
…
አሁን አቢይ አህመድ እያመጣ ያለው ለውጥ ከጥገናዊ ለውጥም በብዙ ሜትር ርቆ ያለፈና ወደ ስርነቀል ለውጥም ያልተጠጋ በኢህአድግ ዘመን ከኢህአድግ በወጣ ቡድን ይደረጋል ተብሎ የማይታሰብ ተአምራዊ ጉድ ነው።
አቢይ አህመድ መለስ ዜናዊም ሆነ ሀይለማሪያም ደሳለኝ ደፍረውት የማያውቁትን የመከላከያ ጀነራሎች አንድ አዳራሽ ውስጥ አጉሮ ሲፈልግ በአማርኛ ደስ ሲለው ደሞ በእንግሊዚኛ እየቀያየረ በድፕሎማቲክ ቋንቋ ከ 10 አለቃ የማይሻሉ መሆናቸውን ሲነግራቸው ሰምተናል ። ህውሃት ለአመታት ሲጠቀምበት የነበረውን ፌደራል ፖሊስንና የአዲስአበባ ፖሊስን ድምፅ ሳያሰማ ሳይለንሰር በተገጠመበት የፖለቲካ መሳሪያ እየሸራረፈው ነው።
…
አቢይ አህመድ በትናትናው ስብሰባ መከላከያም ውስጥ በቅርብ ሪሻፍል እንደሚደረግ ሳያቅማማ ነግሯቸዋል ። የኢትዮጵያ መከላከያ ነገር አስቂኝ ነው።
የአለም ሀያል ሀገር የሆነችው አሜሪካ ከ 1.5 በላይ የጦር ሰራዊት እያላት የጀነራሎቿ ቁጥር 231 ብቻ ናቸው። የአሜሪካ ህግ የጀኔራሎች ቁጥር ከ231 እንዳይበልጥ ደንግጓል። ኢትዮጵያ ያላት የሰራዊት ብዛት 2 መቶ ሺ አይሞላም ። በዚች ሰራዊት መጠን ግን ከ 400 በላይ ጀኔራሎች አላት። በአለም ላይ በ4ኛ ክፍል የትምህርት ደረጃ ላይ ፕሮፌሰር የሚል ማእረግ የደረበ ጀነራል ማእረግ አገር ነች። አሁን ይሄ ውስጡ ምስጥ እንደበላው እንጨት የበሰበሰና የራሱን ህዝብ በጠራራ ፀሃይ የሚገድል ሰራዊት ሊገልበው እየተዘጋጀ ነው።
…
ትናንት አንዳርጋቸው ፅጌ ለንደን መግባቱን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ “የመሪነት ስነልቡና የታደለ መሪ ” መሆኑን መስክሯል። ይሄን እኔም አምናለሁ ። ለአንዳርጋቸው መፈታት የአቢይ ሚና የአንበሳውን ድርሻ እንደሚወስድ ተናግሯል። ይሄን የሚያውቁት የእንግሊዟ ጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬሳ ሜይ ለአቢይ አህመድ ደውለው አቢይ በአገሪቱ ውስጥ እያደረገ ያለውን ለውጥ እንደሚደግፉትና ከጎኑ እንደሆኑ መናገራቸውን የእንግሊዝ ጋዜጦች በስፋት ፅፈዋል።
ይሄ ሁሉ ሆኖ ግን የጠቅላይ ሚኒሰትር አቢይ አህመድን የለውጥ ባቡር በዜሮ የሚያባዛ ምናልባትም አቢይ እተክለዋለሁ ብሎ ለሚያስበው ስርአት ውድቀት የሚያደርስ ስራ በመሪው ድርጅት ኦህዴድ እየተፈመ ነው። ይሄ ነውረኛ ድርጊት የአማራ መፈናቀል ነው። ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና በአንድ ወቅት እንዳሉት ህውሃት በአማራ ላይ የተከተለው ፖሊሲ እድሜ ልኩን ዋጋ አስከፍሎ ጉዳት እያደረሰበት ነው እንዳሉት ኦህዴድም በአማራ ላይ የሚከተለውን ፋሽስት ባህሪ በእንጭጩ ካልቀጨው ቀጣዩ ጊዜ አስቸጋሪ ነው።