወደ መጥፊያዋ እንድትደረደር የሚፈልጉ አሉ ። ያንን እንቃወማለሁ ። ፓለቲካ ለሀገር እድገት ጠቃሚነትም ጎጅነትም አለው ።ስለዚህ እኔ የማላውቅበትን ፓለቲካ ፓለቲከኛ ልሆን አልችልም ።  ለሀገራችን ዘላቂ መፍትሄ እንፈልግ።  ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር ።
Filed in: Amharic