>

አርቲስት ሀጫሉ በድጋሚ ታሪክ ሰራ (ሄቨን ዮሀንስ)

አርቲስት ሀጫሉ ሁንደሳ በወኔ በሙሉ ልብ በጀግንነትና በእልህ በሚሊኒየም አዳራሽ በተሰበሰቡ ባለ ስልጣናትና ህዝቦች እንድሁም ደህንነቶች ብሎም በቀጥታ ስርጭት ለሚከታተሉት በሙሉ በቃሊቲ በቂሊንጦ የታጎሩ ወገኖችን ድምፅ አስተጋባ ። ተነስ ወገኔ የኦሮሞ ጀግኖች ቃሊቲ ናቸው ተነስ የኦሮሞ ልጅ የሆንክ የኦሮሞ ጀግኖች ቂሊንጦ ቶርቺ እየተደረጉ ነው ። የእኔ ጀግኖች እዛ ናቸው ። ፍትህ ይገባቸውል ። አራት ኪሎ ይከፈት ቤተ መንግስት እንግባ እያለ በንደትና በስቃ ድምፅ አንጎራጎረ ተንጎራደደ ። እኔም ናጥ አድርጎኛል ማንም ኢትዮጵያዊ እውነትን ይዞ መታሰር የለበትም ባይ ነኝና ።
አቦ ለማና  አብይ እንድሁም አባ ዱላ ሌሎችም ባለስልጣናትን ነገራቸው ሂዲ ጉቡ አራት ኪሎ አላቸው። ትንቢት የሚመስለው ዘፈን ገፋፍቶ ገፋፍቶ በፍጥነት አራት ኪሎ በኦሮሞ ልጆች ተጥለቀለቀች ። ደስም ተሰኙ ። ባለ ውለታቸውን አይዘነጉምና የኦሮሞ ባለ ሀብቶች ዛሬ መኪና ብር ወዘተ የሀብት ቁሳቁስን አዘነቡለት ። ሀጫሉ ሁንደሳ ከምርም ጀግና ነው ። ፊት ለፊት የተጋፈጠ የወጣት ፈርጥ ነው ። ጀግና ደስ ይለኛል አድንቄዋለሁ ተደጋጋሚም ፅፌለታለሁ ። ሀጫሉ 5 አምስት አመት የወገኖችን ህመም የታመመ በተጠርጣሪነት ቂሊንጦ የታሰረ ልጅ ነው ። ተጠርጥሮም አንድም ቀን ፍርድ ቤት ሳይቀርብ ጉዳዩ ሳይታይለት ታስሮ ወጥቶ ለስኬት የበቃ ልጅ ነው ።
የያዕቆብ ልጅ ዮወሴፍ ከሀገሩ በግፍ ተሰዶ በግብፅ ንጉስ ቤት ሲሰራ በንጉሱ ሚስት በሀሰት ተከሶ ወንጀለኛ ሆኖ እስር ቤት ተወረወረ ። ያኔ ሁለት ሰዎች ህልም ያያሉ ዮወሴፍ ፈታላቸውና ። ከእዚህ ስትወጡ አስቡኝ እንዳትረሱኝ አስታውሱኝ አላቸው ። አንዱን ትሞታለህ ብሎት ነበርና ሞተ አንዱን አስታውሰኝ አደራ ሹመት ታገኛለህ ያለው ዮሴፍን
ዘንግቶት ነበርያም ሆኖ ሁሉ የሚሆነው እግዚአብሔርም ሲፈቅድ በጊዜው እና በወቅቱ እንዲያስታውሰው ግድ ሆነ ያኔ ዮሴፍም ከእስር ወጥቶ የንጉሱን ወንበር ብቻ ሲቀረው ሌላውን ነግሶበት ግብፅን መራት ።
 ሀጫሉም በእስር አብሮአቸው የነበረውን የእስር ጋዶቹን የላመ የጣመ ሲበላ አልዘነጋቸውም ። በዘመናዊ ቤትና በዘመናዊ መኪና እንዲሁም በዝናው  ተታሎ አልፈራም ቀንና ግዜ ጠብቆ በሚያምር ድምፅ በሚገርም ወኔ  ድምፃቸውን አሰማ ለግፉአኑ ጩህታቸውን ጮህላቸው።
 ያኔ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በሀገርም ውስጥ ከሀገርም ውጭ ሁሉንም ቀልብ ገዛ ። የታሰሩም ተፈቱ ። አሳሪዎቹ እና ከሳሾቹ እንደ ማንም በሶስት መስመር ደብዳቤ ተባራሪ ሆኑ፤ ይሄ ከመንግስታዊ የስልጣን ወምበር ሲሆን ክፉ ስራቸው ደግሞ እስከ መቃብር የሚያሳድዳቸው ሆኑ። በስፍራውም ፖለቲካውን የሚፈትሉ ፣ ባለስልጣን ከመሆናቸው በፊት ሰው መሆናቸውን ለአፍታም ያልዘነጉ ተሾሙበት። አጫሉም ዝናውን ተከትሎ የመጡትን  አጓጊ የሆኑ ሽልማቶች ሁሉ ለተፈናቀሉ ወገኖቹ በስጦታ አበረከተ። እዮሀ  ታሪክ ተሰራ ማለት ይህም አይደል።
Filed in: Amharic