ኤርትራ በጣሊያን ቅኝ በነበረችበት ግዜ አሥመራ ውስጥ የጥቁር ሰፈር አባሻውል ፤ የነጬ ሰፈር ኲምፒሽታቶ ካቴድራል ማህጃጅ ሲሆን ኤርትራዊው ወደነዚህ ሰፈሮች የሚሄዱት ለአሽከርነት ስራ ብቻ ነበር።የስራ ግባ ደወል ከተማዋ ላይ ሲነፋ ጥቁር አበሻ ከአባሻውል እየሮጠ ጌቶቹ ባሰማሩት ቦታ ላይ መገኘትና ግልጋሎት መስጠት አለበት ዘግይቶ የደረሰ ግርፋት ይጠብቀው ነበር።እናት ኢትዮጲያ ቤት ፒያሳ ካምቦ አስመራ ተክለሃይማኖት ደቀ ማህሪ አዲሱ ቄራ ፖፖላሬ ገነት ሆቴል የድሮው ፊያት ….ወንድም ኤርትራውያን የሚነግዱበት የሚዝናኑበት ክብርና ሞገስ ተላብሰው ተጋብተው ተንቀባራው የሚንደላቀቈበት ሀብት ያፈሩበት አገራቸው ነበር። ሻእብያ ኢትዬጲያ ቅኝ ይዛናለች ያለው ይህን ኑሮ ነበር።
ወያኔ ለስልጣኑ ሲል ክልል 0 – ኤርትራን አስገንጥሏል። የአትዬጲያን ህዝብም ያለወደብ አስቀርቷል።የወያኔ ባንዳዊ ባህርይ ስውር ደባ ውጤት መሆኑ ነው።ቻይና ድሃና በዘመኑ ስልጣኔ ኊላ ቀር በነበርችበት ጊዜ የአውሮፓ ቅኝ ገዢ የነበረችው ፓርቱጋል የቻይናን የባህር ወደብ የሆነችውን ማአካዎን ለ400 አመት በቅኝ ይዛነበር።እንደዘሁም ብርቲሽ ያሁኗን ትልቐን የወደብ አገር ሆንግ ኮንግን ለ158 አመት ቅኝ ይዛ ነበር።በነዚህ የቅኝ ዘመናት ውስጥ በተለያዩ ወቅት የተነሱት የቅኝ ገዢዋች መንግስታት መሪዎችና በተለያዩ የቻይና አፄዎች መካከል በዙ የስምምነት ውሎች ተፈርመው ተሰርዘዋል።በ1940 ቹ የቻይና ህዝብ እጣ በቻይና ኮሚንስት ፓርቲ እጅ ወደቀ። ይህ ፓርቲ ደሃይቱን ቻይናን ከኩባያ ሩዝ የእለት ገቢ አንስቶ እስከ አቶሚክ ባለቤትነት አስመነጠቃት። ከድህነትና ከዘመኑ ቴክኖሎጂ ኃላ ቀር የነበረችውና በቅኝ ገዠዋች ሴራና በመሃል አገር አፄዎች (ዴናስቲ) ክፍፍል ለመጨረሻዎቹ 400 አመታት ስትርመሰመስ የቆየችው አገር በአንድ ኮምኒስታዊ አምባገነን ፓርቲ ስር ጠንካራ ማእከላዊ መንግስት መሰረተች ።በተለይ ፓርቲው ያካሄደው እልክ አስጨራሽ ባህላዊ አብዮት ተራራን ንዶ ሜዳ የሚያደርግ ጠንካራ ትውልድ መሰረተ። የቻይና የወታደራዊ ሃይል ግንባታም ከሃያላን ሀገሮች ጎራ አሰለፋት አስከበራት።
በመጨረሻም ከቅኝ ገዢዎች ጋር የነበረውን የመጨረሻዎቹንም ስምምነት እንደማትቀበል አሳውቃ ያጣቻቸውን የወደብ አገረቿን በ1997 ሆንግ ኮንግን በ1999 ማአካዎን አስመለሰች።ኢትዬጲያ ያለማጋነን የምስራቅ አፍሪካ ቻይና እንደምትሆን ጅቡቲና ኤርትራ የኢትየጲያ ማአካኦና ሆንግ ሆንግ እንደሚሆኑ ምንም ጥርጥር የሌለው ህልሜ ነው።ቅዠቴ ነው አላልሁም።እውን የሚሆን ህልም ነው።ሁሉም የሚወስነው በመሃል አገር ጥንካሬና አንድነት ነው። ሁላችንም ወያኔ ከዘረጋልን ከነገድ ፓለተካ፣ ከክልል ፓለቲካ አላቀን በአህጉራችን ጠንካራ ተራራ የሚንድ ትውልድ ፈጥረን በአለም ተወዳዳሪ የምትሆን አንድ አገር መስርተን ለልጆቻችን ማስረከብ ይኖርብናል።ክፍፍልን ማቆም ካልቻልን በነፃነትና በመብት ስም ሁላችንም ተገነጣጥለን እንወድቃለን።በጋራ ሆነን ያላሸነፍነው ድህትም ተበጣጥሰንም የምንወጣው አይሆንም።የእኛ የደካማነት መገለጫ የሚሆነው ስብርባሪ ታረካችንም ክብርና ፅጋ ለልጆቻችን አያላብሰም። አዲሱ ጠቅላይ ሚንስተር ዶ/ር አብይና የአገሪቷ አዲስ ፖሊሲ አውጨዎች መገንዘብና ደፍረው ማድረግ ያለባቸው አንድ ትልቅ ሃቅ 1ኛ.የአገራችንን አንድነትና ሉአላዊነትን በከፍተኛ ደረጃ ማምጣት ፤ 2ኛ.ዜጎች በህግ ፊት እኩል ሆነው በየትኛውም የአገሬቷ ግዛት ሳይሽማቀቁ ተፈቅረውና ተከባብረው በጋራ የሚኖሩባት ህጋዊ ዋስትና ለዜጎች መሰጠት። ለዚህ ደግሞ የዜጎችን ፍቅር ሰላምና እድገት – እንቅፈትና ደንቀራ የሆነውን ቐንቐን መሰረት ያደረገ ኊላቀር የክፍፍልና የክልል ፓለተካ ህገመንግስት መሰረዝና መሰረቱ ሰው ሁሉ እግዚአብሄር በእኩልነት ፈጥሮታል ወደሚል የዜገኝነት ፓለቲካ መለወጥ ነው።ለዛሬው በዚህ ይብቃኝ።ቻው።