>
5:30 pm - Sunday November 1, 8944

"ለትግራይ ህዝብ የሚያዋጣው የኢትዮጵያ ህዝብ እንጂ ወንጀለኛው ህወሃት አይደለም!!!" [የጄኖሳይድ ዎች ፕሬዚዳንት ፕ/ር ግሪገሪ ስታንተን]

                                  በ አበበ ገላው
በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያው ውስጥ ያለው ትልቁ አደጋ በሌላው ህዝብ መሃል በሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ላይ ነው። ህወሃት በትግራይ ህዝብ ስም በእብሪት በስሙ ሲገድል፣ ሲዘርፍ፣ በንጹሃን ዜጎች ላይ ኢሳብአዊ ግፍ ሲፈጽም፣ በየእስር ቤቱ ጥፍር ሲነቅል፣ ብልት ሲያኮላሽ፣ ዘርኝነትን ሲያስፋፋ፣ ጥላቻ ሲዘራ፣ አገር ሲከፋፍል፣ በገፍ ህዝብ ሲያፈናቅልና በጅምላ ሲያስር በስሙ በሚነግድበት ህዝብ ላይ የሚያከትለውን ጠንቅ ከምንም ባለመቁጠር ነበር።
የጄኖሳይድ ወች ፕሬዚዳንት የሆኑት ፕሮፌሰር ግሪገሪ ስታንተን እኔ የምፈራው ህወሃት የትግራይ ተወላጆችን ለከፋ አደጋ ማጋለጡን ነው ያሉት ከአመታት በፊት ነበር። ለትግራይ ህዝብ የሚያዋጣው የሞተለትና ከወራሪ ለዘምናት የታደገው የኢትዮጵያ ህዝብ እንጂ ወንጀለኛው ህወሃት አለመሆኑ ከምን ጊዜውም በላይ ዛሬ ግልጽ ሆናል።
ያም ሆነ ይህ ያልሰማ ይሰማ። የግሪገሪ ስታንተን የማስጠንቀቂያ ትንቢት የዘመኑ ነብያት አይነት የቅዥት መላ ምት አይደለም። በሳይንሳዊ በጥናት ላይ የተመሰረተ የአደጋ ማስጠንቀያ ነው።
ፕሮፌሰሩ ቃል በቃል የተናገሩት ይሄን ነበር፤ “One of the big worries we have, I say this with real sincerity, is because this is an effectively a Tigrian takeover of the whole country, do you know who is eventually pay for this? The Tigreans. Tigrians will become hated in the country. I lived in Rwanda and Burundi. I saw what happened when an elite basically took over a country. In both these countries the Tutsi elite basically run the countries. So they were very much resented by the Hutus. What was the result? Genocide! I am worried not just for the ordinary people who are Oromos or Amharas or Ogadeni. I am worried for the Tigrians.  Tigrians can become victims of genocide themselves if others turn against them and try to kill them. The name of our organization is Genocide Watch. We are worried about this kinds of forces because they are natural human forces. You can see them develop.”
ትርጉም፤ “ትልቁ ያለብን ጭንቀት፣ ይህንን በእውነት ከልቤ ነው ይምናገረው፣ መላውን አገር ትግሬዎች ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥረውታል። ለዚህ በስተመጨረሻ ዋጋ የሚከፍለው ማነው? ትግሬዎች። በዚች አገር ትግሬዎች ይጠላሉ።
በሩዋንዳ እና ብሩንዲ ኖሬለሁ። አንድ [የጎሳ] ልህቃን አንድን አገር ሙሉ በሙሉ ሲቆጣጠሩ ምን እንደሚሆን አይቻለሁ። በሁለቱም አገሮች የቱትሲ ልህቃን ነበሩ አገር የሚመሩት። የዛ ውጤት ምን ነበር? የዘር ፍችት።
እኔ ኦሮሞ ወንም አማራ ወንም የኦዳዴን ተወላጅ ለሆኑ ተራ ዜጎች አልጨነቅም። የኔ ጭንቀት ለትግሬዎች ነው። ሌሎች ከተነሱባቸው እራሳቸው የዘር ፍጅት ሰለባ ይሆናሉ። የኛ ድርጅት ስም ‘ጄኖሳይድ ዎች’ ነው። ለእንደዚህ አይነት ክስተቶች የምንጨንቅበት ምክን ያት የፈጥሯዊ ሰብአዊ ሃይሎች ስለሆኑ ነው። ክስተቶቹ እያደጉ ሲመጡ ማየት ትችላላችሁ።”
በድጋሚ አውቆ  አልሰማ ያለ ይህወሃቶች ጆሮ ይስማ!
Filed in: Amharic