ጄነራል ሳሞራ ” አማልዱኝ ” እያለ ነው
“ቆሎ እየቆረጠምንም ቢሆን በክብር እንኖራለን”
በእነ ጀኔራል ተፈራ ማሞ ክስ መዝገብ ታስረው ከተፈቱት መካከል
ጌታቸው ሽፈራው

እንዲህ ነበር ያሉኝ!
“9 አመት ሙሉ ስንሰቃይ ዘወር ብሎ አላየንኝ። ብዙ ስቃይ ደርሶብናል። ቤተሰባችን ተብትኗል። አሁን ጊዜ ሲክደው ነው አማላጅ የሚልከው። እኛ የታገልነው ለሕዝብ ነው። ለጥቅም ቢሆን እዛው ሆነን እናገኘው ነበር። ይህን ያህል ባልተሰቃየን ነበር። ወደዚህ ስንገባ የህይወት መስዋዕትነት እንደሚያስከፍልም አውቀን ነው። ይህን ሁሉ ስቃይ አይተናል። የሚያልፍ ጊዜያዊ ችግር ስለገጠመን እነሱ ጋር የምንሆን መስሏቸው ነው። ቆሎ እየቆረጠምንም ቢሆን በክብር እንኖራለን። የገጠመን ችግር የሚያልፍና ጊዜያዊ ነው”
ጀኔራል ሳሞራ ግን ያሳሰራቸውን፣ ያን ያህል የተሰቃዩትን ሰዎች መለማመጥ የጀመረው ምን ቢገጥመው ነው?