
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቦረና ላይ ሄዶ 10ሺህ ሰዉ ሰብስቦ በአማራኛ ቢያወራ ምናልባትም 5 ወይም 10 ሰወች ሊሰሙት ይችላሉ፡፡ አዲግራት ሄዶ በአማረኛ ቢያወራ 5 ወይም 10 ሰወች ሊሰሙት ይችላሉ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ባህርዳር ወይም ጎንደር ወይም ደሴ፤ደብረማርቆስ ደብረብርሃን ወይም አዲ አባባ ላይ 10ሺህ ሰዉ ሰብስቦ በትግርኛ ቢያወራ በእርግጠኝነት ከ 4 ሺህ በላይ አማራ ይሰማዋል፤ በኦሮሞኛ ቢያወራ ከአምስት ሺህ በላይ አማራ ይሰማዋል፡፡ ሌላዉ ቀርቶ እንኳን ብአዴን ዉስጥ ያሉ እንደንጉሱ ጥላሁን አይነት አማራዎች ኦሮሞኛ እና አማረኛ አቀላጥፎ የሚናገርሩ እንደምሳሌ መዉሰድ ይቻላል፡፡ የአማራን ህዝብ አማረኛ ብቻ እንደሚያዉቅና ለሌሎች ቋንቋወች Phobia እንዳለበት አድርጎ የሚስል ያዉ የተለመደዉ የዉሸት ትርክት ነዉ፡፡ የቋንቋ ፎቢያ ካለበት ብአዴን ነዉ ያለበት እሱም የእንግሊዝኛ ቋንቋ Phobia ነዉ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ እራሱን መግለጽ በሚችልበት ቋንቋ ቢናገር የአማራ ህዝብ ምንም ችግር የለበትም፡፡ የአንድነት ጎራዉ ነዉ የቋንቋን ጉዳይ ሲያቦካዉ የነበር፡፡ እና እኛ ምናአገባን፡፡ አንድነቱ ዉስጥ የእነ ለገሰ ዋቅጅራ ና የእነ ለታ ልጆች የእነ አርያና የእነ በርሄ ልጆች ነዉ ያሉበት፡፡ የአማራ የብሄርተኝነት ፖለቲካ ከዚህም በላይ እጅግ ጤነኛ እና ለሌለዉ ተምሳሌት ሊሆን የሚችል ነዉ፡፡ እንደደረሰብን በደል እማ ቢሆን ይሄኔ አብረን አልነበርንም፡፡
የአማራ ህዝብ ጥያቄወች የሚከተሉት ናቸዉ
• የማንነት(ወልቃይት፤ራያ፤መተከል) እንዲሁም አማራወች በያሉበት በቋንቋቸዉ የመጠቀም፤ባህላቸዉን የመሳደግና የፖለቲካ ዉክልና የማግኘት
• የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፍትሃዊ ተጠቃሚነት
• እኩል የፖለቲካ ተሳትፎ
• እኩል የሀገር ሀብት ክፍፍል
• ነጻነት፤ዲሞክራሲና የመብት መከበር
• ፍትህ ያለ አድሎ የማግኘት ናቸዉ
• የአማራ እራሱ በመረጣቸዉ ልጆቹ እንዲተዳደር ናቸዉ ጉልህ ጥያቄወች
ከዚህ ዉጪ ያለዉ ተራ ፕሮፖጋንዳ ይሄን ትልልቅና ወቅታዊ የአማራ ህዝብ ጥያቄ ለመሸፋፈን ነዉ፡፡ መስመር ሳንለቅ ና distract ሳንደረግ ጥያቂያችን በዚሁ መንገድ እናቀርባለን
የአማራ ህዝብ open society የምንለዉ አይነት ህዝብ ነዉ፡፡ የአስተሳሰብ፤የባህል፤የቋንቋ፤ የሃይማኖት ፤የአመለካከት፤ የጀነቲከስና የአዲዮሎጂ ብዝሃነት በጸጋ ተቀብሎ የሚኖር ህዝብ ነዉ፡፡ አማራን ከማኝኛዉም ማህበረሰብ ባላይ ወደፊት ተጠቃሚ እና በቀላሉ እራሱን እንዲለዉጥ የሚያድረገዉ ያለዉ የተፈጥሮ ሃብት ሳይሆን በእነዚህ ልዩነቶች የተገነባዉ የሰዉ ሀብቱ ነዉ፡፡ እኒህ ጤነኛ የአስተሳሰብ፤የባህልና የቋንቋ ብዝሃነት የቴክኖሎጅ ፍልስፍናን ይጨምራል (innovation)፤entrepreneur and pragmatic ማህበረሰብ እንዲኖር ያደርጋል፤ ብዙ ሳይንቲስቶች፤አስተማሪዎች፤መሪወችና የመብት ተሟጋቾች የሚወጣበት ማህበረሰብ ይሆናል፡፡ የአማራ ህዝብ future እጅግ አንጸባረቂ በየትኛዉም የአለም ክፍል ያለ ማህበረሰብ ሊኖረዉ የማይችል ጸጋና ተስፋ ከፊቱ ይጠብቀዋል፡፡ የአማራ ህዝብ አዋጅ አላወጣም ይሄን ቋንቋ እንዳትናገር ብሎ ወይም ታፔላ አልዘቀዘቀም፡፡ We embrace diversity. አብዛኘዉ የአማራ ህዝብ ከአማረኛ በተጨማሪ ሁለትና እና ሶስት ቋንቋ ይናገራል፡፡ማነዉ እና የቋንቋ Phobia ያለበት? ንገሩኝ ባይ ሁላ፡፡