>

የዕንቁው ኢትዮጵያዊ ፕሮፌሰር የመጨረሻዎቹ ቀናት እስከ ስንብት!!! (ታማኝ በየነ)

ታላቁ ኢትዮጵያዊ ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ለስድስት ዓመት ያህል በግፍ ከታሰሩ በኋላ የጤናቸው ሁኔታ እያሽቆለቆለ ሲመጣ ወደ ውጭ ሀገር እንዲሄዱ ተደረገ። በአሜሪካን ሀገር ሂውስተን ግዛት ውስጥ በሚገኘው የመድሃኒዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ተገኝተው ከስድስት አመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ጸሎት አደረጉ። በዚች ዕለት የታዩት አስራት በአካልም በመንፈስም ጠንካራ ሆነው ነበር ። ይህ በሆነ በሁለት ሳምንት  ጊዜ ውስጥ ግን አረፉ የሚልዜና ተሰማ ። በሂውስተን መድሃኒአለም ቤተክርስቲያን ያደረጉት ንግግርም የመጨረሻው የአደባባይ ንግግራቸው ሆነ። በዚህ አጋጣሚ ያንን መድረክ ያመቻቹትን በሂውስተን የመድሃኒዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ምእመናን ካህናት የቦርድ አባላትና የቦርዱ ሊቀመንበር የነበሩት አቶ መስፍንን እንደ አንድ ዜጋ ከልብ አመሰግናቸዋለሁ።
ታላቁን ኢትዮጵያዊ ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስን ወደ ሀገራቸው በክብር ለመሸኘት በቨርጂኒያ በተዘጋጀው ፕሮግራም ላይም ከመላው አሜሪካ በተለይም ከሜሪላንድ ከዋሽንግተን ዲሲና ከቨርጅኒያ የተሰበሰበው የህዝብ ብዛት የሚገርም ነበር።
በታላቅ ክብር ወደ ኢትዮጵያ የተሸኘው የፕሮፌሰር አስራት አስከሬን አዲስአበባ ሲገባ ትኩረት እንዳያገኝ መንግስት ቢጥርም ህዝብ በነቂስ ወጥቶ እያለቀሰ ሳይሆን እየዘመረ እያነባ ሳይሆን አስራት አልሞተም እያለ በእልህ ሸኛቸው።
የአስራትን የህዝብ ፍቅር ለማየት እድል ላላገኛችሁ ወጣቶች ይሄ ፊልም ፍንጭ ይሰጣችኋል ብየ ተስፋ አደርጋለሁ ።
ህይወታቸውን በሙሉ ሀገራቸውን ያገለገሉት አስራት ወልደየስ ስራና ስማቸው ዘላለማዊ ነው።

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=1634045420047913&id=177754275677042

Filed in: Amharic