>

እኔም አበጠር ወርቁ ነኝ!?! (አንዷለም ቡከቶ ገዳ)

እንዴት ናችሁ ወገኖቼ?!..እኔ እንኳን ደህና አይደለሁም፡፡መንፈሴ ታውኳል?!እንዴትስ አንድ ደሃ አባት ብልቱ የተሰለበ ፡አይኑ የተጎለጎለ ልጁን ከጉልበቱ ስር ታቅፎ በአቅም ማጣት እና በተጠቂነት ስሜት አይኑን ክርትት ክርትት ሲያደርግ አይቼ መንፈሴ አይታወክ?!….እንዴትስ ለጋ ህጻን በማያውቀው እና በማያገባው ነገር አካሉ ለእርድ እንደቀረበ ከብት በህይወት እያለ ሲበለት …የሚሳሳላት አይኑ በጨካኞች ካራ ስትጎለጎል… እናቱ ስማ ያልጠገበችው ጉንጩ በአላዋቂ አዋቂዎች ገና በህይወት እያለ እየተቆረጠ ሲጣል አይቼ ….ስቅስቅ ብዬ አላለቅስ…?!.የ13 አመት ቡቃያ “አረ ስለነብስ!” እያለ ህይወቱን ሊያተርፍ ሲለምን ….
አእምሮዋቸው የተደፈነ ሰዎች ብልቱን እንደ ዶሮ አንገት ቆርጠው ሊጥሉት….ሲጎትቱ  ሲይዙት ….ተናግሮ ባልጠና አንደበት …..”በዛ በበጋ “በመዝፈኛ እድሜው…..
“አረ ስለወንድ ልጅ አምላክ ሽንት መሽኛዬን አትቁረጡብኝ!” ብሎ እንደ አዋቂ ሲለምን ሰምቼ ….
እኔም ራሴ ወንድ ልጅ በዛ ላይ የወንድ ልጅ አባት
እንዴትስ የህጻን ልጅ መንፈስ በታላቅ ስቃይ  ስትቃትት …..አይቼ መንፈሴ አይታወክ አልሳቀቅ….!? አረ ኤዲያ መጻፍም እኮ የመንፈስ ጥንካሬ ይጠይቃል….እያንዳንዱን  ፊደል ለማውጣት …ልቤ  ከልብ መድማቱን ………….አይኔ ማንባቱን ማን ያውቃል…!?፡
 እንዴት የሰው ልጅ ባገሩ…… በገዛ በራሱ ዜጋ …..ይሄን የሚያህል  ሰቆቃ  ነጋ ጠባ ይደርስበታል…….?!
አማራ እንደ ኢትዮጲያዊ… እየኖረ ሁሌ  እንደ አማራ ይሞታል…..
ጉሙዝ የሚሉት  ማነው?! ሶማሌስ  ማን ሆነና ነው?! …
ከመሬቴ ላይ ሂዱልኝ  ብሎ ……በገዛ ሀገራችን መሬት እኛን   መጻተኛ ያደረገን?!
እንዴትስ ይሄን የግፍ ግፍ የሚቀበል…………………………. አበሾች ህሊና ኖረን
ሶማሌ ሶማሌ እንዲሆን …………..አሊ በርኬ አልደማም?!
ኦሮሞ በካራማራ ………ደሙን ከአፈሩ አላስማማም?!
የእናት አገር ጥሪ ነው ብሎ ቱታ አካሉን አልሰዋም?!
ኡፍ! …ከዚህ በላይ መጻፍ አልችልም!…….
ዛሬ ከአገሬ ውጡልን የሚለው የጉሙዝ እና የበርታ ህዝብ አፉን ሞልቶ አገር አለኝ ይል ዘንድ ድንበሩ አሁን ያለበት ቦታ ተለይቶ ይሰመር ዘንድ ….እንደሌሎች አፍሪካውያን ወንድሞቹ በባርነት እንዳይፈነገል ….እያንዳንዷ ስንዝር መሬት የትግሬው… የአማራው…. የኦሮሞው ….. የወላይታው ወዘተ አጥንትና ደም እንደተከፈለባት ያውቅ ይሆን?! (በነገራችን ላይ የጉሙዝ አጥንትና ደም ለአገር አንድነት  መከፈሉን  ” አይ ሃይሊ ዳውት”…. ዛሬ  አብዲ ኢሌ ካገሬ ውጡ ብሎ ወገኖቼ የአያት ቅድመ አያታቸው እትብት የተቀበረበትን ቀዬ ትተው  ከሞቀ ቤታቸው በአንድ አለሌ መሃይም ትእዛዝ ተፈናቅለው በለገጣፎ እንደ አብርሃም በድንኳን ሲኖሩ ሳይ እንዴት እንደሚያመኝ አትጠይቁኝ?!እንዴትስ አያመኝም?!
አማራውስ ጫካ መንጥሮ ካቀና መሬት ላይ በቅጡ ፊደል ባልቆጠር የቀበሌና የወረዳ ካድሬ የሚፈናቀለው ከርስቱ የሚነቀለው ኢትዮጵያ ለአማራው አገሩ አይደለችምን???? ይሄ ምን ማለት ነው። “ከአገራችን ውጣ…” አይገባኝም።
 ……የአበጠር እናት ጨክና የማትገርፈው የልጇ ገላ በካራ ሲተለተል….ስታይ ….ሳይ…ትላንት አብዮትና ሶሻሊዝም ዛሬ ብሄርና ፌደራሊዝም ምን እንደሆነ እንኳን ባልገባቸው  ደንቆሮ  የቀበሌና የወረዳ ካድሬዎች ምክንያት ተራው ህዝብ  ክቡሩን የሰው ልጅ ህይወት ሊቀጥፍ እጁን ሲዘረጋ ሳይ …….እንዴት  አያመኝም?! ከዚህስ በላይ ህመም አለ?! ከዛም በላይ ደግሞ ቅጥል የሚያደረግኝ ነገር አለ ….ይሄ መከላከያ ሰራዊት የሚባለው ስብስባችን ፡፡….ቆይ ይሄ ሁሉ  ጦር የምንቀልበው ለመቼ ነው?!….አስፈሪው ፡ጀግናው፡ አሰላሳዩ፡ እህል አጫጁ   ወዘተ የሚባልለት ሰራዊት…..እንኳንስ በሚለተሪ ኢንተለጀንስ ቀርቶ እኛ ተራዎቹ እንኳን  ልቡ ያበጠ የጉሙዝ እና በርታ ጎረምሳ የቀበሌ አመራር  “እስከዚህ ቀን ድረስ አማሮች ክልላችንን ለቃችሁ ካልወጣችሁ እርምጃ ይወሰድባችኋል” ብሎ ሊያውም በግልጽ ደብዳቤ የጻፈውን እያየን …መከላከያውም ይሄን እያወቀ  ዝም ካለ  እኛ  መንግስትን እንጂ ህገመንግስትን የሚያስከብር መከላከያ አለን ማለት እንችላለን?! ነው  ወይስ መከላከያችን በውጭ አገራት ሰላም ማስከበር እንደለመደው በዶላር አበል ካልተከፈለው  ንቅንቅ አይልም?! ክፈሉ ካላችሁን እናዋጣለን!..ነው ወይስ የእናንተንም አበል የፈረደበት በላይነህ ክንዴ ይክፈል?!….ነው ወይስ የአማራ ነብስ ግምቱ ዝቅተኛ ነው?! አረ ሼም ከሼምም የመጨረሻው ሼም ነው! ተው ተው….ለግፍም ለከት አለው!
የአበጠር አይኖች ተጎልጉልው የተጣሉት ፡ወንድነቱ በካራ ተቆርጦ አፈር ላይ የወደቀው በእኛው ጥፋት እንደሆነ ልንረዳውና ሊያመን ይገባል፡፡ እኔም እንደዚህ ትውልድ አባል እንደ አንድ የተማረ ሰውም በአካባቢዬ የሚደረገውን ከእውቀት አጥረት የሚሰራ የጥፋት እና ክፋት ድግግሞሽ ሳይ  ውስጤን ያሳክከኛል፡፡
ለማንኛውም ነገ በጠዋት አበጠር በተኛበት ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል(ምስጋና ለእነ ዶ/ር ደሳለኝ) ሄጄ ልጠይቀው እና የሚሰማኝ ቢሆን ለእሱም ለአባቱም  አንድ ነገር ልነግራቸው  እፈልጋለሁ!….አበጠር ወንድሜ አይዞህ! ምንም እንኳን በደሉ በደረሰብህ ወቅት በረዳት ማጣት ስሜት እየተሰማህ የነበረውን ነገር አሁን መገመት ባልችልም ከዛሬ ወዲህ ግን ብቻህን አይደለኽም…አቶ በላይነህ ክንዴ አለኝታህ አሉልህ….  እኔና ጓደኞቼ ደግሞ ምንም አቅም ባይኖረን እንኳን በምንችለው ሁሉ እንረዳሃለን .. ሁላችንም እንወድሃለን.. ልለው እፈልጋለሁ፡፡
ከዚህ በላይ መጻፍ አልችልም
Filed in: Amharic