አንዲአርጋቸውን በማፈን ሂደት ውስጥ የተሳተፉ አገሮችና ሰዎች ዛሬ ያኔ እንደነበሩት አይደሉም።
…
1 ~ አንዳርጋቸውን በማፈን ሴራ ውስጥ ዋና አገር የነበረችው የመን በሰማይ በሚወነጨፍ ሚሳዬልና በሚወረወር ቦምብ ፈራርሳና ተደረማምሳ የድንጋይ ዘመን አገር ሆናለች።
…
2~ አንዳርጋቸውን በማሳፈን ሴራ ከፍተኛውን ሚና የተጫወተው የየመኑ ፕሬዚደንት የነበረው አሊ አብደላ ሳልህ በሁቲ አማፂያን የራስ ቅሉ በጥይት እንደ ዱባ ተፈልጦ ሲሞት በቴሌቪዥን መስኮት በአይናችን በብሌኑ አይተናል።
…
3~ የመን ሰንአ አለምአቀፍ አውሮፕላን ተርሚናል ውስጥ የታፈነውን አንዳርጋቸው ፅጌን የራሱን ቻርተር የግል አውሮፕላን ልኮ አስመጥቶ ማእከላዊ እንዲሰቃይ ያደረገው ሼህ መሀመድ አላሙዲን በተራው ሳኡዲ አረቢያ ውስጥ ታስሯል ። ቢዝነሱ እየከሰረ ካምፓኒው እየተዘጋ ከአለም ሀብታሞች ስም ዝርዝር ውስጥ ተፍቋል።
…
4~ አንዳርጋቸውን በማሳፈን ውስጥ ከ20 ሚሊዮን ዶላር በላይና አዲስ አበባ የሚገኘውን የትምባሆ ፋብሪካ ለየመን ባለሀብቶች በነፃ የሰጠው የደህንነት ምክትል ሃላፊ የነበረው ወልደሙካኤል በሙስና ሰበብ ታስሮ ቃልቲ ይገኛል።
…
አንዳርጋቸው ፅጌ ዛሬ የኢትዮጵያ ህዝቦች በተለይም የአማራ ፋኖና የኦሮሞ ቄሮዎች ታግለው ባመጡት አጠቃላይ ፖለቲካዊ ትግል ነፃነቱን ሊያገኝ ነው።
” ለክፉና ለአመንዝራ ትውልድ ምልክት አላሳየውም፡፡ እንዲሁ አጠፋዋለሁ!” እንደሚለው ፍካሬ – ኢየሱስ ክፉና አመንዝራ የሆኑትና የታሪክ ጎርፍ እያግበሰበሰ ያመጣብን ወያኔዎች ምልክት ሳያዩ እየጠፉ ነው።
ቦ ጊዜ ለኩሉ !!