የጋዜጠኞች መብት ተከራካሪ የሆነው ሲ.ፒ.ጄ “እንኳን ደህና መጣህ” በሚል ለ3 ቀን ያቀረበለትን ግብዣ ተቀብሎ ነው እስክንድር ወደኒዮርክ ያመራው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ታዋቂው ፀሀፊ ፕሮፌሰር ዊሊያም ኢስተርሊ እና ጋዜጠኛ እስክንድር በኒዮርክ ተገናኝተዋል። ፕ/ሮ ኢስተርሊ፣ “ቲረኒ ኦፍ ኤክስፐርት ” በተሰኘው ዝነኛ መፅሀፋቸው የሚታወቁ ሲሆን ፣ በዋናነት ፕሮፌሰር ጀፈሪ ሳክስ የተባሉ ፀሀፊ ኢህአዴግን በማወደስ የፃፉትን መፅሀፍ በመቃወም የሚታወቁ ናቸው።
ፕ/ሮ ኢስተርሊ ከልማት በፊት “ሰብዓዊ መብትና ዲሞክራሲ መቅደም አለበት ወይም ጎን ለጎን መሄድ አለባቸው” በማለት መፅሀፍ የፃፉ ሲሆን፣ ሳክስ ደግሞ፣ ከምንም ነገር በፊት ለኢኮኖሚ ዕድገት ቅድሚያ የሚሰጡ ናቸው።
ፕ/ሮ ኢስተርሊና እስክንድር ተገናኝተው ኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው የዲሞክራሲና የኢኮኖሚ እድገት ተወያይተዋል። በተለይ ምዕራብያውያን ለኢህአዴግ የሚጡትን እርዳታ አስመልክተው የሃሳብ ልውውጥ ማድረጋቸውን ከስፍራው የደረሰን ዜና ያስረዳል።
ፕ/ሮ ኢስተርሊ የፊታችን ሮብ ሜይ 23/20 18 ሲ.ፒ.ጄ ባዘጋጀው የእራት ግብዣ ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል። ለክብሩ በተዘጋጀለት ፕሮግራም ላይ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔት አስመልክቶ ንግግር እንደሚያደርግ እና የተለያዩ የመፍትሄ ሀሳቦች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸው ተረድተናል።
በስፍራው የተለያዩ ተቋማትን የወከሉ ግለሰቦች እስክንድር እስር ላይ በነበረበት ግዜ እንዲፈታ ለኢትዮጵያ መንግስት ግልፅ ደብዳቤ ፅፈው የነበሩ አሜሪካዊ ምሁራኖችም እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።