
ሰሞኑን ባጋጣሚ አንድ ሆስፒታል ሄጀ ነበር የታመመ ዘመድ ለመጠየቅ እና ሃኪሙ የወሰዳቸዉን መረጃወች ድንገት ቻርቱ ላይ አየሁት እና ብሄር አማራ ይላል፡፡ ብሄር መጠየቁ አግባብ ነዉ ወይ የሚል ጥያቄ ተነስቶ ከሃኪሙ ጋር መከራከር ተጀመረ፡፡ ብሄር የተጠየቀበት ምክንያት ተብሎ የተሰጠኝ ምክንያት የመጣበትን አካባቢ በማወቅ የኒዉትሪሽን ስታተሱን ለማወቅ ያግዛል፤ በመጣበት አካባቢ ያለዉን የበሽታ ስርጭትና በሽታዉን አምጭዉን ለማወቅና እንዲሁም አንዳንዴ ለህክምናዉ ሰዉነታችን የሚሰጠዉ ግብረመልስ በዘር ይወሳናል የሚል ነዉ፡፡ ይህ የማያሳምን ሃሳብ ሁኖ አግኝቸዋለዉ፡፡ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴርም ይሄን ለምን እንደፈቀደ እንግዲህ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ በማንኛዉም መንገድ የዘር ጉዳይ ከተነሳ ግን በዋነኛነት አማራን ለመጉዳት የሚደረግ ስለሆነ፡፡ እኛስ የሚያክሙንን ሃኪሞችና ነርሶች ዘር የማወቅ መብት የለንም ወይ? መጠየቅስ አይገባንም ወይ ዝምብለን መሞት ሳይገባን መሞት አለብን ወይ?
ሌላዉ እኒሁ በዘር ጥላቻ የተመረዙ ሰወች ከፍተኛ ጉዳት የሚደርሱት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ነዉ፡፡ በዩኒቨርስቲ ያለፍን ሰወች አማራ በመሆናችን ብቻ የምንመዘነዉ በዘር ሃረጋችን እንጅ በዉጤታችን እንዳልሆን ይታወቃል፡፡ ከቻሉ በመጀመሪያ ስማችን፤ እሱን መለየት ካልቻሉ እስከ አባት እና አያት ስሞቻችን ድረስ እየሄዱ እየለዩ የፈተና ማርኮቻችን እና ብሎም የመጨረሻ ግሬዳችን በማበላሸት የተካኑ አይደሉም ወይ፡፡ ዩኒቨርስቲ ዉስጥ ዉጤት በዘር አይደለም ወይ፡፡ ሌላዉ በዘሩ ምክንያት ያልሰራዉን ሲያገኝ የአማራ ልጅ ያገኘዉን እንኳን ይቀነስበታል፡፡ መጠየቅም ከባድ ነዉ፡፡ በዚህም ምክንያት የአማራ ተማሪዎች በስራ ቦታ ላይ በተለይም ዉጤትን ተኮር ያደረጉ ዉድድሮች ላይ ተወዳዳሪ ሁነዉ እንዳይቀርቡ ይደረጋል፡፡
በስራ ቅጥር ላይ ስንቀጠር ዘራችን እየታየ አይደለም ወይ፡፡ የትዉልድ ቦታ በማየት ስም በማየት ከቅጥር ዝርዝር ማስወጣት አለያም ለምሳሌ በጤናዉና በትምህርት ዘርፉ የአማራ ልጆች የሚመደቡት በረሃ እና ጫካ አካባቢ አይደለም ወይ፡፡ የሶማሌ በረሃወች እና የደቡብ ጫካወች የሚመደበዉ ማነዉ፡፡ሴት እህቶቻችን ለእንጀራ ብለዉ ሄደዉ ስንቱ ተግደለዋል፡፡ ስንቱ ተደፍረዋል፡፡ በአንጻሩ አማራ ክልልና አና አዲስ አበባ የሚመደቡት የትግራይ ልጆች አይደሉም ወይ፡፡ አማራ ክልል ሲቪል ሰርቪሱ የተሞላዉ በትግራይ ተወላጆች ነዉ፡፡ ይህ ሁላችንም በየሰራንበት ቦታ ላይ የምናረጋግጠዉ ነዉ፡፡ የብአዴኑ ጥረት እንኳን ከ 60 በመቶ በላይ ሰራተኞች አማራ ያልሆኑ አይደሉም ወይ፡፡ እነ ታደሰ ጥንቅሹ፤ ህላዊ ዮሴፍ አማራ ጨቋኝ ነዉ እያሉ ዛሬ ድረስ በትግራይ ቴሌቪዠን ቀርበዉ የሚጃጃሉት ሰወች አይደለም እንዴ የዚህ ድርጅት የሰዉ ሃይል ቀጣሪወች፡፡ እናም የግንቦት ሃያ ልጆች ከወላጆቻቸዉ በላይ አደገኛ መሆናቸዉን ማወቅ አለብን፡፡ እኔ ከሌላዉ ኢትዮጵያዊ ጋር ነገሮችን በቀላሉ ማስተካከል ይቻላል ብየ ነዉ የማስበዉ፡፡ የፕሮፖጋንዳ ሰለባ ስለሆነ ይሄን ማስተካከል ነዉ፡፡ ከእነዚህ ሰዎች ግን የሚስተካከል ነገር አለ ብየ አላስብም፡፡