>
5:13 pm - Friday April 19, 8002

ሥዩም ተሾመ ስለ ‘ሦስተኛ’ ፖሊስ ጣቢያ (ፍቃዱ ሃይሉ እንደከተበው)

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እና እኔ ዛሬ ‘ሦስተኛ ፖሊስ ጣቢያ’ (አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የፖሊስ ማቆያ ጣቢያ) ሔደን ነበር። የሚከተሉትን አጫውቶናል።
☞ እስካሁን ምግብ የሚቀርቡላቸው የማዕከላዊ ሰዎች ናቸው። ይህንንም ማዕከላዊ በተግባር አለመዘጋቱን ማመላከቻ አድርጎ ወስዶታል።
☞ አሁን ያለበት ክፍል ውስጥ 18 ሰዎች ሲኖሩ 12ቱ የኮማንድ ፖስቱ እስረኞች ናቸው።
☞ ክፍላቸው ውስጥ ካሜራ ያለ ሲሆን “ሰው ታመመ ብለን ስንጮህ ሳይደርሱልን፣ ካርታ ስንጫወት በደቂቃ ይመጣሉ” ብሏል።
☞ ‘000’ (ዜሮ ዜሮ ዜሮ) የሚባሉ 18 የማግለያ (solitary confinement) ክፍሎች አሉ ብሎናል። ክፍሎቹ ተዘግተው የሚውሉ ሲሆን አሁን አራት እስረኞች አሉባቸው። ሰዎቹ በደረቅ ወንጀሎች (ፖለቲካ ነክ ያልሆኑ ክሶች) ተጠርጥረው የታሰሩ ሲሆን፣ ሦስተኛ ፎቅ ላይ ተወስደው ነው የሚመረመሩት። ምርመራውን በማሰቃየት (torture) ለመፈፀም አርክቴክቸሩ የተመቻቸ ነው ብሎናል። እዚህ የታሰሩ ሰዎች ከቀኑ 6:00 ሰዐት እስከ 8:00 ድረስ ፀሐይ መሞቅ ይፈቀድላቸዋል። በዚያ ሰዐት እነ ሥዩም ተሾመ ስለሚቆለፍባቸው አያይዋቸውም። ሥዩም ምርመራውን ከጨረሰ በኋላ ያገኘው ኩመሳ (?) የተባለ በነፍስ ማጥፋት የተጠረጠረ የአምቦ ሰው ጥፍሮቹ መነቃቀላቸውን አይቷል። “በጥቅሉ ቶርቸር ቆማል የሚል የተሳሳተ ግምት መወሰድ የለበትም” ብሏል።
Filed in: Amharic