
ማህበሩ በዚሁ ደብዳቤው ላይ እንዳሰፈረው መንግስት ኢሳት ቴሌቪዥን ወደ ሀገር ገብቶ መስራት እንዲችል ጥሪ ማቅረቡ አግባብ አይደለም ብሏል።
ከሁለት አመታት በፊት ኢሳት ባሰራጨው አንድ ዘገባ በትግራይ ህዝብ ላይ ሰፊ ጥላቻ አሰራጭቷል የሚለው ማህበሩ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ውሳኔያቸውን ዳግም እንዲያጤኑ ሲል ጠይቋል።
ይሁንና ማህበሩ ለኢሳት ቴሌቪዢን ከተደረገው ይቅርታ በስተቀር መንግስት ሀገራዊ መግባባትና እርቅ ለመፍጠር የሚያደርገውን ጥረት ከልብ እንደ ሚደግፍ በደብዳቤው አስፍሯል። የማህበሩን ደብዳቤ አያይዘናል።