>

ኢትዮጵያ የታሰረችው በእነ አንዳርጋቸው መታሰር እንጂ በዘራፊው ሼህ መታሰር አይደለም!?! (እየሩሳሌም ተስፋዬ)

ዶ/ር አብይ ለአንድ ዜጋ ዋጋ የሚሰጡ ከሆነ የአላሙዲ ጉዳይ እንዳሳሰበዎት ሁሉ የአንዳርጋቸው እና ሌሎች ፖለቲከኞች ሀገሬን ባሉ ለአመታት ወህኒ ተወርውረው ህዝብ ፍቱልን ሲልዎት አስቸኳይ ምላሽ ሊሰጡን ይገባ ነበር።
እኚህ ሰው እኮ በተጨባጭ ወንጀለኝነታቸውን ያረጋገጡት ሳውዲዎች እና ሞሮኮዎች በስርቆት ያከማቹትን ሐብታቸውን ሳውዲ 60% ሞሮኮ ደግሞ 20% ወርሷቸዋል ። በዚህም ምክንያት አሁን ፎርብስ ባወጣው የአለም ቢሊየነሮች ስም ዝርዝር ከረጅም አመታት በኀላ ሼኩ ያልተካተቱበት ሊሆን ችሏል ። ታዲያ እኚህን ሰው ለማሰፈታት ምን ሞራልና ተነሳሽነት ሊኖር ይችላል ? ጠ/ሚ አብይ ሙስናና ሌብነት ጠል መሆናቸውን በተለያዩ መድረኮች ገልፀዋል ። አሁን ይህ የሼኩ ጠበቃ ሆኖ በአደባባይ መቅረባቸው አቋማቸውን እንድንጠራጠር አያደርገንም ? ደግሞስ ” ፍትህ ” እያሉ ሲጮሁ ወደ እስርቤት ተወርውረው አሁንም በጨለማው የኢህአዲግ እስር ቤት ያሉ ታጋዮች አሉ አይደለም እንዴ ?
በመሰረቱ ለአንድም ዜጋ ዋጋ የሚሰጡ ከሆነ በአበጥር ወርቁ እና ወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለው ግፍ አማራ በመሆናቸው ብቻ ሲገደሉ ሲፈናቀሉ እንደ በግ ሲበለቱ(በግ እንኳ ታርዶ ነው እሚበለተው እነዚህ ግን በቁማቸው ሲበለቱ) ባቀኑት ሀገር መጤ ተብለው ሲባረሩ እየደረሰ ያለው በደል ሊያሳስብዎት ይገባ ነበር እርስዎ ግን እስካሁን ዝምታን መርጠዋል
እናም የአንድ ዜጋ ዋጋ ቢያሳስብዎትም  እንደ ዜጋ ለመቆጠር ግን ቅድመ ሁኔታ እንዳለው አስረግጠው ቢያልፉ መልካም ነው
Filed in: Amharic