አንድ ወቅት ሊክ ያደረገው የዊክሊክስ ኬብል እንደነገረን ጌታቸው አሰፋ ከቀድሞው በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ዶናልድ ያማሞቶ ጋር 3 ጊዜ ተገናኝቷል። በዚህ የ3 ጊዜ ውይይት ወቅት ዶናልድ ያማሞቶ ግርድፍ ፀባይ ስላለው ጌታቸው የግል ባህሪ ለሲአይኤ አስተላልፏል።
…
ከሶስት ጊዜ ግንኙነታቸው ውስጥ በአንዱ ቀን ውይይታቸው ጌታቸው አሰፋ ያማሞቶን
<< አሜሪካ አገሯ ውስጥ ያሉትን እንደ ግንቦት 7 ፣ ኦነግና ኦብነግ ያሉትን አሸባሪዎች ማስጠጋት ካላቆመች እኔም አዲስ አበባ ላይ የአሜሪካ ተቃዋሚዎችን አደራጅቼና አስታጥቄ አገራችሁን አተራምሳለሁ: >> እንዳለው በከፍተኛ ሳቅ ጭምር ለሲአይኤ አስተላልፏል። የጌታቸው አሰፋ ኢግኖራንስና አሮጋንስ ጥጉ እስከዚህ ይደርሳል።
…
ለማንኛው ይሄ ሰው ትናንት ገለል ተደርጓል።
አሁን አቢይ አህመድና መዋቅሩ የበፊቱን የአፈና መዋቅር በአንፃራዊ ሁኔታ በማፈራረስ ሁለት እግሩን ተክሏል።
ከዚህ በኋላ የአቢይ መንግስት Deep state የሚባለውን የደህንነትና የፀጥታ መዋቅር ስለተቆጣጠረ በኢሮሚያና በሌሎች ክልሎች የሚፈፀሙትን ማፈናቀሎችና የሰብአዊ መብት ጥሰቶች በወያኔ ማሳበብ አይችልም።