>

ሰሞኑን በቤተ - መንግስት (መረጃ ) - ሀብታሙ አያሌው

የኢኮኖሚ ሳቦታጅ እየተፈፀመብኝ ነው የሚለው የዶክተር አብይ ንግግር እረፍት ስለነሳኝ የነገሩን ዱካ በመከተል የመረጃ ምንጮቼን ሁሉ በሚገባ አሰስኩ በመጨረሻም የችግሩ ስር የተቀበረበት የደህንነት መስሪያ ቤቱ ቢሮ ደረስኩ።  ዋና ዳይሬክተሩ ጌታቸው አሰፋ የሳቦታጁም ሊቀመንበር ሆኖ ጠቅላዩን ሰንጎ ይዟቸዋል።  እጅግ እልህ አስጨራሽ ውዝግብ ተካሂዶም አሻፈረኝ ስላለ ለጊዜው በጀነራል ሳሞራ የኑስ ድጋፍ ከቢሮው ገለል ተደርጎ ሽምግልናው ቀጥሏል።  ነገር አክርሮ ባሻፈረኝ ከፀና እኛን ወዳሰቃየበት ዘብጥያ ሊያመራ ይችላል፤  እራሱን ከኢህአዴግ የተሃድሶ ሂደት ጋር ካስማማ ነገሮች መልካም ይሆኑለታል። ለጊዜው የቤት ውስጥ እስረኛ ለመሆን ተገዷል።
ጀነራል ሳሞራ የባድመን ጉዳይ በተመለከተ በመፍትሄው ቢስማማም እሱ ከስድስት ወራት በኋላ በጡረታ ሲሰናበት ይፋ እንዲሆን ያቀረበውን ሃሳብ ወደጎን በማለት በተጣደፈው የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ስብሰባ በመወሰናቸው ለቁጣው መግለጫ ስልጣኑን በሁለት ቀናት ውስጥ እንዲረከቡት ለዶክተር አብይ አሳሰበ ኩርፊያውን ገለጠ። ዶክተር አብይ ሳሞራን መድረክ ላይ አምጥተው በሽልማት የመሸኘት ዜና ያስነገሩት እጅግ አድካሚ ከሆነ ሽምግልና በኋላ ነበር።
የጀነራል ሳሞራን ወንበር ለመተካት ወደ ከፍታው የመጣው ጀነራል ሰዓረ ከመለስ ጋር አይን እና ናጫ የነበረ ቢሆንም  የደህንነቱ የጌታቸው አሰፋ ወዳጅ በእውቀት እና በብቃት ሲመዘን ከጀነራል አበባው በታች ቢሆንም ከሳሞራ የተሻለ እንደሆነ ይነገርለታል።  ሰዓረ እና ሳሞራ ከፍተኛ ቅራኔ ውስጥ የነበሩ ባላንጣዎች በመሆናቸው ሳሞራን አሳምኖ የህወሓት ፍላጎት የሆነውን ሰዓረን ለመሾም፤  አሻፈረኝ ያለውን የደህንነቱን ጌታቸው አሰፋን ገለል ለማድረግ፤  ጀነራል ሰዓረን በስልጣን ማባበል ዶክተር አብይን የፈተነ የመተካካትና የጥገና ሂደቱ ከባድ ክፍል እንደ ነበረ መረጃውቼ አመልክተዋል።
በህወሓት አሽከርነት የሚታወቁት ጀነራል አደም በብአዴን አቅራቢነት በጌታቸው አሰፋ ምትክ መሾማቸውን ህወሓት በደስታ ተቀብሎታል። ጀነራል አደም ለህወሓት ታማኝ ሆነው የአየር ሃይል አዛዥ ሆነው ለመቆየት የቻሉ በአየር ሃይሉ አባላት በእጅጉ የሚጠሉና የሚናቁ ሰው ናቸው። በእሳቸው ዘመን የአየር ሃይሉ ሁለቱም ቤዝ ከድሬዳዋም ከደብረዘይትም ተነቅሎ ትግራይ እንዲሄድ ከህወሓት በላይ ህወሓት ሆነው  ከፍተኛ ሚና መጫወታቸው ይነገራል።
አየር ሃይሉ በራሱ የእስር ቤት እንዲሆን ከማድረግ ባሻገር የጌታቸው አሰፋን የዘር ምንጠራ በማስፈፀም በርካታ መኮንኖችን ለእስር ለስደት በመዳረግ እንዲሁም በሙስና ይወነጀላሉ።
     በቀሪው እመለስበታሁ
Filed in: Amharic