>

የባህር በር ከኤርትራውያን የምንለምነው ዳረጎት አይደለም! ህጋዊ መብታችን ነው!!! (እድሪስ ድልነሳው)

ቦሊቪያ በ 19ነኛው ምእተ ዘመን ከጎረቤቷ ከፔሩ ጋር በቺሌ መንግስት ተወረረች። ይህ ወረራ የቦሊቪያን ህዝብ እና መንግስት የባህር ወደብ አልባ አደረገው። ይህም የሆነበት ቦሊቪያ impot እና export በቺሌ በኩል እንድታደርግ ታስቦ ነው።
     ችግሩ መፍትሄ ሳያገኝ የተባበሩት መንግስታት “የባህር በር አለም አቀፍ ሸንጎ” የማያሻማ ህግ እስኪያልፍ ድረስ መፍትሄ ሳያገኝ ቆየ። ያም ሆኖ ሆኖ የቦሊቪያ መንግስት የባህር በሩ እንዲመለስለት ከመከራከር ችላ ያለበት ጊዜ አልነበረም። የባህር ሃይላቸውንም በወንዝ እና ሃይቆቻቸው ዙርያ ማጠናከራቸውን ቀጠሉ። ዛሬ 157 አገሮች የፈረሙበት የባህር እና ወደብ ህግ ከፀደቀ በሁዋላ ፤ ቦሊቭያ እንደገና።የባህር ወደብ ባለቤት ሆናለች። ይህ የቦሊቭያ የባህር በር አነድተኛ መሬት ይሁን እንጅ ፤ ቦሊቭያ የራሷ አስመጭ እና ላኪ መንግስት እንድትሆን አድርጓታል። የቦሊቭያ የባህር ሃይል እና coast guard ከሃይቅ እና ወንዞች ላይ ወጥቶ ዛሬ ያለማንም ጠያቂ ባህር ላይ እየቀዘፈ ነው።
         ከኤርትራ ነፃነት በሁዋላ የኢትዮጵያ መንግስት ተመሳሳይ ጥያቄ ያነሳል ተብሎ እየተጠበቀ ነበር። ይህ መንግስት ብዙ በድሎናል። ነገር ግን የክህደቱ መጠን እዚህ ይደርሳል ብሎ የገመተ ማንም አልነበረም። በማያሻማ ቋንቋ ፤ ኢትዮጵያ የምታነሳው የባህር በር ጥያቄ የለም አሉ። የፀደቀውን የተባበሩት መንግስታት አንቀፅ ማንሳት ለኢትዮጵያ ሰላም ጠንቅ ነው አሉ። የሰብአዊ መብት ተከራካሪዎች እና የተባበሩት መንግስታት ስለ ኢትዮጵያ የባህር ሃይል ያቀረበላቸውን  ጥያቄ ፤ በማጣጣል፤ ኢትዮጵያ የባህር በር የላትም ፤ ስለዚህም ባህር ሃይሉን አንፈልገውም አሉ። በጊዜው የኢትዮጵያ የባህር ሃይል ሸሽቶ ወደ የመን ተጠግቶ ነበር።
          በወሮበላው ስዩም መስፍን ይመራ የነበረ የዘራፊዎች መንጋ ፤ ኤርትራ ኤርትራ አትበሉ ፤ ኤርትራ ነፃ አገር ነው ብሎ ደነፋብን። አቶ መለስ ዜናዊም ይህ ጥያቄ በተነሳ ቁጥር አይኑን አፈጠጠብን። አፉ አረፋ እየዳፈቀ ጥርሱንም አገጠጠ ።
    እኛ በዘመኑ ኤርትራ ኤርትራ አልነበረም ያልነው። ወደድንም ጠላንም ኤርትራ ነፃ መንግስት መሆኗን እናውቃለን። የጮህነው ለኢትዮጵያ መብት ነበር።
     ኢትዮጵያ ከቀይ ባህር ዳርቻ በማእከል(on average) 60 ማይል እርቀት ላይ ብቻ ናት። አንዳንድ ከፍታዎችም ላይ ሆኖ የተንጣለለውን ባህር በአይን ማየት ይቻላል። ለቀይ ባህር በጣም የቀረበው መሬታችን ከ 12 ማይል አይበልጥም ። ስለሆነም በተባበሩት መንግስታት ውሳኔ መስረት የባህር በር ይገባናል። ይህ የባህር በር እንዳይኖረን የተደረገው በወያኔ ወሮበሎች ውሳኔ ነው። እኛ ኢትዮጵያውያን እየጠየቅን ያለነው ኤርትራን ወይም አሰብን አይደለም። እየጠየቅን ያለነው ፤  በአለም አቀፉ ኮንቬንሽን ውሳኔ መሰረት የሚገባንን ህጋዊ መሬት ነው። አለም ከተፈጠረ ጊዜም አንስቶ ፤ የባህር በር አያስፈልገኝም ብሎ ሲከራከር ወያኔ የመጀመሪያው ነው።
       ኤርትራ እና ኢትዮጵያ open border policy ሊኖራቸው ይገባል። ይህ ለሁለቱም።አገሮች ወሳኝ ነው። ነገር ግን የባህር በር ጥያቄ ከኤርትራውያን የምንጠይቀው ጉዳይ አይደለም። ህጋዊ መብታችን ነው። ያለ ኤርትራ ፈቃድ በመሬት ተቆልፈን የምንቀር ህዝብ አስመስለው የሚያወሩት የወያኔ ወሮበሎች ናቸው።
          ኢትዮጵያ ትንሳኤ! !!!
Filed in: Amharic