>
5:09 pm - Friday March 3, 0417

የባድመ ጉዳይ ለአማራው ምኑ ነው? አያገባንም! ለምትሉ፦ (ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው) 

ወያኔ ባድመን ጾረናንና ሌሎች አዋሳኝ ቦታዎችን ለሸአቢያ ሊያስረክብ እንደሆነ ከገለጸበት ቅጽበት ጀምሮ የወያኔ ጎጠኛ ፀረ ኢትዮጵያ ጠባብ የጥፋት አስተሳሰብ ሰለባ የሆነው ሁሉ “እኛን ምን አገባን! ይሄ የትግሬ ጉዳይ ነው ሲፈልጉ ይስጡት ካልፈለጉ ይተውት!” የሚል ያልበሰለ አስተሳሰብ እያንጸባረቁ ይገኛሉ፡፡
ተራ የሚባለው ዜጋ ይሄንን ቢል አይደንቅም፡፡ ይሄንን እያለ ያለው የነቃሁ ነኝ የሚለው መሆኑ ነው አስገራሚው፡፡ እንዲህ ከሚሉት እራሳቸውን እንደነቁ የሚያስቡ ወገኖች አብዛኞቹ የወያኔ ቅጥረኞች ናቸው፡፡ የወያኔ ባለሥልጣናት መሰንበቻቸውን “በባድመ ጉዳይ የትግራይ ሕዝብ እንጅ የኢትዮጵያ ሕዝብ አይመለከተውም!” እያሉ ሲለፍፉ እንደሰነበቱ ልብ ይሏል፡፡
የወያኔ ባለሥልጣናት እንዲህ ሲሉ የሰነበቱበት ምክንያት ባድመንና ሌሎች አዋሳኝ ቦታዎችን ለሸአቢያ በሚያስረክቡበት ጊዜ የኢትዮጵያ ሕዝብ ተቃውሞ እንዳያሰማ ለማድረግ በማሰብ ነው፡፡ ይሄም ብቻ አይደለም ወያኔ ከሀገሪቱ ሰፊ መሬት ቆርሶ ለሱዳን የሰጠው መሬት ጉዳይ የጎንደር ወይም የአማራ ብቻ እንጅ የኢትዮጵያ ወይም የኢትዮጵያ ሕዝብ ጉዳይ እንዳልሆነ እንዲታሰብ በማድረግ ዜጎች የሀገር ድንበርንና ሉዓላዊነትን የማስከበር የዜግነት ግዴታቸውን በመወጣት ለሱዳን የሰጠውን መሬት ለማስመለስ እንዳይተጉ ለማድረግም ነው፡፡
በዚህ መሠረት ነው ምን እያደረገ እንደሆነ ከማያውቀውና ቅጥረኞቹ ካሳሳቱት ጀሌ በስተቀር ሌሎቹ ወይም ቅጥረኞቹ ግን ለምና ሜዳማ የእርሻ መሬት የሆነውን እንዲሁም የወርቅ መዓድን እንዳለው የሚነገርለትን ባድሜን አንዴ “ባድመ ድንጋያማ መሬት ነውና ቢሔድም አይጎዳም!” የሚል የተሳሳተ መረጃ በመስጠት ሌላጊዜ “እኛን አይመለከተንም የሚመለከተው የትግራይን ሕዝብ ነው!” በማለት ፀረ ኢትዮጵያና ጎጠኛ የጥፋት አስተሳሰብን በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ በማስረጹ ሥራ ላይ እየተጉ ያሉት እንደቅጥረኝነታቸው ወያኔን ለማገዝ በማሰብ ነው ተግተው ይሄንን እያደረጉ ያሉት፡፡ ወያኔ ኢትዮጵያን ማፈራረስ ካለበት ቀድሞ መሥራት ያለበት ዕኩይ ሥራ ይሄ በመሆኑ ነው ተግቶ እየሠራበት ያለው፡፡
በመሆኑን ለየዋሁ ጀሌ በተለይም ወያኔ የሀገር ክህደት በመፈጸም ከሀገራችን ቆርሶ ለሱዳን የሸጠው ወይም ሱዳን ለዋለችለት ውለታ ምላሽ የለገሰው ሰፊ የሀገሪቱ መሬት የኢትዮጵያ መሬት እንደመሆኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ ዋጋ ከፍሎ በማስመለስ የሀገሩን ድንበርና ሉዓላዊነት እንዲያስከብር የምንፈልግ ወገኖች “ባድመ የትግራይ እንጅ የእኛ ጉዳይ አይደለም!” ስንል ወያኔ ለሱዳን የሰጠው መሬት ጉዳይ “የጎንደር ሕዝብ ጉዳይ እንጅ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጉዳይ አይደለም!” ማለታችን እንደሆነ ተረድተን በቅጥረኞቹ ሐሰተኛና አሳሳች ፀረ ኢትዮጵያ ጠባብ የጥፋት ስብከትን ከማራገብ እንቆጠብ ዘንድ ማሳሰብ እወዳለሁ፡፡
ይሁንና ይሄንን ስል ግን የትግሬ አክቲቪስቶች (ስሉጣን) ትናንትና “ግንቦት ሃያ የትግራይ ሕዝብ የድል በዓል እንጅ የኢትዮጵያ ሕዝብ በዓል አይደለም! ደርግን ያሸነፈው የትግራይ ሕዝብ እንጅ የኢትዮጵያ ሕዝብ አይደለም!” እያሉ ይህ የሚሉት ነገር ሲበዛ እውነትነት የጎደለው መሆኑን እያወቁ ከተጣባቸው ጠባብነትና ካደረባቸው የድንቁርና ደዌ የተነሣ ትንሽም ሳያፍሩ ደርግን የጣሉት እነሱ ብቻ እንደሆኑ አድርገው ሲያስተጋቡና ጠባብነትን እጅግ አሳዛኝ በሆነ መልኩ ሲያቀነቅኑ እንዳልነበረ አሁን ወያኔ ባድመንና ሌሎች አዋሳኝ ቦታዎችን ያለአንዳች ቅድመ ሁኔታ ለሸአቢያ ሊሰጥ እንደሆነ ሲገልጽ ጊዜ ሰው ይታዘበናል ሳይሉ ዓይናቸውን በጨው አጥበው ኢትዮጵያ እና የኢትዮጵያ ሕዝብ እያሉ ደጋግመው በማላዘን የኢትዮጵያ ሕዝብ ውሳኔውን እንዳይቀበል ስሜት ይቀሰቅሳል ብለው ባሰቡት መንገድ ማላዘን ይዘዋልና ለዚህ እፍረተቢስ ጥሪ አዎንታዊ ምላሽ እንስጥ እያልኩ አይደለም፡፡
በፍጹም እንደዚህ እያልኩ አይደለም! ምክንያቱም፦ 
* የትግሬ ሕዝብ ባድመ ጾረና እና ሌሎች አጎራባች ወረዳዎች ለሸአቢያ እንዲወሰንለት ከሀዲው መለስ ዜናዊ መረጃዎቻችንን በመሠወርና ለሸአቢያ ሽንጡን ገትሮ በመመስከር ሻጥርና ክህደት እንደፈጸመ እያወቀ ሲያመልከው ነበርና ነው፡፡
* ምክንያቱም እነሱ እንዳይሆን አድርገው ያበላሹትን ነገር እነሱ ካለቁ በኋላ ካልሆነ በስተቀር ነገሩን በክህደት ያበላሹት እነሱ እያሉ እነሱን አስቀምጠን እኛ ዋጋ መክፈል ስለማይኖርብንና ስለሌለብንም ነው፡፡
* ምክንያቱም የትግሬ ሕዝብ ከ70 ሽህ በላይ የፈሰሰውን የወገናችንን ደም ደመከልብ አድርጎታልና ነው፡፡
እኛ ባድመንና ሌሎች በክህደት የተሰጡ መሬቶቻችንን ለማስመለስ ብለን የምንዘምተው ይህ ክህደት እንደተፈጸመ እያወቀ ዝም ብሎ የተመለከተውና ዝም ብሎ በመመልከቱም ነገሩ እጅግ በሚያሳዝን ሁኔታ እንዲበላሽ ምቹ ሁኔታን የፈጠረው የትግሬ ሕዝብ ተንጠፍጥፎ ካለቀ በኋላ ነው፡፡
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
Filed in: Amharic