>
5:09 pm - Friday March 3, 3065

የሁለቱ ሚጢጢ ዝሆኖች እርግጫ የህዝቦችን አንድነት ለማጠናከር  ያለውን እድል ያወሳስበዋል!!! (ደረጄ ገረፋ ቱሉ)

በዚህ  የብሄር አደረጃጀት ላይ ያሰረፍኩትን የመጀመሪያ ጥቃት (የመጀመሪያ ግለ ሂስ ) ለማጠቃለል፦
1 አዲሱ የአማራ ፓርቲ ቤአዴንን ለማሸነፍ እና ትኩረት ለማግኘት ከረር ያለ አቋም መያዙ አይቀርም።
2 አሁን በለው ሁኔታ ከቀጠለ OFC ያለው አማራጭ የኦሮሞን ትኩረት ለመሳብ እና ኦህዲድን ለማሸነፍ ያለው ብቸኛ አማራጭ ጣንካራ ብሄርተኛ መሆኑ ብቻ ነው።
3 ሁለቱ ቤሄርተኞች ( OFC እና አዲሱ የአማራ ፓርቲ) አብሮ መስራት ሳይሆን ባላንጣ ሆነው የመቀጠላቸው እድል እጅግ ሰፊ ነው።ምክንያቱም ሁለቱም ጠርዝ ላይ ካልቆሙ መቆም አይችሉም።መሃሉ ተይዟል።
4 ሁለቱ ብሄርተኛ ድርጅቶች የመጀመሪያውን ግጭት የሚፈጥሩት በሸገር ጉዳይ ላይ ይሆናል(ሚክ አማራ በቅርቡ የአማራ ብሄርተኝነት በሸገር ይለመልማል ያለው ጥሩ ምልክት ነው።) ።
በነገራችሁ ላይ ኢህአዲግ የመውጫ በር ካላዘጋጀላቸው በስተቀር ሁለቱ ቡድኖች እስከወዲያኛውም በዚህ ጉዳይ ላይ የመስማማት እድላቸው እጅግ ጠባብ ነው።እናም የነሱም ተስፋ ኢህአዲግ አይደለንም ለማለት ነው።
ለማንኛው ይህ የሁለቱ ሚጢጢ ዝሆኖች እርግጫ  ሀገሪቷ ውስጥ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ለመገንባት እና ሀገሪቷ ውስጥ ያለውን የህዝቦች አንድነት ለማጠናከር  ያለውን እድል ያወሳስበዋል።
5 አዲሱ የአማራ ድርጅት እና ብአዴን ለተወሰነ ጊዜ በወዳጅነት ይሰራሉ።ብአዴን ለተወሰነ ጊዜ ፍስክ ፍስኩን( እንደ መንግስት የማይነገረውን)   በዚህ ፓርቲ በኩል ለህዝቡ ሊያቀርብ ይችላል።
ፓርቲው ለምስረታው ሙላዓለም አደረሽ መጠቀሙን እና የአማራ ብዙሃን መገናኛ ኤጄንስ ለምስረተው የሰጠውን ሽፋን ልብ ማለት ጥሩ ነው።
ይህ የብአዲን እና የአዲሱ ፓርቲ ወዳጅነት ከተወሰነ ጊዜ በኃላ ሊሸክር ይችላል።
6 በፖለቲካ አይን ብቻ ካየነው ከአዲሱ ፓርቲ መመስረት ኢህአዲግ ተጠቃሚ ይሆናል።በተለይ ብአዲን እና ኦህዲድ ወዳጅ ሆነው የመቀጠላቸው እድል ሰፍ ነው።በጭንቅ ጊዜ ሁለቱ ፓርቲዎች የሚወክሉትን ህዝብ በነዚህ ፓርቲዎች በኩል እንደማስፈራሪያ ሊያቀርቡ ይችላሉ።የጭንቅ ጊዜ ለሚወክሉት ህዝብ በውስጥ በኩል  ማጣብህ አይነት ጨወታ ሊጫወቱ ይችላሉ።
7 ጠቅላይ ሚንስትር አቢይ እና ፕረዝዳንት ለማ በጣም ከፍ ያለ ብስለት ካላሳዩ በስተቀር OFC ፍሽካ ነፍቷል።በኦህዲድ እና በ OFC መካከል በሚቀጥለው ሁለት ዓመት ውስጥ እልህ አስጨራሽ ትግል ሊካሄድ ይችላል።ውጤቱም ለህዝቡ ጥሩ አይሆንም።ይህ በሁለቱ ፓርቲዎች መካከል የሚደረገው እልህ አስጨራሽ ትግል ክልሉን ብቻም ሳይሆን ሀገሪቷንም ወደ ጠቅላላ ቀውስ ሊመልሳት ይችላል።በአጭሩ ጥንቃቄ ካልተደረገ በሁለቱ ፓርቲዎች መካከል የሚደረገው ፍትግያ የሜኤሶን እና የኢህአፓ አይነት ሽኩቻ ሊያስከትል ይችላል።
ይህ ሟርት አይደለም።ከወዲሁ ሁሉም እንዲያስብበት እና የሚሆነውን በማድረግ መሆን ያሌለበትን እንዳይሆን እንዲናደርግ ነው።ደርግ ያላልኩት የፕረዝዳንቱ እና የጠቅላይ ሚንስትሩ ባህሪይ ወደዚያ ይወስዳል ቢዬ ስለማላስብ ነው።በአጭሩ በዚህ በኩል በጥንቃቄ ከተሰራ ነገሩ በቀላሉ መፍትሄ የሚያገኝ ነገር ነው።ካልሆነም አደገኛ ነገር የመፈጠር እድሉ ሰፍ ነው።እናም ጥንቃቄ ያስፈልጋል።
8 ህወሃት ከዚህ በኃላ ከቀውስ የማገገም እድሉ እጅግ ጠባብ ነው።ህወሃት የአመራር ቀውስ ብቻም ሳይሆን ከዚህ በኃላ ሀገሪቷን የሚያጋጥሟት ቀውሶች ሁሉ እንደ ጦስ ዶሮ ስለሚወረወሩበት ሊያገግም አይችልም።ህወሃትን ከዚህ በኃላ ከገባበት አጣብቂኝ የሚያወጣው በሳል መሪ በአከባቢው አይታየኝም ።ህወሃት ከዚህ በኃላ የሃይል እርሚጃ እንኳን ሊሞክር ብል እንደገና ለተጨማሪ ኪሳራ ይዳረጋል።
እናም በሁሉም መልኩ የማገገም እድሉ ዜሮ ነው ባይባልም እጅግ አናሳ ነው።
አረና ከበረታ ከረጅም ርቀት ጭላንጭል ብረሃን አለው።አረና ከዚህ በኃላ እጅግ ብዙ ምስጥሮችን ከደህንነት መስሪያ ቤቱ እና ከመከላከያው በአኩራፍ Officer/ች የማግኘት እድሉ ሰፍ ነው።
ይህ ማለት ግን ህወሃት ይሸነልፋ ማለት እንዳልሆነ ይሰመርበት።ህወሃት ኢህአዲግ እስካለ ድረስ ይኖራል።
9 ቤተ አማራ ምነው ዝም አለ?
10 ጀማሪ የኦሮሞ ቤሄርተኞች አባታችሁ ለታክቲካል የሚሰጠውን ድጋፍ የእስትራቴጅ አታድርጉት።እሱ ዛፍ ስተክ ተክላችሁ እሱ ስንቅል መንቀል አዝሏችኃል።እናም ሃይል ቆጥቡ ።
11 የጠቅላይ ሚንስትር አቢይ እና የፕረዝዳንት ለማ ያልተጠበቀ  ማርሽ ቀያር የፖለቲካ  ውሳኔ ሁሉንም ነገር ዜሮ አድርጎ የፖለቲካ ፓርቲዎችን አካሄድ ውጥንቅጡን ሊያወጣ ይችላል።ሁሉንም ዜሮ አዲርጎ የፖለቲካ እስኬሉን ሊሰቅለው ይችላል።በአጠቃላይ ብሄር ነክ ችግሮችን ቆጥረው በመመለስ  የብሄር ፖለቲካን (ብሄርን አላልኩም) መቃብር ሊፈፅሙ ይችላሉ።ብሄር ለምልሞ የብሄር ፖለቲካ የሚከስምበት ጊዜም ቅርብ የመሆን እድል አለው ለማለት ነው።
በነገራችሁ ላይ ጤነኛ  ብሄርተኝነት ( ብሄር ነክ ችግሮች ከተወገዱ) ስለመልም የብሄር ፖለቲካ ይጠወልጋል።
ይህንን ሊያስቀር የሚችለው በቀጣይነት ሀገሪቷን ሊገጥማት የሚችለው  ፈታኙ የኢኮኖሚ ቀውስ ብቻ ነው።
እነ አቢይ የኢኮኖሚ ቀውሱን በአጭር ጊዜ ውስጥ ከፈቱት ከዚህ በኃል  ሁሉም ነገር እዳው ገብስ ነው።
12 በቅርቡ ኢህአዲግን የሚያሸንፍ ፓርቲ አይኖርም።ኢህአዲግን የሚያሸንፍ ፓርቲ የሚፈጠረው ኢህአዲግ የብሄር እና የኢኮኖሚ ችግሮችን ፈቶ የሀገሪቷን socio- economic ሁኔታ ሲቀይር ብቻ ነው።ኢህአዲግ የሚሸነፈው ኢህአዲግ ሲሳካላት ብቻ ነው።ኢህአዲግን በየ አከባቢው የሚያንገጫግጨው ሃይል ግን በየ ምርጫው ከዚህ በኃላ በተደጋጋሚ የመፈጠር እድሉ ሰፊ ነው።ይህ ሃይል በሀገር አቀፍ ደረጃ መንግስት ሆኖ የመውጣት እድሉ ግን እጅግ ጠባብ ነው።ይህ እንዲሆን የሀገሪቷ socio -economic ማዕቀፉ መቀየር አለበት።በአጭሩ ኢህአዲግን ለማክሰም ኢህአዲግ እንዲሳካላት መተባበር የግድ ነው።
13 አትንጫጩ!! ምክንያቱም ከወራት በኃላ እኔ ያልኩትን ነገር ማድረጋችሁ አይቀርም እና!!
በተያያዘ ….

በዘር ተቧድነው የተደራጁ ጎጦች የአማራውን በዘር የመደራጀት ሁኔታ ለማጣጣል ሞራል የላቸውም!!!

ሚልዮን አየለች
ከሰላሳና ከአርባ አመት በላይ በዘር ተቧድነው ተደራጁ በላዩም አንድን ማህበረሰብ ሰቅዞ የያዘውን አንጃ መጋፈጥ ያልቻሉ ጎጦች የአማራውን በዘር የመደራጀት ሁኔታ ለማጣጣል ሞራል የላቸውም  የዘር ፖለቲካ ፍፁም ለኢትዮጵያዊነትን እንደማያዋጣ የተደበቀ ጉዳይ አይደለም አስቀድመው ግን እራሳቸውን ለግማሽ ምዕት አመታት በጎጥ አደራጅተው ለዘራቸው ብቻ ሲሰሩ የነበሩት ቡድኖች ለኢትዮጵያ አንድነት ሲሉ መፍረስ የጠበቅባቸዋል በላዩም አንድነትን ለማስፈን ዘራዊ ከሆነ የፖለቲካ አደረጃጀቶች ህብረ ብሄሮች የበለጠ ስራ ይጠበቅባቸዋል ህዝቡ አንድ ከሆነ እና ኢትዮጵያ ለአንዱ እናት ለሌላኛው የእንጀራ እናት መሆኗን ማስቆም ከተቻለ ሁሉም በዘር የተገነባው ብድን ወደ ህብረ ብሄራዊነት እንደሚመጣ አልጠራጠርም ስለዚህ የአማራው መደራጀትን አልነቅፈውም።
Filed in: Amharic